top of page

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዲጂታል መንገድ የሚሸጠው ሎተሪ ከፍ እያለ መምጣቱን ተናገረ፡፡

  • Dec 18, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 9/2018


የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዲጂታል መንገድ የሚሸጠው ሎተሪ ከፍ እያለ መምጣቱን ተናገረ፡፡


ለእዚህም አሁን በገበያ ላይ ያለው የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ዕጣ ተጠቃሽ ነው ብሏል፡፡


የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ1954 ለመጀመሪያ ጊዜ እድለኞችን መሸለም እንደጀመረ አስታውሷል፡፡


አገልግሎቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲጂታል ሎተሪ የጀመረው ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡


ይህም ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ ጎን ለጎን በዲጅታል፣ በሞባይል መተግበሪያዎች አማካኝነት የቀረበ ነው፡፡


ይህን የዲጂታል ሎተሪ ''ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ'' ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በጋራ የተሰራ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በገበያ ላይ ያለው እና በሃገሪቱ የሎተሪ ሽልማት ታሪክ ትልቁን ወይም 60 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ሎተሪ ገበያ ላይ የቀረበው በዲጂታል ብቻ መሆኑን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተናግሯል፡፡


ከአሁን በፊት በወረቀት ከሚታወቁት ሎተሪዎች በተጨማሪ አዳዲስ የሎተሪ አይነቶችን በመጨመር ለገበያ እያቀረበ መሆኑን አገልጎሎቱ ጠቅሷል፡፡


ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በዲጂታል መንገድ ብቻ ለገበያ የቀረበው የቀረበውን የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ዕጣ ሊወጣ 30 ቀናት እንደቀሩትም ተነግሯል፡፡


የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ከጠቅላላ ሽያጭ ላይ ከ125 ሚሊዮን ብር በላይ ወይንም ከግማሽ በላይ ትኬቶች ለዕድለኞች ሽልማት የሚውሉ ሲሆን ከአጠቃላይ ሽያጩ ለሽልማት የሚወጣው የገንዘብ መጠን ወደ 53 በመቶ ደርሷል ተብሏል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page