አሐዱ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ተናገረ።
- sheger1021fm
- 11 minutes ago
- 1 min read
ህዳር 13 2018
አሐዱ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ተናገረ።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ በበዙ የባንክ ስኬት መለኪያዎች ይበል የሚያስብል ውጤት ማስመዝገቡን በዛሬው ዕለት ባካሄደው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናግሯል።
ይህ ውጤት የተመዘገበውም በበዙ ችግሮች ውስጥ አልፎ መሆኑንም ጠቅሷል።

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ በበጀት ዓመቱ 7.88 ቢሊዮን ብር ደርሷል፤ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ41 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።
በሂሳብ ዓመቱ ከ88.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰቡንም #አሐዱ_ባንክ ጠቅሷል።
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ10.3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከ2.16 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ87 በመቶ እድገት አሳይቷል ሲል የባንኩ ሪፖርት ያስረዳል፡፡
የአሐዱ ባንክ አጠቃላይ ሀብት ከ10.1 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፤ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ57 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል፡፡
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 502.1 ሚሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል፣ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ351 በመቶ ብልጫ ያለው እድገት አሳይቷል፡፡
የተከፈለ ካፒታሉ 1.13 ቢሊዮን ብር፣ ጠቅላላ እዳው ደግሞ 8.55 ቢሊዮን ብር መሆኑን ከሪፖርቱ ተመልክተናል ።
አጠቃላይ የደንበኞቹን ብዛት 1.1 ሚሊዮን፣የቅርንጫፎቹ ብዛት 102 እንደደረሱለት ተጠቅሷል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments