የጋምቤላ ክልል“የመጣውን ሰላም እና ልማት ወደኋላ ለመመለስ እየሰሩ ያሉ እኩይ ሃይሎች” ያላቸው ወገኖች በየቦታው ህይወት እንዲጠፋ በማድረግ ጉዳት ማድረሳቸውን ተናገረ።
- sheger1021fm
- 5 hours ago
- 1 min read
ታህሳስ 9/2018
የጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት “የመጣውን ሰላም እና ልማት ወደ ኋላ ለመመለስ እየሰሩ ያሉ እኩይ ሃይሎች” ያላቸው ወገኖች ሰሞኑን በየቦታው ሰዎች በመግደል፤ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት በማድረስ እና ህይወት እንዲጠፋ በማድረግ ጉዳት ማድረሳቸውን ተናገረ።
የፀጥታ አካላትን እና አመራርን ኢላማ በማድረግ ክልሉን ወደ ለየለት የህዝቦች እልቂት ለማስገባት የተለያዩ ሙከራዎች ሲደረጉ መስተዋሉንም ክልሉ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል።
የፌዴራል እና የክልሉ የፀጥታ አካላት አሁን ላይ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሰፊ ስራ እየሰሩ እንደሆነ የጠቀሰው የክልሉ መንግስት መግለጫ በርካቶችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል፡፡
በበክልሉ ለፀጥታ ስራ ተመድበው ከሚሰሩ የሰራዊት አባላት ውጪ የትኛውንም የጦር መሳሪያ ይዞ በሚገኝ እና በሚንቀሳቀስ ቡድን ላይ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስዱም አሳስቧል።
በተከሰተው የጸጥታ ችግር የሰው ህይወትና መጥፋቱን የጠቀሰው መግለጫው ለዚህም ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል ብሏል።
ስለሞቱ ሰዎች ብዛት ግን ያለው ነገር የለም፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1








