top of page

በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚደረገው ለውጥ ህብረተሰቡን ያሳተፈ አይደለም የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው መሆኑ ተነገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • 3 hours ago
  • 1 min read

ታህሳስ 9/2018

 

በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚደረገው ለውጥ ህብረተሰቡን ያሳተፈ አይደለም የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው መሆኑ ተነገረ፡፡

 

ይህ ሃሳብ የተነሳው ስለ ትምህርት እናውጋ ማህበር ባደረገው ውይይት ላይ ነው፡፡

 

በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሥነ ትምህርት እና የቋንቋዎች ኮሌጅ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ካሣ ሚካኤል ስለትምህርት እናውጋ ማህበር በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የትምህርት ችግር በተመለከተ መመካከራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

 

እነዚህ ማህበርተኞች በቅርቡ በብሪቲሽ ካውንስል በመገናኘት ባለፉት ጊዜያት የተወያዩባቸው ዋነኛ ጉዳዮችን የያዘ ሰነድ አሰናድተው ይፋ አድርገዋል፡፡

 

የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተማሪዎች የተማሪ ወላጆችና ሌሎችም አጋር አካላት አሉበት የተባለው ይህ ማህበር አሁን ስላለው የትምህርት ዘርፍ ችግር ጣት መጠቋቆም ለውጥ ሊያመጣ ስለማይችል ለችግሮቹ መፍትሄ ለማመልከት እና የራሱን ሀላፊነት ለመወጣት በማሰብ ምክክሮቹን እንደሚያደርግ ሰምተናል፡፡

 

ካሣ ሚካኤል(ዶ/ር) እንደሚሉት ትምህርት ወድቋል ብሎ መናገር ለውጥ አያመጣም መፍትሄው በመተጋገዝ ከወደቀበት ማንሳት ነው ይላሉ፡፡

 

የተዘጋጀው ሰነድ ለውይይት መነሻ ሀሳብ ይሆናል በማለት የተሰናዳ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

 

ነገር ግን በትምህርት ዘርፍ ለተጋረጡ ችግሮች ዋነኛ መፍትሄ ይሆናል በሚል የተዘጋጀ አለመሆኑን አብራርተዋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

 

በረከት አካሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page