ኢትዮጵያ በአፍሪካ የንግድ ቀጠና ተወዳዳሪ ለመሆን በብዛትም በጥራትም ማምረቱ ላይ እንድትበረታ ተመክራለች
- sheger1021fm
- Nov 25
- 1 min read
ህዳር 16 2018
ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከሚላኩ ምርቶች መካከል እንደ አትክትልና ፍራፍሬ የግብርና ምርቶች ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የንግድ ቀጠናን መቀላቀሏን ተከትሎ ከቀረጥ ነፃ ምርቶቿን ስለምትልክ ተወዳዳሪ ለመሆን በብዛትም በጥራትም ማምረቱ ላይ እንድትበረታ ተመክራለች፡፡
ይህንን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የውጪ ምንዛሪ እንድታገኝ የግብርና ዘርፍ ላይ እንዴት መሰራት አለበት? ስንል የዘርፉ ባለሞያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ግብርና ኢንስቲትዩት የግብርና ኢኮኖሚክስ ዳይሬክተር እና ተመራማሪውን ታደለ ማሞን(ዶ/ር) ጠይቀናል፡፡
ገዢ ሃገራት ምን ይፈልጋሉ? የሚለውን ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉን ባለሞያው የጥራት ጉዳይ ደግሞ ቀዳሚ እንደሆነም አክለዋል፡፡
በተለይም ድንበር አካባቢ ማለትም በሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን አካባቢ ያሉ አርሶ አደሮች እዚያው አምርተው እዚያው የሚሸጡበት ሂደት ስላለ ይህንን ማስተካከል ያስፈልጋል ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments