top of page

ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል የተባለለት የቤቶች ልማት ፖሊሲ እየተሰናዳ ነው፡፡

  • sheger1021fm
  • 4 minutes ago
  • 1 min read

ታህሳስ 10/2018

 

ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል የተባለለት የቤቶች ልማት ፖሊሲ እየተሰናዳ ነው፡፡

 

ፖሊሲው ለቤት ግንባታ የሚሆን የመሬት፣ የፋይናንስ አቅርቦት እንዴት ይሁን የሚለውን ያካተተ እንደሚሆን ሰምተናል፡፡

 

ይህን ያለው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ነው።

 

ፖሊሲው አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው ለማድረግ 8 አቅጣጫዎችን ለይቶ ያስቀመጠ እንደሆነም ተነግሯል።

 

በተጨማሪም በመጭዎቹ 5 ዓመታት ሊገነባ የታቀደውን የ1.5 ሚሊየን ቤቶች ግንባታም እውን ለማድረግ ፖሊሲው አስቻይ ሁኔታን ይፈጥራልም ተብሎለታል።

ree

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀጋዬ ሞሼ፤ የቤት ችግርን ለመፍታት የመሬት እና የፋይናንስ አቅርቦት ችግር መፍታት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ መሰረተ ልማትን ማሟላት የሚሉ እና  ሌሎች በፖሊሲው ተለይተው ተቀምጠዋል፤ እነሱ ላይም ይሰራል ብለዋል።

 

የግል ቤት አልሚዎች ከዚህ ቀደም ሲያነሷቸው የነበሩ እንደ አሳሪ የሕግ ማዕቀፎች እና የአሰራር ስርዓቶች ያሉ ችግሮች እየተፈቱ ነው ያሉት አቶ ጸጋዬ ነገር ግን አሁንም በዘርፉ ያሉ ችግሮች እንዳሉ ሃላፊው ጠቅሰዋል።

 

በዘርፉ ያሉ ቤት አልሚዎች የሚያነሷቸውን ችግሮች በተመለከተ እየተሰናዳ ነው ባሉት የቤት ልማት ፖሊሲ ችግሮቹ እንደሚፈታም ያምናሉ።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

ፍቅሩ አምባቸው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page