top of page


ደረጃቸውን ያልጠበቁ የኤሌክትሪክ መኪኖች ለገበያ እየቀረቡ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ
ህዳር 15 2018 መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ወደ ሀገር እንዳይገቡ መከልከሉን ተከትሎ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥራቸው በርክቷል፡፡ በሌላ በኩል ግን ደረጃቸውን ያልጠበቁ የኤሌክትሪክ መኪኖች ለገበያ እየቀረቡ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በበኩሉ ከጉምሩክ ፍተሻ አምልጠው የሚገቡ ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቅሶ እናስተካክላለን የሚል ምላሽ ሰጥቶናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ንጋት መኮንን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡..
Nov 241 min read


ኢትዮጵያዊያን ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት ለስራ ከሄዱ በኋላ ለሚያጋጥሟቸው የጤና እክሎች ተከታትሎ መፍትሄ የሚሰጥ አሰራር የለም ተባለ፡፡
ህዳር 15 2018 ኢትዮጵያዊያን ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት ለስራ ከሄዱ በኋላ ለሚያጋጥሟቸው የጤና እክሎች ተከታትሎ መፍትሄ የሚሰጥ አሰራር የለም ተባለ፡፡ ይንን ችግርም ለመፍታ ይረዳል የተባለ እና የሀገር ውስጥ እና የአለም አቀፍ ተቋማት በጋራ የሚሰሩበት ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን ሰምተናል። ፕሮጀክቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ እና ሌሎችም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ይሳተፉበታል ተብሏል። ከዚህ ቀደም ሴቶች ለቤት ሰራተኝነት ወደ አረብ ሀገራት ሲሄዱ አንዴ ብቻ ተመርምረው እንደሚሄዱ እና በስራ ወቅት የጤና ችግር ቢገጥማቸው እንኳን ቋሚ ክትትል የሚያደርግ አሰራር እንዳልነበረ ሲነገር ሰምተናል፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያውያኑ ለተለያ የጤና ቀ
Nov 241 min read


ከ200,000 ለሚልቁ ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ መስክ
ህዳር 15 2018 ከፍተኛ ሊባል የሚችል ቁጥር ያላቸው ሴቶች በኢትዮጵያ የአበባ እርሻ ልማት የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል። የዘርፉ ስኬቶች ከሚባሉ ጉዳዮች አንዱም ይኸው የስራ ዕድል ፈጠራ ነው። እንዲያም ሆኖ የሚሰሙ አንዳንድ ቅሬታዎች አሉ ። ለተመሳሳይ ስራ እኩል ክፍያ ያለማግኘት መብት አለመከበር እና የኬሚካል አጠቃቀም ችግር ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ የአበባ እርሻ ልማት ከተጀመረ ሃያ ዓመታት አልፈዋል። በእነዚህ ጊዜያት ዘርፉ ቀላል የማይባል ዕድገት ማሳየቱን መንግስት እና በስራው የተሰማሩ ባለሃብቶች ይናገራሉ። ልማቱ ሲጀመር ከ28.5 ሚሊየን ዶላር የማይበልጠው የዘርፉ የአመት ገቢ አሁን ላይ ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ መሆኑ እንደ ማሳያ ይቀርባል። ከ200,000 ለሚልቁ ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ መስክ መሆኑም እንዲሁ ይነሳል።
Nov 242 min read


ኢትዮጵያ የአርብቶ አደሮችን ድንበር ተሻጋሪ ችግሮች ለመፍታት ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተባብራ እንደምትሰራ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ(ዶ/ር) ተናገሩ።
ህዳር 13 2018 ኢትዮጵያ የአርብቶ አደሮችን ድንበር ተሻጋሪ ችግሮች ለመፍታት ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተባብራ እንደምትሰራ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ(ዶ/ር) ተናገሩ። በአካባቢው ሀገራት የሚገኙ አርብቶ አደሮች ወቅቶችን በመከተል ከቤት እንስሳቶቻቸው ጋር ድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታው አስታውሰዋል። በዚህ እንቅስቃሴያቸውም ከግጦሽ መሬት እና ውሃ ጋር የተገናኙ ችግሮች ይገጥሟቸዋል ብለዋል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ኢትዮጵያ ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተቀራርባ እንደምትሰራ ተናግረዋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD) ትኩረቱን በአካባቢው ሀገራት በሚገኙ አርብቶ አደሮች ላይ ያደረገ ውይይት እዚህ በአዲስ አበባ አካሂዷል። በውይይቱም በአካባቢው አርብቶ አደሮች መካከል ኢኮ
Nov 221 min read


አሐዱ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ተናገረ።
ህዳር 13 2018 አሐዱ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ተናገረ። ባንኩ በበጀት ዓመቱ በበዙ የባንክ ስኬት መለኪያዎች ይበል የሚያስብል ውጤት ማስመዝገቡን በዛሬው ዕለት ባካሄደው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናግሯል። ይህ ውጤት የተመዘገበውም በበዙ ችግሮች ውስጥ አልፎ መሆኑንም ጠቅሷል። የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ በበጀት ዓመቱ 7.88 ቢሊዮን ብር ደርሷል፤ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ41 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል። በሂሳብ ዓመቱ ከ88.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰቡንም #አሐዱ_ባንክ ጠቅሷል። ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ10.3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከ2.16 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ ከቀ
Nov 221 min read


የተለያዩ እና ብዙም ያልተለመዱ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዤ መጥቻለሁ ሲል ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ተናገረ።
ህዳር 12 2018 የተለያዩ እና ብዙም ያልተለመዱ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዤ መጥቻለሁ ሲል ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ተናገረ። ማህበሩ በዛሬ ዕለትም በይፋ ስራ መጀመሩን በሰጠው መግለጫ አስረድቷል። ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ለሚዲያ እና ኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተለይ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበት አማራጭ መያዙንም አስረድቷል። የህብረት ስራ ማህበሩ በሴት የቦርድ አባላት የሚመራና በዘርፉ የረጅም ዓመት ልምድ ባካበቱ ባለሞያዎች የተቋቋመ መሆኑም አስረድቷል። በዘርፉ አሁን ላይ እየተተገበሩ ከሚገኙ የብድር አገልግሎቶች በተለየ መልኩ አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ መምጣቱን በመጠቆም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚነትን ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑም ተጠቅሷል። በቡድን የሚመጡ ብድር ፈላጊዎች ልዩ የወለድ ቅ
Nov 211 min read


ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በኢትዮጵያ በሚከሰቱ ሞቶች ከግማሽ በላይ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑንን ጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
ህዳር 12 2018 ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በኢትዮጵያ በሚከሰቱ ሞቶች ከግማሽ በላይ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑንን ጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ የኩላሊት ህመተኞችን በተመለከተ የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች መጀመራቸውን ሰምተናል፡፡ እየጨመሩ ካሉ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች መካከል የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት፣ ስትሮክ፣ ኩላሊት፣ የልብና የደም ስር መዘጋት እንዲሁም የአዕምሮ መታወክና ካንሰር ከብዙ በጥቂቶቹ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ተናግሯል፡፡ በተለይም የደም ግፊት ከፍተኛ ለሆነ የኩላሊት በሽታ እያጋለጠ እንደሆነና በዚህም 6 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ስር ለሰደደ የኩላሊት ህመም አንደሚጋለጡ በጥናት መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ነግረውናል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያሉት ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምን ለ
Nov 211 min read


በየጊዜው የሚለዋወጡ ህጎች የኢንቨስትመንት መስኩ ተገማች እንዳይሆን ማድረጉን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተናገረ።
ህዳር 12 2018 በየጊዜው የሚለዋወጡ ህጎች የኢንቨስትመንት መስኩ ተገማች እንዳይሆን ማድረጉን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተናገረ። የፀጥታ ችግርም እንቅፋት እንደሆነበት ኮሚሽኑ ለህዝብ እንደራሴዎች ተናግሯል፡፡ ኪሚሽኑ ይህን የተናገረው የሶስት ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ትናንት ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ባቀረበበት ወቅት ነው። የኢንቨስትመንት ኮሚሽንን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዳገቶ ኩምቢ ባለፉት 3 ወራት 400 ሚሊዮን ዶላር በተኪ ምርት ወይንም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት ታቅዶ መፈጸም የተቻለው ግን 211 ሚሊዮን ዶላር ወይንም የእቅዱን 53 በመቶ እንደሆነ አስረድተዋል። 19 የሚሆኑ ድርጅ
Nov 212 min read


ለኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት 32 በመቶ ያሚያበረክተው ግብርና
ህዳር 12 2018 ለኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት 32 በመቶ ያሚያበረክተው ግብርና፤ አሁንም በአብዛኛው በበሬ ከማረስ አልተላቀቀም፡፡ ዛሬም የሀገሬው #ገበሬ ከራሱ አልፎ ሌሎችን መመገብ ፈተና ሲሆንበት ይታያል። ለመሆኑ ለሃገር ውስጥ የምርት አቅርቦትም ይሁን የግብርና ወጪ ንግዱን ገቢ ለማሳደግ እንዴት መሰራት አለበት ስንል የዘርፉን ባለሞያ ጠይቀናል፡፡ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢኮኖሚክስ ምርምር ዳይሬክተር እና ተመራማሪው ታደለ ማሞ(ዶ/ረወ) ገበሬው ችግር የሆነበትንና የተሻለ የምርት አቅርቦት እንዲኖር ቢሰራበት ያሉትን ነግረውናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTub
Nov 211 min read


በኢትዮጵያ ያሉት ከተሞች መልሰው መልማት አለባቸው ይባላል፤ ግን እንዴት ?
ህዳር 12 2018 በኢትዮጵያ ያሉት ከተሞች ስማቸው ነው እንጂ ከተማ በብዙ መስፈርቶች ከተሞች አለመሆናቸውን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ከተሞቹ መልሰው መልማት አለባቸው ይባላል፡፡ ግን እንዴት ? ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ያሬድ እንዳሻው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2
Nov 211 min read


ለመጪውን የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንዲሁም የገና በዓል ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሚሄዱ የውጪ ዜጎች አውደርዕይ መሰናዳቱ ተነገረ
ህዳር 12 2018 መጪውን የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንዲሁም የገና በዓል አስመልክቶ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሚሄዱ የውጪ ሃገር ዜጎች በተለይም ለዲኘሎማቲክ ማህበረሰቡ አውደርዕይ መሰናዳቱ ተነገረ፡፡ ኢትዮጵያን ለዓለም ሀገራት ለማስተዋቅ የተለያዩ ለስጦታ የሚሆኑ ምርቶች ይገኙበታል የተባለው አውደርዕይ የተሰናዳው በሦስት ድርጅቶች ነው ተብሏል፡፡ ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኤቨንት፣ ዲሊኦፖል ሆቴል፣ እና ሳራ ኔክስት ፋሽን ዲዛይን በጋራ አውደርዕዩን ማሰናዳታቸው ተነግሯል፡፡ የፈረንጆቹ የገና በዓል የተለያዩ ስጦታዎች የሚሰጡበት በመሆኑ ይህንን እድል በመጠቀም ምርቶች እንዲተዋወቁ አውደ ርዕዩ መሰናዳቱን የሳራ ኔክስት ፋሽን ዲዛይን መስራች ሳራ መሀመድ ተናግረዋል፡፡ በአውደ ርዕዩ በተለያዩ ምርቶች ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች እንደሚሳተፉ እና ልምድ የሚ
Nov 211 min read


‘’በሩብ ዓመቱ ከቀረቡልኝ ቅሬታዎች የሚበዙት፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው’’
ህዳር 12 2018 ህዝብ የሚበድሉ አንዳንድ የመንግስት እና የግል ተቋማት የምሰጣቸውን የእርምት ሀሳብ ባለመቀበል እያስቸገሩኝ ነው ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ። ተቋማቱ አስተዳደራዊ በደል መፈፀማቸውን ያምናሉ፤ ግን ለማስተካከል ፍቃደኛ እየሆኑ አይደለም ተብሏል። በተቋሙ የህግና አስተዳደር በደል ምርመራ መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መንግስቱ ቀኜ አስተዳደራዊ በደል ፈፅመው እንዲያስተካክሉ የነገርናቸው አንድ አንድ ተቋማት፣ የመፍትሔ ሃሳቡን መቀበላቸው በጥፋተኝነት ያስጠይቀናል የሚል ፍራቻ አላቸው ብለውናል፡፡ አንድ አንድ ተቋማት ደግሞ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ምንም አይነት ህጋዊ ዕርምጃ መውሰድ አይችልም የሚል የተሳሳተ ግምት እንዳላቸው ኃላፊው ነግረውናል። የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በሩብ ዓመቱ ከቀረቡለት አቤቱ
Nov 211 min read


ኢትዮ ቴሌኮም እና አዋሽ ባንክ ደንበኞቻቸውን ዋስትና ሳይጠይቁ በቴሌብር የዲጂታል ፋይናንስ እና የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎቶችን ማስጀመራቸውን ተናገሩ።
ህዳር 12 2018 ኢትዮ ቴሌኮም እና አዋሽ ባንክ ደንበኞቻቸውን ዋስትና ሳይጠይቁ በቴሌብር የዲጂታል ፋይናንስ እና የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎቶችን ማስጀመራቸውን ተናገሩ። ይህ በአይነቱ ለየት ያለ ነው የተባለለት የፋይናንስ አገልግሎት “ጥላ“ እንደሚባል ሰምተናል። ይህ "ጥላ" የተባለው አነስተኛ ያለዋስትና የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት፣ በገጠርም ሆነ በከተማ ያሉ ደንበኞች ፤ አገልግሎቱን እንዲያገኙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ታግዞ የተመቻቸ ነው ተብሏል። ለብድር አገልግሎቶቹ በዓመት በጠቅላለው ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የብድር አቅርቦት ስምምነት መደረጉንም ሰምተናል። ከተጀመሩት የዲጅታል ፋይናንሲንግ አገልግሎቶች መካከልም፤ የቁጠባ እገልግሎት፤ የግለሰብ ደንበኛ ብድር አገልግሎት፤ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ወይም ነጋዴዎች ፤ ለዲቫይስ
Nov 211 min read


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በባንኩ ከሚፈፀመው የገንዘብ ልውውጥ ውስጥ 90 በመቶው የሚላወሰው በዲጂታል መንገድ ነው አለ።
ህዳር 11 2018 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ጊዜ በባንኩ ከሚፈፀመው የገንዘብ ልውውጥ ወይም ግብይት ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው የሚላወሰው በዲጂታል መንገድ ነው አለ። ይህም ከቀዳማዊ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ17 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል። የባንኩ አብዛኛው ግብይት በዲጂታል መንገድ በመሆኑ ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቱ በዚያው ልክ ከፍ እያለ መምጣቱ ይታወቃል ሲሉ የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ሲናገሩ ሰምተናል። አቶ ኤፍሬም ይህንን ያሉት ባንኩ የሳይበር ደህንነት ወርን በማስመልከት ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ነው። በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት በዲጂታል መንገድ ከተገላበጠው 17.7 ትሪሊዮን ብር ውስጥ 13 ትሪሊዮን ብር ወይም 73 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑንም አቶ ኤፍሬም አስረድተዋል። የባንኩ
Nov 201 min read


