ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡
- sheger1021fm
- 3 minutes ago
- 1 min read
ታህሳስ 11/2018
ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡
የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም።
ከመንግስት የሚቀርበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች የሚያከፋፍለውና ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በመንግስት የተቋቋመ ኮሚቴ በበኩሉ ምንም አይነት ድጋፍ እንደማይደረግላቸው እና ይጠብቁ እንደተባሉ ተናግሯል፡፡
ተፈናቃዮቹ ወደ ደብረ ብርሃን ከተመለሱ በኋላም ከዚህ ቀደም ስማቸው ተመልሰዋል በሚለው ስለተቀነሰ አሁን ከመንግስት በኩል የሚቀርብላቸው ድጋፍ የለም እንደተባሉ ያስረዳሉ፡፡
ተፈናቃዮቹ ቋሚ የሆነ ድጋፍ እንደሌላቸው በዚህም መቸገራቸውን ነግረውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1








