top of page


በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ለማቅረብ መቸገራቸውን የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛው የስደተኞች ኮሚሽንና የሚመለከታቸው ተቋማት ተናገሩ፡፡
ታህሳስ 11/2018 በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ለማቅረብ መቸገራቸውን የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛው የስደተኞች ኮሚሽንና የሚመለከታቸው ተቋማት ተናገሩ፡፡ እጃችን ላይ ያለው የምግብ እርዳታ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ተሟጦ ያልቃል ያሉት ተቋማቱ አስቸኳይ ድጋፍ ካልተገኘ በስደተኞች መጠለያ ረሃብ መከሰቱ አይቀርም ብለዋል፡፡ በአለም አቀፉ ደረጃ የእርዳታ ሰጭዎች እጅ በማጠሩ ከ70 በመቶ በላይ ድጋፍ ተቋርጧል ያለው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ነው፡፡ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ስደተኞች እጄ ላይ የቀረው የምግብ እርዳታ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተሟጦ ያልቃልም ሲል አብረውት ከሚሰሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት ጋር በጋራ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡ በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን
Dec 20, 20252 min read
ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡
ታህሳስ 11/2018 ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም። ከመንግስት የሚቀርበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች የሚያከፋፍለውና ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በመንግስት የተቋቋመ ኮሚቴ በበኩሉ ምንም አይነት ድጋፍ እንደማይደረግላቸው እና ይጠብቁ እንደተባሉ ተናግሯል፡፡ ተፈናቃዮቹ ወደ ደብረ ብርሃን ከተመለሱ በኋላም ከዚህ ቀደም ስማቸው ተመልሰዋል በሚለው ስለተቀነሰ አሁን ከመንግስት በኩል የሚቀርብላቸው ድጋፍ የለም እንደተባሉ ያስረዳሉ፡፡ ተፈናቃዮቹ ቋሚ የሆነ ድጋፍ እንደሌላቸው በዚህም መቸገራቸውን ነግረውናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Dec 20, 20251 min read


ባህላዊና የዘመናዊ የአጥንት ህክምና
ታህሳስ 11/2018 ባህላዊ ህክምና በተለይ ደግሞ የአጥንት ህክምና አሁንም ብዙዎች ይመርጡታል። የዘመናዊ የአጥንት ህክምና አዋቂዎች ደግሞ በወጌሾች ላይ ቅሬታ ሲያቀርቡ ይሰማል። ታዲያ ምን ይሻላል? 80 በመቶ ያህል ኢትዮጵያዊ በተለይም በገጠር ነዋሪ የሆነው ህመም ሲገጥመው ከዘመናዊ ይልቅ ባህላዊውን የህክምና ስርዓት መራጭ እንደሆነ ይነገራል ይህም ለሁሉም ዓይነት ህመሞች ቢሆንም በተለይ ከአጥንት ህክምና ጋር በተገናኘ ግን የከተማ ነዋሪዎችም ከዘመናዊ ይልቅ እንደ ባህላዊ ወጌሻ ያሉ የአጥንት ህክምናዎችን ነው የሚመርጡት። የባህላዊ ህክምና ስራውን በእውቀትና በጥበብ የሚከውኑ ባለሙያዎች እንዳሉ ሁሉ ግን ከስነ ምግባርም ከውቀት ውጪ በመስራት ጉዳት የሚያገኛቸው ብዙ ሰዎች በመኖራቸው ከዘመናዊው ህክምና ጋር የሚቃረን ሀሳብ እየተፈጠረ መሆ
Dec 20, 20252 min read


