ኢትዮጵያ የአርብቶ አደሮችን ድንበር ተሻጋሪ ችግሮች ለመፍታት ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተባብራ እንደምትሰራ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ(ዶ/ር) ተናገሩ።
- sheger1021fm
- 2 minutes ago
- 1 min read
ህዳር 13 2018
ኢትዮጵያ የአርብቶ አደሮችን ድንበር ተሻጋሪ ችግሮች ለመፍታት ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተባብራ እንደምትሰራ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ(ዶ/ር) ተናገሩ።
በአካባቢው ሀገራት የሚገኙ አርብቶ አደሮች ወቅቶችን በመከተል ከቤት እንስሳቶቻቸው ጋር ድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታው አስታውሰዋል።
በዚህ እንቅስቃሴያቸውም ከግጦሽ መሬት እና ውሃ ጋር የተገናኙ ችግሮች ይገጥሟቸዋል ብለዋል።
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ኢትዮጵያ ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተቀራርባ እንደምትሰራ ተናግረዋል።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD) ትኩረቱን በአካባቢው ሀገራት በሚገኙ አርብቶ አደሮች ላይ ያደረገ ውይይት እዚህ በአዲስ አበባ አካሂዷል።

በውይይቱም በአካባቢው አርብቶ አደሮች መካከል ኢኮኖሚያዊ ትብብርን በማሳደግ ሠላማዊ ግንኙነትን ማጠናከር ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቅሷል።
ኢጋድ ጁቡቲ ፤ ኤርትራ ፤ኢትዮጵያ ፤ ኬንያ ፤ ሶማሊያ ፤ ደቡብ ሡዳን፤ ዩጋንዳ እና ሡዳን ያሉበት ስብስብ እንደሆነ ይታወቃል።
በአፍሪካ አህጉር ካሉ 250 ሚሊየን አርብቶ አደሮች ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት በእነዚሁ ሀገራት የሚገኙ እንደሆኑ ተጠቅሷል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








