top of page

‘’በሩብ ዓመቱ ከቀረቡልኝ ቅሬታዎች የሚበዙት፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው’’

  • sheger1021fm
  • Nov 21
  • 1 min read

ህዳር 12 2018

 

ህዝብ የሚበድሉ አንዳንድ የመንግስት እና የግል ተቋማት የምሰጣቸውን የእርምት ሀሳብ ባለመቀበል እያስቸገሩኝ ነው ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ።

 

ተቋማቱ አስተዳደራዊ በደል መፈፀማቸውን ያምናሉ፤ ግን ለማስተካከል ፍቃደኛ እየሆኑ አይደለም ተብሏል።

 

በተቋሙ የህግና አስተዳደር በደል ምርመራ መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መንግስቱ ቀኜ አስተዳደራዊ በደል ፈፅመው እንዲያስተካክሉ የነገርናቸው አንድ አንድ ተቋማት፣ የመፍትሔ ሃሳቡን መቀበላቸው በጥፋተኝነት ያስጠይቀናል የሚል ፍራቻ አላቸው ብለውናል፡፡

 

አንድ አንድ ተቋማት ደግሞ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ምንም አይነት ህጋዊ ዕርምጃ መውሰድ አይችልም የሚል የተሳሳተ ግምት እንዳላቸው ኃላፊው ነግረውናል።

 

ree

የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በሩብ ዓመቱ ከቀረቡለት አቤቱታዎች ከ50 ከመቶ በላይ ቅሬታዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው ብሏል።

 

ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ባህርዳርና ሃዋሳ ብዙ አቤቱታ ከሚቀርቡባቸው ከተሞች መካከል ናቸው ተብሏል፡፡

 

የተቋሙ ህግና አስተዳደር ምርመራ ኃላፊው የሚሰጣቸውን የእርምት ሃሳብ የማይቀበሉ የመንግስትም ይሁን የግል ተቋማት ላይ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ስልጣን አለው ብለዋል።

 

ኃላፊው ወደ ተቋማቸው ከሚመጡ ቅሬታዎች የመሬት ይዞታና ያለ አግባብ ከሥራ መባረር እንደሚበዛ ነግረውናል።

 

በማንኛውም የመንግስት እና የግል ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ በደል ደርሶብኛል የምትሉ ቅሬታችሁን በ9503 ነፃ የስልክ መስመር በኩል ማቅረብ ትችላላችሁ ተብላችኋል።

 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

 

ንጋት መኮንን

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

 

Recent Posts

See All
በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡

ታህሳስ 6 2018 በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ የአካባቢው ቡሣ ጎኖፋ ወይም የእርዳታ ማስተባበሪያ በበኩሉ ድጋፍ እንዲቀጥል ለሚመለከተው የበላይ አካል ባሳውቅም ድጋፍ ግን ሊቀጥል አልቻለም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page