በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የተሻለ የስራ ዕድል ቢፈጠርም አሁንም ብዙ ቀሪ ስራዎች አሉ ተባለ።
- sheger1021fm
- 10 hours ago
- 1 min read
ህዳር 11 2018
በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የተሻለ የስራ ዕድል ቢፈጠርም አሁንም ብዙ ቀሪ ስራዎች አሉ ተባለ።
ዘርፉ ለ200,000 ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠሩ የተነገረ ሲሆን 80 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።
መዋዕለ ነዋይ በማፍሰስ ወደ ዘርፉ ልማት መግባት ለሚፈልጉ ሴቶች ግን አሁንም ሁኔታዎች ብዙም ምቹ አለመሆናቸው ተነግሩዋል፡፡
የመሬትና የብድር አቅርቦት በዘርፉ መሠማራት የሚፈልጉ ሴቶችን ይገጥማሉ ከተባሉ ችግሮች መካከል ናቸው።
ዘርፉ ላይ በአመራር ደረጃ ያሉ ሴቶች ቁጥርም ዝቅተኛ ነው።

የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማህበር ትኩረቱን በሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያደረገ ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ በያመቱ እንደምታገኝ በኮንፈረንሱ ላይ ሲነገር ሠምተናል።
ከሀያ ዓመት በፊት ግን ከዘርፉ ታገኝ የነበረው ገቢ 28.5 ሚሊዮን ዶላር ነው ተብሏል።
ከግብርና ንዑስ ዘርፎች አንዱ የሆነው አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ለኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ በማስገኘት አራተኛ ደረጃ የሚገኝ መሆኑ ተጠቅሷል።
ግብርና በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ህዝቡ ከ70 በመቶ በላይ ለሚሆኑት ቀጥተኛ የስራ ዕድል የፈጠረ መስክ መሆኑ ተነግሯል።
ከእነዚህ መካከል ደግሞ 53 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው ተብሏል።
ንጋቱ ረጋሳ












Comments