top of page

በአዲስ አበባ ከስራ ቦታ ደህንነትና ጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በዓመት ከ37 እስከ 75 ሰዎች እንደሚሞቱ ጥናት አሳየ።

  • sheger1021fm
  • 1 hour ago
  • 1 min read

ታህሳስ 9/2018


በአዲስ አበባ ከስራ ቦታ ደህንነትና ጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በዓመት ከ37 እስከ 75 ሰዎች እንደሚሞቱ ጥናት አሳየ።


በከተማዋ ካሉ አምራች ኢንዱስትሪዎ ውስጥ 76 በመቶዎቹ ለሞት፣ ለጤና ችግርና የአካል ጉዳት አጋላጭ ናቸው ተብሏል።


ይህ የተባለው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ከአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመሆን በሥራ ቦታ ደህንነትን ላይ አተኩረው ያደረጉትን ጥናት ባቀረቡበት መድረክ ላይ ነው።


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድኑ ተሳታፊ የሆኑት ካሱ ጂልቻ በአምራች ኢንዱስትሪዎችና የግንባታ ቦታዎች ያለው የድምፅ ብክለት፣ የሙቀት እና የብርሃን መጠን ከተቀመጠለት ገደብ ከሁለት እና ሶስት ዕጥፍ በላይ ነው ብለዋል።

ree

በዚህም ምክንያት በአምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ከሚሰሩ ሰራተኞች 41 በመቶዎቹ የመስማት ችግር አንዳጋጠማቸው፣ 34 በመቶዎቹ ደግሞ የመተንፈሻ አካላት የጤና ጉዳት እንዳለባቸው የጥናቱ ሪፖርት አሳይቷል ተብሏል።


እንደ ባንክ እና ቴሌኮም ባሉ የአግልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ ከሚሰሩ ሰራተኞች ደግሞ፤ ከስራ ቦታ የአቀማመጥ እና እንቅስቃሴ አለመመቻቸት የተነሳ 69 በመቶዎቹ የመገጣጠሚያና የወገብ ህመም እንዳለባቸው ተነግሯል።


60 በመቶዎቹ ደግሞ የጭንቀትና ድባቴ ስነልቦናዊ ችግር አንዳጋጠማቸው ተጠቅሷል።


ጥናቱ በከተማዋ ባሉ ከ500 በላይ የኢንዱስትሪ እና የአግልግሎት ሰጪ ተቋማትና ከ1,500 በላይ ሰራተኞች ላይ ግብዓት ተሰብስቦ የተሰራ መሆኑን ሰምተናል።


ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page