ኢትስዊች ለመጪዎቹ 15 ዓመታት የሚመራበትን እቅድ እንዲያዘጋጅለት ከአለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ጀነሲስ አናሊቲክስ ጋር ተፈራረመ፡፡
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 1 min read
ህዳር 17 2018
ኢትስዊች ለመጪዎቹ 15 ዓመታት የሚመራበትን እቅድ እንዲያዘጋጅለት ከአለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ጀነሲስ አናሊቲክስ ጋር ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱ ዘርዘር ያለ የ5 ዓመት መሪ እቅድ መቅረጽንም እንደሚያካትት በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ወቅት ተናግሯል፡፡
ኢትስዊች ባለፉት 5 ዓመታት የሰራቸው ስራዎች በተመለከተ ሰፊ ግምገማ ማድረጉን ተናግሮ ወደፊት ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ደግሞ ጀነሲስ አናሊቲክስ እንዲሰራ ስምምነት አድርጓል፡፡
በፋይናንስ ተቋማት መካከል በዲጂታል አማካኝነት የሚደረጉ ግብይቶችን ወይም ክፍያዎችን ተናባቢ ማድረግ፣ የሀገር ውስጥ የክፍያ ሥርዓት ማቅረብ፣ የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ አገልግሎት መስጠት፣ ለፋይናንስ ተቋማት የጋራ መሰረተ ልማትና ሥርዓት ማቅረብን ጨምሮ ሌሎች ስራዎች ኢትስዊች ሲሰራ መቆየቱን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ይለበስ አዲስ አስታውሰዋል፡፡

ሀገር ከያዘችው የዲጂታል ኢትዮጵያ ፕሮግራም ፣ ከብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ ኢትስዊች ያሉ ተቋማት ምን እየሰሩ ነው? የሚሉትን አካቶች የአምስት አመቱ መሪ እቅድ እንደሚሰናዳም ዋና ስራ አስፈፃሚው ጠቅሰዋል፡፡
ጀነሲስ አናሊቲክስ መሪ እቅዱን ለመስራት የእስካሁን የኢትስዊችን ስራዎች እንደሚገመግም፣ የፋይናንስ ተቋማት ደግሞ ወደፊት ብሄራዊ ኢትስዊቹ ምን እንዲሆንላቸው እንደሚፈልጉ ጠይቆ ስትራቴጂውን ይሰራል ተብሏል፡፡
ኢትስዊች ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ በሁሉም የግል እና የመንግስት ባንኮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ የተቋቋመ ብሔራዊ ስዊች ነው፡፡
በቅርቡ የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት፣ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተሮች እና የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪዎች በባለቤትነት ተቀላቅለውታል፡፡
ዋና አላማውም በፋይናንስ ተቋማት መካከል በዲጂ
ኩባንያው ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1.42 ቢሊዮን ብር አትርፌያለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








