top of page

ኢትዮ ቴሌኮም እና አዋሽ ባንክ ደንበኞቻቸውን ዋስትና ሳይጠይቁ በቴሌብር የዲጂታል ፋይናንስ እና የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎቶችን ማስጀመራቸውን ተናገሩ።

  • Nov 21, 2025
  • 1 min read

ህዳር 12 2018


ኢትዮ ቴሌኮም እና አዋሽ ባንክ ደንበኞቻቸውን ዋስትና ሳይጠይቁ በቴሌብር የዲጂታል ፋይናንስ እና የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎቶችን ማስጀመራቸውን ተናገሩ።


ይህ በአይነቱ ለየት ያለ ነው የተባለለት የፋይናንስ አገልግሎት “ጥላ“ እንደሚባል ሰምተናል።


ይህ "ጥላ" የተባለው አነስተኛ ያለዋስትና የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት፣ በገጠርም ሆነ በከተማ ያሉ ደንበኞች ፤ አገልግሎቱን እንዲያገኙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ታግዞ የተመቻቸ ነው ተብሏል።

ለብድር አገልግሎቶቹ በዓመት በጠቅላለው ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የብድር አቅርቦት ስምምነት መደረጉንም ሰምተናል።


ከተጀመሩት የዲጅታል ፋይናንሲንግ አገልግሎቶች መካከልም፤ የቁጠባ እገልግሎት፤ የግለሰብ ደንበኛ ብድር አገልግሎት፤ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ወይም ነጋዴዎች ፤ ለዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት መስጠት ይገኙበታል ተብሏል።

በተጨማሪም ደንበኞች ቴሌብርን ብቻ ተጠቅመው ከአዋሽ ባንክ ኤቲኤም በቀላሉ ገንዘብ ማውጣት የሚችሉበት አገልግሎት መጀመሩንም ሰምተናል።


ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም ከ57 ሚሊዮን በላይ ከበልጡት የቴሌ ብር ደንበኞቹ መካከል ፤ ለ15 ሚሊየን ደንበኞች ፤ ከ31.6 ቢሊዮን ብር በላይ የዲጂታል ብድር አገልግሎት ያለዋስትና መስጠቱን አስረድቷል።


ኩባንያው ይህን የብድር አገልግሎት የሰጠው ከአራት ባንኮች ጋር በመሆን ነው።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page