top of page

ለመጪውን የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንዲሁም የገና በዓል ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሚሄዱ የውጪ ዜጎች አውደርዕይ መሰናዳቱ ተነገረ

  • Nov 21, 2025
  • 1 min read

ህዳር 12 2018

 

መጪውን የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንዲሁም የገና በዓል አስመልክቶ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሚሄዱ የውጪ ሃገር ዜጎች በተለይም ለዲኘሎማቲክ ማህበረሰቡ አውደርዕይ መሰናዳቱ ተነገረ፡፡

 

ኢትዮጵያን ለዓለም ሀገራት ለማስተዋቅ የተለያዩ ለስጦታ የሚሆኑ ምርቶች ይገኙበታል የተባለው አውደርዕይ የተሰናዳው በሦስት ድርጅቶች ነው ተብሏል፡፡

 

ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኤቨንት፣ ዲሊኦፖል ሆቴል፣ እና ሳራ ኔክስት ፋሽን ዲዛይን በጋራ አውደርዕዩን ማሰናዳታቸው ተነግሯል፡፡

 

የፈረንጆቹ የገና በዓል የተለያዩ ስጦታዎች የሚሰጡበት በመሆኑ ይህንን እድል በመጠቀም ምርቶች እንዲተዋወቁ አውደ ርዕዩ መሰናዳቱን የሳራ ኔክስት ፋሽን ዲዛይን መስራች ሳራ መሀመድ ተናግረዋል፡፡ 

በአውደ ርዕዩ በተለያዩ ምርቶች ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች እንደሚሳተፉ እና ልምድ የሚለዋወጡበትም እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል፡፡

 

ይህንንም በመጠቀም ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁ አምራቾች በገበያ ላይ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለመጨመርና የተሻለ የገበያ እድል እንዲፈጠርላቸውም ያግዛል ተብሏል፡፡

 

የኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኤቨንት ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሩት ኃይሉ በበኩላቸው  የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑንና በዓይነቱ ለየት ባለ መልኩ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ላይ በማተኮር የተለያዩ ዝግጅቶች የተሰናዱበት ነው ብለዋል፡፡

 

ዲፕሎማቶች የተለያዩ ኤምባሲ ተወካዮች የንግድ ተቋማት መሪዎች እና በተለያየ ሙያ ላይ ያሉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል ብለዋል፡፡

 

በሦስቱ ተቋማት የተሰናዳው የዲፕሎማቲክ አውደ ርዕይ ከመጪው ህዳር 19-21 2018  ዓ.ም በዲሊኦፖል ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ የተለያዩ ምርቶች የሚቀርቡበት እንደሆነም ሰምተናል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

 

ምህረት ስዩም

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

 

Recent Posts

See All
ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡

ሐምሌ 21 2018 ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡ የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡ ከቅርብ

 
 
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page