top of page

ኤችአይቪን ለመከላከልና ለህክምና አገልግሎት በመንግስት ከሚሰሩ ስራዎች በተጨማሪ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ ብዙ ጫናዎችን እያቀለለ ነው ተባለ።

  • sheger1021fm
  • 11 minutes ago
  • 2 min read

ህዳር 18 2018


ኤችአይቪን ለመከላከልና ለህክምና አገልግሎት በመንግስት ከሚሰሩ ስራዎች በተጨማሪ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ ብዙ ጫናዎችን እያቀለለ ነው ተባለ።


በኢትዮጵያ ኤች አይቪን ጨምሮ የአባላዘር በሽታዎች ምርመራ፣ ህክምና እንዲሁም ሌሎች የጤና አገልግሎቶች ላይ ሲሰራ የቆየው ኤድስ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን (AHF) ኢትዮጵያ 10 ዓመት ማስቆጠሩን ተናግሯል።


ድርጅቱ የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት ሲያከብር እንደተናገረው ከ73,000 በላይ ኤችአይቪ በደማቸው ላለባቸው ኢትዮጵያውያን የጸረ ኤች አይ ቪ ህክምና እና ሌሎች ኤች አይ ቪን ተከትለው የሚመጡ ተጓዳኝ ህመሞች ህክምና እየሰጠ መሆኑን ተናግሯል።


ree

በተጨማሪም ድርጅቱ የዌልነስ ክሊኒክ በሙከራ ደረጃ ከፍቶ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመለየት የአባላዘር በሽታዎችን መመርመር፣ ቶሎ ማከም እና ሥርጭቱን መቀነስ ላይ እየሰራ መሆኑን የኤ ኤች ኤፍ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶ/ር መንግስቱ ገ/ሚካኤል ተናግረዋል።


በሙከራ ደረጃ በ2016 ዓ.ም በተከፈተው ከዚህ ክሊኒክ በተጨማሪ ሁለተኛ የሆነውን የዌልነስ ክሊኒክም ዛሬ አገልግሎት አስጀምሯል።


በክሊኒኩ በአሁኑ ሰዓት በወር 1,000 ለሚሆኑ ተገልጋዮች የኤች አይ ቪ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተነግሯል።


በተጨማሪም ከራሱ ክሊኒኮች ውጪ በሌሎች 18 የመንግስት የጤና ተቋማት የተለያዩ የላብራቶሪ ማሽኖች፣ የህክምና መድኃኒቶችን በመለገስ ነጻ አገልግሎት አየሰጡ መሆኑን ዶ/ር መንግስቱ ጠቅሰዋል።


በሌላ በኩል በየዓመቱ ከ1 ሚሊየን በላይ ኮንዶም በመግዛት ለቫይረሱ እጅግ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በነጻ እያደረስኩ ነው ብሏል ድርጅቱ።


የኤችአይቪ መከላከል እና ህክምና ላይ በመንግስት ከሚከወነው በተጨማሪ ድርጅቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የኤች አይ ቪ አባላዘር በሽታዎችና ቫይራል ሄፒታይተስ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ ፈቃዱ ያደታ ተናግረዋል።


ተገልጋዮች በገንዘብ ችግር ምክንያት የኤች አይ ቪ ህክናቸውን እንዳያቋርጡ ሙሉ ድጋፍ በማድረግ የኤች አይ ቪ ስርጭቱን መቆጣጠር ላይ ያለው ድጋፍም ቀላል አይደለም ብለዋል።


በተለይም ሌሎች አለም አቀፍ ድጋፎች መቀነስ ቢያጋጥምም ድርጅቱ አሁንም ያለምንም ማቋረጥ እያገለገለ በመሆኑም አቶ ፈቃዱ ምስጋና አቅርበዋል።


AHF በአለም አቀፍ ደረጃ በ50 ሀገራት ከ2.7 ሚሊየን ለሚበልጡ ሰዎች አገልግሎቱን በነፃ እየሰጠ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በኢትዮጵያ ከ73 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተገልጋዮች እንዳሉት ሰምተናል።


በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች ቁጥር በአጠቃላይ 600,000 ያህል መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page