top of page

''በሎጅስቲክስ ዘርፍ ያለውን የባለሞያዎች ክፍተት ለመሙላትም ባለሞያዎችን በማሰልጠኑ እበረታለሁ'' የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

  • sheger1021fm
  • 14 minutes ago
  • 1 min read

ታህሳስ 8/2018

 

በገቢና በወጪ ንግድ፣ በጉምሩክ፣ በወደብ እና በመሰል ዘርፎች የባለሞያዎች እጥረት ስላለ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ስርዓታቸው አካትተው  ሊሰሩበት ይገባል ተብሏል፡፡

 

በሎጅስቲክስ ዘርፍ ያለውን ይህንን የባለሞያዎች ክፍተት ለመሙላትም ባለሞያዎችን በማሰልጠኑ እበረታለሁ ሲል የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

 

ree

በተለይም በዘርፉ ሴቶች በበቂ እንዲሰማሩ እየተሰራ ነው የተባለ ሲሆን፤ በዲግሪ ተመርቀው በየክልሉ ስራ ሌላቸው ሴቶች ተመልምለው ወደዚህ ዘርፍ የሚያስገባቸውን ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡


በክልሎች በኩል ተመልምለው በአዲስ አበባ በዲፕሎማ ደረጃ ሲሰለጥኑ የቆዩ 94 ሴቶችም በትናንትናው ዕለት ተመርቀዋል፡፡

 

ree

በምረቃ መርሀግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ተመራቂዎቹን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

 

ሴት ተመራቂዎቹን በማሰልጠን እንደ አንድ ባለድርሻ እየሰራ የነበረው የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋ በሎጀስቲክስ ዘርፍ የባለሙያዎች እጥረት መኖሩን ተቅሰው ከሚሰጡት አጫጨር ስልጠናዎች በተጨማሪ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትምህርት ስርዓታቸው ዉስጥ አካትተው ባለሞያችን በማፍራቱ ሊሰሩበት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 

ከየክልሉ ተመልምለው በዲፕሎማ የተመረቁት ሴቶች ምን ምን ላይ ነው የሰለጠኑት ስንል የጠየቅናቸው፤ በኢትየጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የኢትዮጵያ ትሬድ ሎጅስቲክስ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ደሳለኝ ጌታሁን ሰልጣኞቹ፣ በገቢና በወጪ ንግድ፣ በጉምሩክ፣ በወደብ እና በመሰል ዘርፎች እንደሰለጠኑ ነግረውናል፡፡

 

ree

አሁን ላይ በዘርፉ የተሰማሩት ባለሞያች የወንዶች ቁጥር ክፍ ያለ በመሆኑና ሴቶችም ወደ ዘርፉ ለማስገባት በአሁን ዙር ሴቶች ብቻ ተመርጠው እንዲሰለጥኑ መደረጉንም አንስተዋል አቶ ደሳለኝ፡፡

 

በሎጀስቲክስ ዘንድ የሚሰለጥኑ ተመራቂዎች ወደ ስልጠና ሲገቡ ቢያንስ 40 ከመቶዎቹ ወዲያው ስራ እንዲያገኙ የማድረግ ስምምነት ከባለድርሻ አካላት እንደሚደረግ እና ከትናንት ተመራቂዎችም በዚሁ ስምምነት መሰረት ስራ ያገኙ እንዳሉ ተነግሯል፡፡

 

የተቀሩትም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ባጠረ ጊዜ ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል መባሉንም ሰምተናል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page