ኢትዮጵያዊያን ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት ለስራ ከሄዱ በኋላ ለሚያጋጥሟቸው የጤና እክሎች ተከታትሎ መፍትሄ የሚሰጥ አሰራር የለም ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- 5 minutes ago
- 1 min read
ህዳር 15 2018
ኢትዮጵያዊያን ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት ለስራ ከሄዱ በኋላ ለሚያጋጥሟቸው የጤና እክሎች ተከታትሎ መፍትሄ የሚሰጥ አሰራር የለም ተባለ፡፡
ይንን ችግርም ለመፍታ ይረዳል የተባለ እና የሀገር ውስጥ እና የአለም አቀፍ ተቋማት በጋራ የሚሰሩበት ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን ሰምተናል።
ፕሮጀክቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ እና ሌሎችም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ይሳተፉበታል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም ሴቶች ለቤት ሰራተኝነት ወደ አረብ ሀገራት ሲሄዱ አንዴ ብቻ ተመርምረው እንደሚሄዱ እና በስራ ወቅት የጤና ችግር ቢገጥማቸው እንኳን ቋሚ ክትትል የሚያደርግ አሰራር እንዳልነበረ ሲነገር ሰምተናል፡፡
በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያውያኑ ለተለያ የጤና ቀውሶች ማለትም የአእምሮ ጤና መቃወክን ጨምሮ ሌሎች ችግሮችን እንደሚያተናግዱ ተመልክተናል ሲሉ የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ ዶክተር ካሳሁን ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡
ይህንን እና ሌሎች ችግሮችን ይፈታል የተባለም ኢኖቬት የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








