top of page

በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ለማቅረብ መቸገራቸውን የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛው የስደተኞች ኮሚሽንና የሚመለከታቸው ተቋማት ተናገሩ፡፡

  • sheger1021fm
  • 20 minutes ago
  • 2 min read

ታህሳስ 11/2018

 

በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ለማቅረብ መቸገራቸውን የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛው የስደተኞች ኮሚሽንና የሚመለከታቸው ተቋማት ተናገሩ፡፡

 

እጃችን ላይ ያለው የምግብ እርዳታ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ተሟጦ ያልቃል ያሉት ተቋማቱ አስቸኳይ ድጋፍ ካልተገኘ በስደተኞች መጠለያ ረሃብ መከሰቱ አይቀርም ብለዋል፡፡

 

በአለም አቀፉ ደረጃ የእርዳታ ሰጭዎች እጅ በማጠሩ ከ70 በመቶ በላይ ድጋፍ ተቋርጧል ያለው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ነው፡፡

 

ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ስደተኞች እጄ ላይ የቀረው የምግብ እርዳታ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተሟጦ ያልቃልም ሲል አብረውት ከሚሰሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት ጋር በጋራ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡

 

በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን ያለው ግጭት እንዲሁም በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ስደተኞችን ቁጥር ጨምሮታል ያለው አገልግሎት ሰጭ መስሪያ ቤቱ በዛ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው የእርዳታ እጥረት ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል ብሏል፡፡

 

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ከተባበሩት መንግስታት ከፍተኛው የስደተኞች ኮሚሽን(UNHCR) ፣ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ፣ እና ከአለም የምግብ ድርጅት(WFP) በጋራ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ለስደተኞች እየተሰጠ ያለውን እርዳታ ለማቆም እየተገደድን ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡


ree

 

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞችን በማስጠለል ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ሀገር ነች፡፡

 

ከጎሮቤት ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሶማሊያና ኤርትራ የመጡ ስደተኞችም ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ይነገራል፡፡

 

ቁጥራቸውም ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ሲሆን አለም አቀፉ እርዳታ በእጅጉ በመቀዛቀዙ ለስደተኞች ምግብ የማቅረቡ ጉዳይ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መድረሱን ተቋማቱ በመግለጫቸው አክለዋል፡፡

 

በዚህም ምክንያት ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ የአለም የምግብ ድርጅት ለ780,000 ስደተኞች ያቀርብ የነበረውን የምግብ እርዳታ 40 በመቶ ለማቋረጥ ተገዷል ተብሏል፡፡

 

ምግብ በጠፋ ቁጥር ስደተኞች ራሳቸውን ለማኖር ሌሎች አማራጮችን እንዲወስዱም ይገደዳሉ በሚል ተቋማቱ አደስጠንቅቆዋል፡፡

 

የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ስደተኛ የጠተለለበት ሲሆን ከዚህ ቀደም በክልሉ ስደተኞች ባጋጠማቸው የምግብ እጥረት ከካምፕ ወጥተው ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል፡፡

 

ስደተኞቹን ለመጭው ስድስት ወር ለመመገብና ለማኖር 90 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን እርዳታው ካልተገኘ ስደተኞቹ ላይ ረሃብና የምግብ እጥረት ሊከሰት ይችላልም የሚል ስጋትም በመግለጫው ሰፍሯል፡፡

 

ree

እስካሁን ባጋጠመው የእርዳታ እጥረትም የምግብ እጥረት ማጋጠም መጀመሩም ተጠቅሷል፡፡

 

በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈረንጆቹ አመት አዲስ በሚወለዱ እና ከ1 ዓመት በታች በሆኑ ህፃነት የሞት ምጣኔው በ4.7 በመቶ መጨመሩም ተነግሯል፡፡

 

በካምፕ ያሉ ስደተኞች ራሳቸውን ለማቆየት የቀራቸውን ነብረት መሸጥ ፣ የምግብ ሰዓት መዝለልና ልጆቻቸውን ከትምህርት አስቀርተው ለስራ መላክ እንዲሁም ያለ እድሜ ጋብቻ እየወሰዷቸው ያሉ አማራጮች ናቸው ተብሏል፡፡

 

ከምግብ እጥረቱ ባሻገር የውሃ እጥረትና የትምህርት አገልግሎት መስተጓጎልም በኢትዮጵያ የተጠለሉ ሚሊዮን ስደተኞቹ እየገጠማቸው ያለ ፈተና ነው ተብሏል፡፡

 

በመሆኑም የከፋው ከመምጣቱ በፊት ለስደተኞቹ የሚሆን እርዳታ እንዲደረግ  ተቋማቱ  ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ በመግለጫው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

ትዕግስት ዘሪሁን

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Recent Posts

See All
ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ 

ታህሳስ 11/2018   ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡   የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም።   ከመንግስት የሚቀርበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች የሚያከፋፍለውና ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በመንግስት የተቋቋመ ኮሚ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page