የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ (Subsidiary) የሆነው አዋሽ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ ስራ መጀመሩን ተናገረ።
- sheger1021fm
- Dec 19, 2025
- 1 min read
ታህሳስ 9/2018
የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ (Subsidiary) የሆነው አዋሽ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ ስራ መጀመሩን ተናገረ።
አዋሽ ካፒታል ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ህዳር 10 / 2018 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቀበሉን አስታውሷል፡፡
በዛሬው ዕለትም የማስጀመሪያ መርሃግብር በስካይላይት ሆቴል ተከናዉኗል፡፡

የማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ካፒታል የቦርድ ሰብሳቢ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው "ሀገራችን በፋይናንስ ዘርፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ ምዕራፍ በመግባት ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እያደረገች በምትገኝበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቋቋሙ ለቢዝነስ ዘርፉ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል" ብለዋል፡፡
አዋሽ ካፒታል በ200,000,000 ብር ካፒታል ስራ መጀመሩ ተነግሯል።
አዋሽ ካፒታል የተለያዩ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎቶችን ማለትም በድርጅት ፋይናንስ እና የማማከር አገልግሎት፤ በዋስትና ንግድ እና የማገናኘት ስራ፤ በምርምር እና የገበያ ኢንተሊጀንስ፤ በአረንጓዴ ፋይናንስ የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ ዋና ስራ አስፈጻሚው አንዱአለም ኃይሉ(ዶ/ር) በማስጀመሪያ ሥነሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1












Comments