top of page

የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከሶስት ዓመት በፊት በጀመረው ከማስያዣ ነፃ በሆነው "ምቹ ብድር አገልግሎት" 40 ቢሊዮን ብር ማበደሩን ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • 12 minutes ago
  • 2 min read

ታህሳስ 8/2018


የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከሶስት ዓመት በፊት በጀመረው ከማስያዣ ነፃ በሆነው "ምቹ ብድር አገልግሎት" 40 ቢሊዮን ብር ማበደሩን ተናገረ፡፡


ምቹ ዲጂታል ብድር ከተጀመረ 3 ዓመት ከ3 ወር አንደሆነው ባንኩ ለሸገር በላከው መግለጫ ጠቅሷል፡፡


40 ቢሊዮን ብር ብድሩ ከ2.44 ሚሊዮን በላይ በሆኑ ሂሳቦች የተሰጠ መሆኑንም ሰምተናል፡፡


ከዚህም ውስጥ 80 በመቶ ተበዳሪዎች ሴቶችን ናቸው ተብሏል፡፡


ብድሩ በጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ሥራ ዘርፍ ለተሰማራው ማህበረሰብ አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ ዋስትና ሆኗል ሲል ብንኩ አስረድቷል፡፡

ree

ምቹ ለብድር ማስያዣ በሚሆን ንብረት እጦት፣ ከፋይናንስ አገልግሎት ተገልለው የቆዩትን የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ዘርፍ የደረሰና ለስኬታቸው ዋቢ እየሆነ ያለ ፈጣን ብድር መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል።


እንደ ተበዳሪው የአከፋፈል ሁኔታ መልካም የአከፋፈል ልምድ ላላቸው፣ ዲጂታል የምዘና ስርዓቱ የብድር መጠናቸውን እያሳደገ የሚሄድ ነው፡፡


ለዕለት ወይም መደበኛ ላልሆኑ ንግዶች በምቹ ጉያ ለ1 ሳምንት የሚቆይ ከብር 2‚000-15000፤ ፈቃድ ላላቸው የንግድ ሥራዎች በምቹ ዋቢ ለ1 ወር የሚቆይ ከብር 50‚000-100‚000 ብር ፤ ወይም እንደ ተበዳሪው ፍላጎት እስከ ብር 300,000 ብር በተሻሻለ የመመለሻ ጊዜ ይሰጣል ሲል መግለጫው ያስረዳል።


ለሴቶች በሚሰጠው ምቹ ኪያ መደበኛ ላልሆኑ ንግዶች ለ2 ሳምንት የሚቆይ ከብር 3000-5000፣ ፈቃድ ላላቸው የንግድ ሥራዎች ለ1 ወር የሚቆይ ከብር 10000-30000 ብድር ይሰጣል ተብሏል።


ምቹ ከክፍያ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር በኤ.አይ ምዘና በተገኘ የፋይናንስ መረጃ ላይ መሰረት በማድረግ፣ ያለ ማስያዣ የሚሰጥ ነው።


ባንኩ፣ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደው የ2025 ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ፎረም ዘላቂ የፋይናንስ አገልግሎት የሚሰጥ የዓመቱ ምርጥ የፋይናንስ አቅራቢ በመባል እውቅና እና ሽልማት ማግኘቱንም በላከልን መግለጫ ላይ ጠቅሷል።


በሀገር አቀፍ ደረጃም ‘ምርጥ የፋይናንስ ተቋም’ በመባል እውቅና እና ሽልመት ማግኘቱም ተጠቅሷል።


የዲጂታል ያለ ማስያዣ ብድር አቅርቦቱን ሁሉንም ማህበረሰብ ክፍል ለማድረስ የሸሪዓን መርሆዎች በጠበቀ መልኩ በከወለድ ነጻ የቀረበው ምቹ በሙከራ ላይ ነው ተብሏል።


የአርሶ አደሮች ምቹ ብድር መጀመሩን ሰምተናል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page