top of page

ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) የህይወት ዘመን ጋዜጠኝነት ሽልማት ተሰጣቸው።

  • sheger1021fm
  • Dec 1, 2025
  • 1 min read

ህዳር 22 2018


ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) የህይወት ዘመን ጋዜጠኝነት ሽልማት ተሰጣቸው።


የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ መስራችና ስራ አስኪያጅ #መዓዛ_ብሩ ሽልማቱ የተሰጣቸው የኢጋድ(IGAD) ዓመታዊ የሚዲያ ሽልማት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት ነው።

ሽልማቱንም ከኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስና ከኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር ) ተቀብለዋል።


ኢጋድ በየዓመቱ በተለያዩ  ዘርፎች የአባል ሀገራትን የተመለከቱ ዘገባ የሰሩ ጋዜጠኞችን የሚሸልም ሲሆን ዘንድሮም የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከቱ ዘገባዎች የሰሩ ጋዜጠኞች ስራ አወዳድሮ ሸልሟል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page