የህዳሴው ግድብ የሚያመነጨውን ሃይል በተመለከተ የተለያየ ቁጥር ሲጠቀስ የነበረው በምን ምክንያት ነበር?
- sheger1021fm
- 4 hours ago
- 1 min read
ህዳር 17 2018
የህዳሴው ግድብ ከግንባታው መጀመር እስከ ፍፃሜው በነበረው ሂደት የሚያመነጨውን ሃይል በተመለከተ የተለያየ ቁጥር ሲጠቀስ ቆይቷል።
5150 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው ግድቡ በአንድ ወቅት የማመንጨት አቅሙ 6450 ሜጋ ዋት ነው፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ 5250 ሜጋ ዋት ያመነጫል የሚሉ የተለያዩ ቁጥሮች ሲጠቀሱ ነበር።

ለመሆኑ ይህ የተለያየ ቁጥር በመንግስት የሰራ ሀላፊዎች ሲጠቀስ የነበረው በምን ምክንያት ነበር?
የቀድሞው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትርና የግድቡ የሶስትዮሽ ድርድር መሪ ተደራዳሪ ስለሺ በቀለ(ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ በግንባታው ሂደት የተለያየ ለውጥ ይደረግ እንደነበር አንስተዋል።
በመጨረሻ በተደረገው ማሻሻያም የነበሩ ችግሮችን በማረም ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉን ያብራራሉ።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