''በተመደቡበት መስመር ላይ ረዥም ደቂቃ የሚቆሙ አሽከርካሪዎች የመቆጣጠሪያ ዘመናዊ መላ በመጠቀም ክትትል እያደረግሁ ነው'' የአዲስ አበባ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት
ታህሳስ 10/2018 የአዲስ አበባ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት በተመደቡበት መስመር ላይ ረዥም ደቂቃ የሚቆሙ አሽከርካሪዎችና የተመደቡበትን መስመር በአግባቡ ስለመሸፈናቸው ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ መላ በመጠቀም ክትትል እያደረግሁ ነው አለ። ድርጅቱ የአገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ አድርጓል የሚል ቅሬታ ቢቀርብም የከተማ አውቶብስ ተጠቃሚዎች አንዳንዴ የተራዘመ መስመር ሲጠቀሙ ከተቀመጠው ታሪፍ በተጨማሪ ይከፍላሉ እንጂ የዋጋ ጭማሪ ተደርጎ አይደለም ብሏል። የአዲስ አበባ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አዳዲስ በተመሠረቱ የመኖሪያ አካባቢዎች ላይ የሚያጋጥም የትራንስፖርት እጥረት ለማስተካከል የመጠበቂያ ሰዓቱን በማሳጠር የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዲደረስ ለማድረግ ጥረት እያደረግሁ ነው ብሏል። የአዲስ አበባ የከተማ አውቶብስ ተጠቃሚዎች አንዳንዴ አገልግሎቱ
Dec 20, 20251 min read


ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል የተባለለት የቤቶች ልማት ፖሊሲ እየተሰናዳ ነው፡፡
ታህሳስ 10/2018 ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል የተባለለት የቤቶች ልማት ፖሊሲ እየተሰናዳ ነው፡፡ ፖሊሲው ለቤት ግንባታ የሚሆን የመሬት፣ የፋይናንስ አቅርቦት እንዴት ይሁን የሚለውን ያካተተ እንደሚሆን ሰምተናል፡፡ ይህን ያለው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ነው። ፖሊሲው አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው ለማድረግ 8 አቅጣጫዎችን ለይቶ ያስቀመጠ እንደሆነም ተነግሯል። በተጨማሪም በመጭዎቹ 5 ዓመታት ሊገነባ የታቀደውን የ1.5 ሚሊየን ቤቶች ግንባታም እውን ለማድረግ ፖሊሲው አስቻይ ሁኔታን ይፈጥራልም ተብሎለታል። የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀጋዬ ሞሼ፤ የቤት ችግርን ለመፍታት የመሬት እና የፋይናንስ አቅርቦት ችግር
Dec 19, 20251 min read


ኢትስዊች ኢትዮ-ፔይ(EthioPay) ሲል የሰየመውን ብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ መለያ ይፋ አደረገ፡፡
ታህሳስ 10/2018 ኢትስዊች ኢትዮ-ፔይ(EthioPay) ሲል የሰየመውን ብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ መለያ ይፋ አደረገ፡፡ ኢትዮ-ፔይ ሁሉንም የኢትስዊች ተናባቢ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶች በአንድ ማንነት ስር የሚያሰባስብ እና በፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት በኩል ለደንበኞች ከፊት የሚታይ የብራንድ መለያ ነው ተብሏል። ኢትዮ-ፔይ በርካታ የክፍያ አገልግሎቶችን ለማቀፍ የተነደፈ ብራንድ መሆኑ ትናንት ይፋ በተደረገበት ስነስርዓት ላይ ተነግሯል፡፡ በዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ውስጥ ደህንነቱ በተጠበቀ እና በቅጽበት የዲጂታል ክፍያዎችንም ሆነ የገንዘብ ዝውውር የሚያንቀሳቅስ ብቸኛ የጋራ የዲጂታል መስመር ሆኖ የሚያገለግል ነው ተብሏል። በዋናነት ኢትዮ-ፔይ ገንዘብን በቅጽበት ማንቀሳቀስ ብቻ ሳይሆን የፋይናንስ እና ሌሎች ተቋማትን እንዲሁም ደ
Dec 19, 20251 min read


ታህሳስ 10/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
ታህሳስ 10/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ አሜሪካ በተጨማሪ ሁለት አለም አቀፉ የወንጀል ችሎት (ICC) ዳኞቹ ላይ ማዕቀወብ ጣለችባቸው፡፡ ዳኞቹ ለአሜሪካ ማዕቀብ የተዳረጉት ችሎቱ እስራኤል በጋዛ ዘመቻዋ ፈፅማዋለች የተባለውን የጦር ወንጀል መመርመሩን እንዲያቆም ያቀረበችውን መሟገቻ ውድቅ በማድጋቸው ምክንያት እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ ችሎቱ ቀደም ሲል በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና በቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም የተነሳ አሜሪካ በበርካታ የICC ዳኞች እና አቃቢያነ ህግ ላይ ማእቀብ እያከታተለችባቸው ነው፡፡ የአሜሪካ ጦር ባልደረቦች በአፍጋኒስታን አድርሰውታል የተባለን የጦር ወንጀል ለመመርመር የተነሱ የICC ባልደሮችም ለማዕቀብ መዳረጋቸው
Dec 19, 20252 min read


‘’ለእያንዳንዱ ስደተኛ መብት በጋራ እንቁም ፍልሰቱንም ለሁሉም ክብር ያለው እና ደህንነቱ የተጠበቀ እናድርግ’’ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
ታህሳስ 10/2018 ‘’ለእያንዳንዱ ስደተኛ መብት በጋራ እንቁም ፍልሰቱንም ለሁሉም ክብር ያለው እና ደህንነቱ የተጠበቀ እናድርግ’’ ሲሉ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናገሩ፡፡ ዋና ፀሀፊው የአለም አቀፉን የፍልሰት ቀን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመላው አለም ከ300 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀዬአቸው በመፈናቀል በሌሎች ሀገራት የሚገኙ ሲሆን የፍልሰተኞች ጉዳይ አለም አቀፍ ገፅታ ያለው እና በኢኮኖሚ አንፃር ብቻ የሚታይ አይደለም ሲሉ የንጋት ግሎባል ኢንሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል መለሰ ነግረውናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. የኔነህ ሲሳይ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://youtub
Dec 19, 20251 min read


ንብ ኢንተርናሸናል ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመርኩ 10 ዓመት ሞላኝ አለ።
ታህሳስ 10/2018 ንብ ኢንተርናሸናል ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመርኩ 10 ዓመት ሞላኝ አለ። ከ10 ዓመት በፊት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶች “ንብ ሃላል” በሚል ስያሜ በልዩ መስኮት መስጠት መጀመሩን እና በተለዩ ቅርንጫፎች አገልግሎቱን ሲሰጥ እንደቆየ ባንኩ ተናግሯል። ይህንን የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠትም ንብ ባንክ የሚፈለገውን የሸሪዓ ሕግ አማካሪ ኮሚቴ በማቋቋም የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን ሰምተናል። በዚህ ሰዓትም ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ 23 ቅርንጫፎች እንዳሉት አስረድቷል። በቀሩት ሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በልዩ መስኮት አገልግሎቱ እየቀረበ ነው ተብሏል። የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሔኖክ ከበደ በአዲስ መልክ የተዘጋጀውን ከወለድ ነፃ የ
Dec 19, 20251 min read


የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ (Subsidiary) የሆነው አዋሽ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ ስራ መጀመሩን ተናገረ።
ታህሳስ 9/2018 የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ (Subsidiary) የሆነው አዋሽ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ ስራ መጀመሩን ተናገረ። አዋሽ ካፒታል ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ህዳር 10 / 2018 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቀበሉን አስታውሷል፡፡ በዛሬው ዕለትም የማስጀመሪያ መርሃግብር በስካይላይት ሆቴል ተከናዉኗል፡፡ የማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ካፒታል የቦርድ ሰብሳቢ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው "ሀገራችን በፋይናንስ ዘርፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ ምዕራፍ በመግባት ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እያደረገች በምትገኝበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቋቋሙ ለቢዝነስ ዘርፉ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል" ብለዋል፡፡ አዋ
Dec 19, 20251 min read


የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዲጂታል መንገድ የሚሸጠው ሎተሪ ከፍ እያለ መምጣቱን ተናገረ፡፡
ታህሳስ 9/2018 የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዲጂታል መንገድ የሚሸጠው ሎተሪ ከፍ እያለ መምጣቱን ተናገረ፡፡ ለእዚህም አሁን በገበያ ላይ ያለው የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ዕጣ ተጠቃሽ ነው ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ1954 ለመጀመሪያ ጊዜ እድለኞችን መሸለም እንደጀመረ አስታውሷል፡፡ አገልግሎቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲጂታል ሎተሪ የጀመረው ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህም ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ ጎን ለጎን በዲጅታል፣ በሞባይል መተግበሪያዎች አማካኝነት የቀረበ ነው፡፡ ይህን የዲጂታል ሎተሪ ''ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ'' ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በጋራ የተሰራ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በገበያ ላይ ያለው እና በሃገሪቱ የሎተሪ ሽልማት ታሪክ ትልቁን ወይም 60 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ሎተሪ ገበያ ላይ
Dec 18, 20251 min read


