top of page

ንብ ኢንተርናሸናል ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመርኩ 10 ዓመት ሞላኝ አለ።

  • Dec 19, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 10/2018


ንብ ኢንተርናሸናል ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመርኩ 10 ዓመት ሞላኝ አለ።


ከ10 ዓመት በፊት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶች “ንብ ሃላል” በሚል ስያሜ በልዩ መስኮት መስጠት መጀመሩን እና በተለዩ ቅርንጫፎች አገልግሎቱን ሲሰጥ እንደቆየ ባንኩ ተናግሯል።


ይህንን የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠትም ንብ ባንክ የሚፈለገውን የሸሪዓ ሕግ አማካሪ ኮሚቴ በማቋቋም የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን ሰምተናል።

በዚህ ሰዓትም ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ 23 ቅርንጫፎች እንዳሉት አስረድቷል።


በቀሩት ሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በልዩ መስኮት አገልግሎቱ እየቀረበ ነው ተብሏል።


የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሔኖክ ከበደ በአዲስ መልክ የተዘጋጀውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የንግድ ምልክት ይፋ አድርገዋል።


ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ወደ ባንክ ቢዝነሱ ከገባ 26 ዓመት አልፎታል።


በኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የባንክ ሥርዓት በማንኛውም ባንክ በመደበኛ ባንኮች ውስጥ በመስኮት፤ በመደበኛ ባንኮች በቅርንጫፍ ደረጃ፤ የመደበኛ ባንኮች እህት ኩባንያ በመሆን ወይም ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ ሆኖ ሊቋቋም የሚችልበት አማራጮች አሉት።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page