top of page

''ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመለሽ ተሽከርካሪዎችን እቀጣለሁ'' የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

  • sheger1021fm
  • 6 minutes ago
  • 1 min read

ህዳር 10 2018

 

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመለሽ ተሽከርካሪዎችን እቀጣለሁ አለ።

 

ቢሮው ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች በከተማዋ እየበዙ ነው ያለ ሲሆን ከዚህ በኋላ በመመሪያው መሰረት ረዳት የሌላቸውን ታክሲዎች እቀጣለሁ ብሏል።

 

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት  አገልግሎት ክትትልና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ታመነ ያለ ረዳት ማሽከርከር ገንዘብ በመቀበል፣ገቢና ወራጅ በመቆጣጠር የሹፌሩን ትኩረት ስለሚሰርቅ ለአደጋ ያጋልጣል ብለውናል።

 

ree

ኃላፊው ከዚህ ቀደም ለሌሎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ብቻ ትኩረት በመስጠታችን ረዳት ያላቸውና የሌላቸውን ተሽከርካሬዎች የመለየት ውስንነት ታይቶብናል ብለዋል።

 

ከዚህ በኋላ ግን የታክሲ ረዳት መኖር አንዱ የትራፊክ ደህንነት አካል በመሆኑ ሁሉም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. 

 

ንጋት መኮንን

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page