የተለያዩ እና ብዙም ያልተለመዱ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዤ መጥቻለሁ ሲል ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ተናገረ።
- sheger1021fm
- 14 minutes ago
- 1 min read
ህዳር 12 2018
የተለያዩ እና ብዙም ያልተለመዱ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዤ መጥቻለሁ ሲል ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ተናገረ።
ማህበሩ በዛሬ ዕለትም በይፋ ስራ መጀመሩን በሰጠው መግለጫ አስረድቷል።
ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ለሚዲያ እና ኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተለይ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበት አማራጭ መያዙንም አስረድቷል።
የህብረት ስራ ማህበሩ በሴት የቦርድ አባላት የሚመራና በዘርፉ የረጅም ዓመት ልምድ ባካበቱ ባለሞያዎች የተቋቋመ መሆኑም አስረድቷል።
በዘርፉ አሁን ላይ እየተተገበሩ ከሚገኙ የብድር አገልግሎቶች በተለየ መልኩ አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ መምጣቱን በመጠቆም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚነትን ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑም ተጠቅሷል።
በቡድን የሚመጡ ብድር ፈላጊዎች ልዩ የወለድ ቅናሽ እንዲያገኙ የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እንደሚያደርግ፣ወላጆች ተማሪ ልጆቻቸው የት/ቤት ክፍያ ብድር እንዲያገኙ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጋር በተገናኘ የሚያስፈልጋቸውን ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን ጠቁሟል።

ለህክምና፣ የውጪ ጉዞዎች የሚሆን ብድር ማህበሩ በልዩነት ይዟቸው ከመጡ ብድሮች መካከል መሆናቸውም ተነግሯል።
ከወለድ ነፃ ብድር በማመቻቸት የተቀላጠፈ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁም ብሏል።
የሚዲያ እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከሚሰሯቸው ስራዎች ጋር በተገናኘ የፋይናንስ ችግር ለስራቸው እንቅፋት እንዳይሆን ልዩ የብድር አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ማህበሩ ጠቅሷል።
ይህንንም ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ስምምነት የኪነ ጥበብና የሚዲያ ባለሙያዎች ከኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