በወላጆቻቸው መታሰር ምክንያት ወደ ማረሚያ ቤት መግባት ግድ የሚሆንባቸው ህፃናት እንዴት ይሆን የሚስተናገዱት?
ህዳር 11 2018 ያለ ጥፋታቸው፤ በወላጆቻቸው መታሰር ምክንያት ወደ ማረሚያ ቤት መግባት ግድ የሚሆንባቸው ህፃናት በዚያ ሲገኙ እንዴት ይሆን የሚስተናገዱት? እነርሱን ማዕከል ያደረገ አገልግሎትስ ያገኙ ይሆን? ስንል ጠይቀናል፡፡ ስለ ጉዳዩ የጠየቅነው ማረሚያ ቤቶችን የሚያስተዳድረው የፌድራሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምን አለ? የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚው አቶ ገረመው አያሌው፤ እስካሁን የእነዚህን ህፃናት መብትና ጥቅም የሚያጠብቅ የህግ ማዕቀፍ የለም ብለውናል፡፡ ወደ ማረሚያ ቤቶች የሚገቡ ልጆች ከእናቶቻቸው ጋር ነው የሚገቡት፤ እስካሁን ባለው አሰራር ለህፃናቱ ተብሎ የሚመደብ በጀት ባለመኖሩ ህፃናቱ ከቀለብ ጀምሮ ሌሎችንም ማግኘት የነበረባቸውን ጥቅም እንዳያገኙ ሆኗል ብለዋል፡፡ ይህንንም በመረዳት የእነርሱን ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችል የህግ
Nov 202 min read


ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ
ህዳር 11 2018 ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የሚከለክል መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጀ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ማንኛውም ተማሪዎች ከተፈጥሮ ጸጉራቸው በስተቀር አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል አይችሉም ተብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ በዓላት በተለይም እንደ ክሬዚ ዴይ፣ ኦልድ ዴይ፣ ቤቢ ዴይ፣ ቶማቶ ዴይ፣ ከለር ዴይ፣ ቫላንታይን ዴይ እና ሌሎችም የበዓል ቀናቶች ተብለው የሚከበሩ በዓላት ማክበር በመመሪያው ተከልክሏል፡፡ በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በተገቢ መንገድ መልሰብ ሲል ባወጣው መመሪያ ስር ሴቶች ጉርድ ቀሚስ
Nov 203 min read


ለኢትዮጵያ ሁለተኛ የሆነው የዓይን ባንክ በጅማ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ፡፡
ህዳር 11 2018 ለኢትዮጵያ ሁለተኛ የሆነው የዓይን ባንክ በጅማ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ፡፡ የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ እንደተናገረው በአዲስ አበባ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ውስጥ ካለው የአይን ባንክ በተጨማሪ ለረጅም ጊዜ ተይዞ በነበረ ዕቅድ በክልል ከተማ የዓይን ብሌን የሚሰበሰብበት ባንክ ተከፍቷል ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሀብታሙ ታዬ እንደነገሩን ጅማ ላይ ተጨማሪ የዓይን ባንክ ለመክፈት የተጀመሩት ስራዎች ተጠናቀው ባንኩ ስራ እንዲጀምር ተደርጓል ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ በአይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት ከበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች ድጋፍ የሚፈልጉ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን የሚናገሩት አቶ ሀብታሙ ካለው ፍላጎት አንጻር ሁለት የአይን ባንክ አሁንም በቂ አይደለም ይላሉ፤ የፍላ
Nov 202 min read


በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የተሻለ የስራ ዕድል ቢፈጠርም አሁንም ብዙ ቀሪ ስራዎች አሉ ተባለ።
ህዳር 11 2018 በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የተሻለ የስራ ዕድል ቢፈጠርም አሁንም ብዙ ቀሪ ስራዎች አሉ ተባለ። ዘርፉ ለ200,000 ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠሩ የተነገረ ሲሆን 80 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸው ተጠቅሷል። መዋዕለ ነዋይ በማፍሰስ ወደ ዘርፉ ልማት መግባት ለሚፈልጉ ሴቶች ግን አሁንም ሁኔታዎች ብዙም ምቹ አለመሆናቸው ተነግሩዋል፡፡ የመሬትና የብድር አቅርቦት በዘርፉ መሠማራት የሚፈልጉ ሴቶችን ይገጥማሉ ከተባሉ ችግሮች መካከል ናቸው። ዘርፉ ላይ በአመራር ደረጃ ያሉ ሴቶች ቁጥርም ዝቅተኛ ነው። የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማህበር ትኩረቱን በሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያደረገ ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው። ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ በያመቱ እንደምታገ
Nov 201 min read


