በሀዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ።
- sheger1021fm
- 3 hours ago
- 1 min read
ህዳር 17 2018
በሀዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ።
ግለሰቡ በጂንካ ከተገኘው የመጀመሪያው የማልበርግ ቫይረስ ተጠቂ ጋር ንክኪ የነበረው ወደ አካባቢው ተጉዞ ወደ ሃዋሳ ተመላሽ የነበረ ነውም ተብሏል።
ይህ የተባለው የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማርበርግ ቫይረስ ዙሪያ እየሰሩት ያለውን ስራ በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
በዚህም ወቅት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ላሉ ሰዎች በየእለቱ የላብራቶሪ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ቫይረሱ ከተከሰተበት ከህዳር 5ቀን እስከ ህዳር 17ቀን 2017ዓ.ም ድረስ 73 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል ያሉት ሚኒስትሯ በዚህም 11 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 6ቱ ህይወታቸው አልፏል፤ 5ቱ ደግሞ በህክምና ላይ ናቸው ሲሉም አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ሌሎች ሃገራት ላይ ተሞክሮ ለውጥ ያመጣ ዶሚድስፔር የተባለ ፀረ ህዋስ መድሃኒት ወደ ሃገር ቤት በማስገባት ለ16 የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም በህክምና ላይ ላሉት 5 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሰጥተናል ብለዋል።
መድሃኑቱ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር መቅደስ በህክምና ላይ ያሉት 5ቱ ተጠቂዎች የማገገም ሂደት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።
በፅኑ ህሙማን ክፍል 1 ታማሚ እንዳለ የተነገረ ሲሆን አስፈላጊው ክትትል እየተደረገለት ነው ተብሏል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








