አማራ ባንክና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ የሰነደ መዋለ ንዋይ ምዝገባን በተመለከተ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
- sheger1021fm
- 10 hours ago
- 2 min read
ታህሳስ 9/2018
አማራ ባንክና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ የሰነደ መዋለ ንዋይ ምዝገባን በተመለከተ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዩሐንስ አያሌው(ዶ/ር) እና የወጋገን ካፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩታዊት ዳዊት ናቸው፡፡
ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ የአማራ ባንክ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ላይ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ ለማካሄድ የሚያስችለውን ረቂቅ ሰነድ (Draft Prospectus) ዝግጅቱ አጠናቅቆ ለባለስልጣኑ ማስረከቡ ተነግሯል፡፡
ሁለቱ ባንኮች ባደረጉት ስምምነት መሰረት አማራ ባንክ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በኩል ነባርም ሆነ አዳዲስ አክሲዮኖችን መሸጥ ቢፈልግ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ሰነድ ያዘጋጅል፣ ምክር ይሰጣል፡፡

የአማራ ባንክ ባለአክሲዮኖችም በተመሳሳይ ያለቸውን ድርሻ መሸጥ ወይም የሚገዛ ድርሻ ሲኖር መግዛት ቢፈልጉ ከእንግዲህ ብኋላ ሼሮች መሸጥ የሚቻለው በካፒታል ገበያ በኩል ስለሆነ ዋጋ መተመንን፣ ምክር መስጠትን ጨምሮ የተላያዩ ስራዎችን ወጋገን ካፒታል ይሰራል ተብሏል፡፡
ከ164,000 በላይ ባለአክሲዮኖችን ያሉት አማራ ባንክ በካፒታል ገበያ ውስጥ የባንኩን አክሲዮኖችን እንዲሸጥ ለማስችል፣ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ለማቋቋም፣ ተጨማሪ ካፒታል ማሰባሰብ የመሳሰሉ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል የዛሬው ስምምነት ወስኝ እርምጃ ነው ሲሉ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዩሐንስ አያሌው(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱ፤ አማራ ባንክን ከቀዳሚ የፋይናንስ ተቋማት አንዱ ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ ላይ ጤናማ አስተዳደርንና የገበያ ዲሲፕሊን መርሆዎችን ለማክበር ያለውን ትጋት የሚያሳይበት ነው ሲሉ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ አስረድተዋል።
አማራ ባንክ ወደፊት በካፒታል ገበያ ውስጥ ለሚኖረው ሚናና ተሳትፎ ከወጋገን ካፒታል ላይ ለጣለው ኃላፊነትና እምነት ወጋገን ካፒታልን ያመሰገኑት ያመሰገኑት ዶ/ር ዮሐንስ ኢንቨስትመንት ባንኩ የተጣለበትን ኃላፊነት እንደሚወጣ እምነታችን ነው ብለዋል፡፡
ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት፤ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች ወይንም ሌሎች ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ላይ መመዝገብ ቢፈልጉ፣ ድርሻውን መሸጥና ሀብት መጨመር ካሰቡ ሰነድ ማዘጋጀት አንዲሁም የምክር አገልግሎት ይሰጣል።
እንዲሁም የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች አውጭና ገዢ የማገናኘት፣ በውክልና የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት ማመቻቸት፤ እንዲሁም በተፈቀደለት ሌሎች ተዛማጅ የካፒታል ገበያ ዘርፎች ዋንኛ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች አከናዋኝ በመሆን ይሰራል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1












Comments