አማራ ባንክና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ የሰነደ መዋለ ንዋይ ምዝገባን በተመለከተ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ታህሳስ 9/2018 አማራ ባንክና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ የሰነደ መዋለ ንዋይ ምዝገባን በተመለከተ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዩሐንስ አያሌው(ዶ/ር) እና የወጋገን ካፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩታዊት ዳዊት ናቸው፡፡ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ የአማራ ባንክ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ላይ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ ለማካሄድ የሚያስችለውን ረቂቅ ሰነድ (Draft Prospectus) ዝግጅቱ አጠናቅቆ ለባለስልጣኑ ማስረከቡ ተነግሯል፡፡ ሁለቱ ባንኮች ባደረጉት ስምምነት መሰረት አማራ ባንክ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በኩል ነባርም ሆነ አዳዲስ አክሲዮኖችን መሸጥ ቢፈልግ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ሰነድ ያዘጋጅል፣ ምክር ይሰጣ
Dec 18, 20252 min read


ግብርና ለኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት(GDP) ከፍ ያለ ድርሻ የሚያበረከት ሲሆን ለብዙዎችም የስራ ዕድል የፈጠረ ዘርፍ ነው።
ታህሳስ 9/2018 ግብርና ለኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት(GDP) ከፍ ያለ ድርሻ የሚያበረከት ሲሆን ለብዙዎችም የስራ ዕድል የፈጠረ ዘርፍ ነው። ለዚህ ዘርፍ እየቀረበ ያለው ብድር ግን ከአስር በመቶ በታች መሆኑ ተነግሯል። ግብርና ከኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት ከ32 በመቶ በላይ የሚሆነውን ድርሻ እንደሚሸፍን መረጃዎች ያሳያሉ። ከወጪ ንግድ ከሚገኘው ገቢም ከ80 በመቶ የሚልቀው ከዚሁ ዘርፍ የሚገኝ እንደሆነ ተነግሯል። ዘርፉ ከኢትዮጵያ ህዝብ ከ62 በመቶ ለሚልቀው የስራ ዕድል መፍጠሩም ይጠቀሳል። በአጠቃላይ ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲህ አይነት ጉልህ ድርሻ ላለው ለዚህ ዘርፍ እየቀረበ ያለው ብድር ግን ዝቅተኛ እንደሆነ፤ የኢትዮጵያ አበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ተናግረዋል።
Dec 18, 20252 min read


በአዲስ አበባ ከስራ ቦታ ደህንነትና ጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በዓመት ከ37 እስከ 75 ሰዎች እንደሚሞቱ ጥናት አሳየ።
ታህሳስ 9/2018 በአዲስ አበባ ከስራ ቦታ ደህንነትና ጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በዓመት ከ37 እስከ 75 ሰዎች እንደሚሞቱ ጥናት አሳየ። በከተማዋ ካሉ አምራች ኢንዱስትሪዎ ውስጥ 76 በመቶዎቹ ለሞት፣ ለጤና ችግርና የአካል ጉዳት አጋላጭ ናቸው ተብሏል። ይህ የተባለው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ከአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመሆን በሥራ ቦታ ደህንነትን ላይ አተኩረው ያደረጉትን ጥናት ባቀረቡበት መድረክ ላይ ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድኑ ተሳታፊ የሆኑት ካሱ ጂልቻ በአምራች ኢንዱስትሪዎችና የግንባታ ቦታዎች ያለው የድምፅ ብክለት፣ የሙቀት እና የብርሃን መጠን ከተቀመጠለት ገደብ ከሁለት እና ሶስት ዕጥፍ በላይ ነው ብለዋል። በዚህም ምክንያት በአምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ከሚሰሩ ሰራተኞች 41 በመቶዎቹ የመስማት ችግር አንዳጋጠማቸው፣
Dec 18, 20251 min read


ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን የሚያገናኝ የፈጣን መንገድ ግንባታ መጀመሯ ከዚህ ቀደም ተነግሯል፡፡
ታህሳስ 9/2018 ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን የሚያገናኝ የፈጣን መንገድ ግንባታ መጀመሯ ከዚህ ቀደም ተነግሯል፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ብትሆንም በዙሪያዋ ያሉ ወደ 10 ወደቦችን በኪራይ መጠቀሟ አይቀርም ተብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1 Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1 WhatsApp : https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O X : https://x.com/s
Dec 18, 20251 min read


በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚደረገው ለውጥ ህብረተሰቡን ያሳተፈ አይደለም የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው መሆኑ ተነገረ፡፡
ታህሳስ 9/2018 በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚደረገው ለውጥ ህብረተሰቡን ያሳተፈ አይደለም የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው መሆኑ ተነገረ፡፡ ይህ ሃሳብ የተነሳው ስለ ትምህርት እናውጋ ማህበር ባደረገው ውይይት ላይ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሥነ ትምህርት እና የቋንቋዎች ኮሌጅ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ካሣ ሚካኤል ስለትምህርት እናውጋ ማህበር በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የትምህርት ችግር በተመለከተ መመካከራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህ ማህበርተኞች በቅርቡ በብሪቲሽ ካውንስል በመገናኘት ባለፉት ጊዜያት የተወያዩባቸው ዋነኛ ጉዳዮችን የያዘ ሰነድ አሰናድተው ይፋ አድርገዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተማሪዎች የተማሪ ወላጆችና ሌሎችም አጋር አካላት አሉበት የተባለው ይህ ማህበር አሁን ስላለው የትምህርት ዘርፍ ችግር ጣት መጠቋቆም ለውጥ ሊያመ
Dec 18, 20251 min read


ምጣኔ ሐብት - ኢትዮዽያ የባቡር መሰረተ ልማት!
ታህሳስ 9/2018 ምጣኔ ሐብት - ኢትዮዽያ የባቡር መሰረተ ልማት! ኢትዮዽያ የባቡር መሰረተ ልማትን በአራቱም አቅጣጫ ገንብታ ወደ ኢኮኖሚው ብታስገባው የሚፈጥረው አቅም ቀላል የሚባል አይደለም። ቀድሞም ቢሆን በልዩ ልዩ ምክንያት የሚደነቀቃፈው የኢትዮዽያ የገቢና ወጭ ንግድ፤ አሁን ግን ወጥ በሆነ የሎጅስቲክስ አሰራር ለውጥ እየተቆጠረበት እንደሆነ ተሰምቷል። ከዚህ መአዘን ከገቢ እቃዎች መካከል፤ የኢትዮጵያን ግዙፍ ማሽነሪዎች፣ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ማዳበሪያ ዘይት ነዳጅ እና ሌላውንም የሚያጓጉዘው የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር የሎጅስቲክስ ስራውን እያቃለለ እንደሆነ ተናግሯል። በተለይ በባቡር መሰረተ ልማት ላይ የተንጠለጠለ የሎጅስቲክስ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ምድር ባቡሩ መንገድ መጀመሩ ተሰምቷል። ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ተህቦ
Dec 18, 20251 min read


የጋምቤላ ክልል“የመጣውን ሰላም እና ልማት ወደኋላ ለመመለስ እየሰሩ ያሉ እኩይ ሃይሎች” ያላቸው ወገኖች በየቦታው ህይወት እንዲጠፋ በማድረግ ጉዳት ማድረሳቸውን ተናገረ።
ታህሳስ 9/2018 የጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት “የመጣውን ሰላም እና ልማት ወደ ኋላ ለመመለስ እየሰሩ ያሉ እኩይ ሃይሎች” ያላቸው ወገኖች ሰሞኑን በየቦታው ሰዎች በመግደል፤ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት በማድረስ እና ህይወት እንዲጠፋ በማድረግ ጉዳት ማድረሳቸውን ተናገረ። የፀጥታ አካላትን እና አመራርን ኢላማ በማድረግ ክልሉን ወደ ለየለት የህዝቦች እልቂት ለማስገባት የተለያዩ ሙከራዎች ሲደረጉ መስተዋሉንም ክልሉ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። የፌዴራል እና የክልሉ የፀጥታ አካላት አሁን ላይ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሰፊ ስራ እየሰሩ እንደሆነ የጠቀሰው የክልሉ መንግስት መግለጫ በርካቶችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል፡፡ በበክልሉ ለፀጥታ ስራ ተመድበው ከሚሰሩ የሰራዊት አባላት ውጪ የትኛውንም የጦር መሳሪያ ይዞ በሚገኝ እና በሚንቀሳቀስ ቡ
Dec 18, 20251 min read


