top of page

ኢትስዊች ኢትዮ-ፔይ(EthioPay) ሲል የሰየመውን ብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ መለያ  ይፋ አደረገ፡፡ 

  • sheger1021fm
  • 8 hours ago
  • 1 min read

ታህሳስ 10/2018

 

ኢትስዊች ኢትዮ-ፔይ(EthioPay) ሲል የሰየመውን ብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ መለያ  ይፋ አደረገ፡፡

 

ኢትዮ-ፔይ ሁሉንም የኢትስዊች ተናባቢ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶች በአንድ ማንነት ስር የሚያሰባስብ እና በፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት በኩል ለደንበኞች ከፊት የሚታይ የብራንድ መለያ ነው ተብሏል።

 

ኢትዮ-ፔይ በርካታ የክፍያ አገልግሎቶችን ለማቀፍ የተነደፈ ብራንድ መሆኑ ትናንት ይፋ በተደረገበት ስነስርዓት ላይ ተነግሯል፡፡

 

ree

በዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ውስጥ ደህንነቱ በተጠበቀ እና በቅጽበት የዲጂታል ክፍያዎችንም ሆነ የገንዘብ ዝውውር የሚያንቀሳቅስ ብቸኛ የጋራ የዲጂታል መስመር  ሆኖ የሚያገለግል ነው ተብሏል።

 

በዋናነት ኢትዮ-ፔይ ገንዘብን በቅጽበት ማንቀሳቀስ ብቻ ሳይሆን የፋይናንስ እና ሌሎች ተቋማትን እንዲሁም ደንበኞችን በአንድ ብራንድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ተብሎለታል፡፡


 ለፋይናንስ ተቋማት ኢትዮ-ፔይ የጋራ የዲጂታል መሰረተ ልማት  ላይ ተናባቢ፣ ዘርፈ ብዙ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የሚያደርግ መለያ (Brand) ነው፡፡

ree

ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት  ክፍያ መቀበልን የሚያቀልል፣ መተማመንን የሚገነባ ፤ለአገልግሎት ተጠቃሚው የየትኛውንም የፋይናንስ ተቋም አገልግሎት እንዲጠቀሙ የሚያስችል አንድ መለያ  ነው ሲሉ የኢትስዊች የቦርድ ሰብሳቢው አቶ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል።

 

አቶ ሰለሞን ሁሉም የፋይናንስ ተቋማት የኢትዮ-ፔይ  መለያን በፍጥነት በአገልግሎት መዳረሻዎቻቸው  ውስጥ እንዲያካትቱ እና ከደንበኞቻቸው  ጋር በሚኖራችው የግብይት እንቅስቃሴ ውስጥም ግንባር ቀደም አድርገው እንዲተገብሩት አሳስበዋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..

ንጋቱ ሙሉ

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page