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ከሀገር ከወጡ ከመቶ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ቅርሶች ተቀበለ
ህዳር 11 2018 ከሀገር ከወጡ ከመቶ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ቅርሶች፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ተቀበለ። ቅርሶቹ 12 ሲሆኑ በአንድ ቤተሰብ አባላት ተጠብቀው የቆዩ መሆናቸውን ሰምተናል። ከቅርሶቹ መካከል ፎቶግራፎች፣ ጋሻ፣ ዘውድ፣ ዝናር፣ ጎራዴ እና ሌሎች ይገኙበታል። ቅርሶቹ ከ1913 እስከ 1921 ዓ.ም በወቅቱ በነበሩት ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ እና ከአልጋወራሽ ተፈሪ መኮንን በኢትዮጵያ የጀርመን መልዕክተኛ ለነበሩት ቪስ ትሪዝ በስጦታ መልክ የተበረከተላቸው እንደሆኑም ሰምተናል። ቅርሶቹን በአሁኑ ሰዓት በስዊዲን ሀገር የሚኖሩት የመልዕክተኛው የልጅ ልጅ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም በዛሬው ዕለት በራስ መኮንን አዳራሽ በተከናወነ ሥርዓት አስረክበዋል። ቅርሶቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለ
Nov 201 min read


''ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመለሽ ተሽከርካሪዎችን እቀጣለሁ'' የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ
ህዳር 10 2018 የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመለሽ ተሽከርካሪዎችን እቀጣለሁ አለ። ቢሮው ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች በከተማዋ እየበዙ ነው ያለ ሲሆን ከዚህ በኋላ በመመሪያው መሰረት ረዳት የሌላቸውን ታክሲዎች እቀጣለሁ ብሏል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ክትትልና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ታመነ ያለ ረዳት ማሽከርከር ገንዘብ በመቀበል፣ገቢና ወራጅ በመቆጣጠር የሹፌሩን ትኩረት ስለሚሰርቅ ለአደጋ ያጋልጣል ብለውናል። ኃላፊው ከዚህ ቀደም ለሌሎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ብቻ ትኩረት በመስጠታችን ረዳት ያላቸውና የሌላቸውን ተሽከርካሬዎች የመለየት ውስንነት ታይቶብናል ብለዋል። ከዚህ በኋላ ግን የታክሲ ረዳት መኖር አንዱ የትራፊክ ደህንነት አካ
Nov 191 min read


ላለፉት 6 ዓመታት በጉምሩክ ተይዘውብኝ የነበሩት ኮምፒውተሮች ተለቀውልኛል ሲል ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት ተናገረ፡፡
ህዳር 10 2018 ላለፉት 6 ዓመታት በጉምሩክ ተይዘውብኝ የነበሩት ኮምፒውተሮች ተለቀውልኛል ሲል ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት ተናገረ፡፡ ይህ የሆነው ጉዳዩን ወደ ሚዲያ ካመጣሁት በኋላ ነውም ብሏል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ህፃናት ለማሰልጠን ሊውል የነበረና በልገሳ ከውጭ ሃገር ያስገባሁት ኮምፒውተር በጉምሩክ ተይዞ 6 ዓመት ሆነው ሲል የህፃናት መርጃ ድርጅቱ ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ከድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ ወ/ሮ ሰሎሜ ኩምሳ እንደሰማነው መረጃው በሚዲያ በተሰራጨ ማግስት ከድርጅቱ የክብር አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር ጋር በመሆን ድርጅቱ ለጉምሩክ ኮሚሽን ኮምፒውተሮቹ እንዲመለሱለት ያቀረበው ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አግኝቶ፤ 107 ኮምፒውተሮች፣ እንደ ኪቦርድ፣ ጊታር፣ ድራም ያሉ የሙዚቃ መሳሪያዎችን፣ የል
Nov 192 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