''በሎጅስቲክስ ዘርፍ ያለውን የባለሞያዎች ክፍተት ለመሙላትም ባለሞያዎችን በማሰልጠኑ እበረታለሁ'' የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር
ታህሳስ 8/2018 በገቢና በወጪ ንግድ፣ በጉምሩክ፣ በወደብ እና በመሰል ዘርፎች የባለሞያዎች እጥረት ስላለ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ስርዓታቸው አካትተው ሊሰሩበት ይገባል ተብሏል፡፡ በሎጅስቲክስ ዘርፍ ያለውን ይህንን የባለሞያዎች ክፍተት ለመሙላትም ባለሞያዎችን በማሰልጠኑ እበረታለሁ ሲል የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ በተለይም በዘርፉ ሴቶች በበቂ እንዲሰማሩ እየተሰራ ነው የተባለ ሲሆን፤ በዲግሪ ተመርቀው በየክልሉ ስራ ሌላቸው ሴቶች ተመልምለው ወደዚህ ዘርፍ የሚያስገባቸውን ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡ በክልሎች በኩል ተመልምለው በአዲስ አበባ በዲፕሎማ ደረጃ ሲሰለጥኑ የቆዩ 94 ሴቶችም በትናንትናው ዕለት ተመርቀዋል፡፡ በምረቃ መርሀግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር
Dec 17, 20251 min read


በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል የተባለ ፖሊሲ እየተረቀቀ እንደሚገኝ ተነገረ
ታህሳስ 8/2018 ህገ ወጥ ኬላዎችን እና የኮቴ ክፍያን ጨምሮ በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል የተባለ ፖሊሲ እየተረቀቀ እንደሚገኝ ተነገረ ረቂቅ ፖሊሲው እየተሰናዳ ያለው በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እንዲሁም በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እንደሆነ ሰምተናል። ሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ለእዚሁ የመንገድና ትራንስፖርት ረቂቅ ፖሊሲ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ትናንት አካሂደዋል። የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ፖሊሲው ቀጠናዊ ትስስር እውን እንዲሆን እንዲያግዝ፣ ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች መጠቀምን እንዲያበረታታ እና በመንገድና በትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ችግር እንዲፈታ ሆኖ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው መንገ
Dec 17, 20251 min read


የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከሶስት ዓመት በፊት በጀመረው ከማስያዣ ነፃ በሆነው "ምቹ ብድር አገልግሎት" 40 ቢሊዮን ብር ማበደሩን ተናገረ፡፡
ታህሳስ 8/2018 የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከሶስት ዓመት በፊት በጀመረው ከማስያዣ ነፃ በሆነው "ምቹ ብድር አገልግሎት" 40 ቢሊዮን ብር ማበደሩን ተናገረ፡፡ ምቹ ዲጂታል ብድር ከተጀመረ 3 ዓመት ከ3 ወር አንደሆነው ባንኩ ለሸገር በላከው መግለጫ ጠቅሷል፡፡ 40 ቢሊዮን ብር ብድሩ ከ2.44 ሚሊዮን በላይ በሆኑ ሂሳቦች የተሰጠ መሆኑንም ሰምተናል፡፡ ከዚህም ውስጥ 80 በመቶ ተበዳሪዎች ሴቶችን ናቸው ተብሏል፡፡ ብድሩ በጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ሥራ ዘርፍ ለተሰማራው ማህበረሰብ አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ ዋስትና ሆኗል ሲል ብንኩ አስረድቷል፡፡ ምቹ ለብድር ማስያዣ በሚሆን ንብረት እጦት፣ ከፋይናንስ አገልግሎት ተገልለው የቆዩትን የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ዘርፍ የደረሰና ለስኬታቸው ዋቢ እየሆነ ያለ ፈጣን ብድር መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል። እን
Dec 17, 20252 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








