top of page

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ከሀገር ከወጡ ከመቶ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ቅርሶች ተቀበለ

  • sheger1021fm
  • 7 minutes ago
  • 1 min read

ህዳር 11 2018


ከሀገር ከወጡ ከመቶ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ቅርሶች፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ተቀበለ።


ቅርሶቹ 12 ሲሆኑ በአንድ ቤተሰብ አባላት ተጠብቀው የቆዩ መሆናቸውን ሰምተናል።


ከቅርሶቹ መካከል ፎቶግራፎች፣ ጋሻ፣ ዘውድ፣  ዝናር፣ ጎራዴ እና ሌሎች  ይገኙበታል።


ቅርሶቹ ከ1913 እስከ 1921 ዓ.ም በወቅቱ በነበሩት ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ እና ከአልጋወራሽ ተፈሪ መኮንን በኢትዮጵያ የጀርመን መልዕክተኛ ለነበሩት ቪስ ትሪዝ በስጦታ መልክ የተበረከተላቸው እንደሆኑም ሰምተናል።


ቅርሶቹን በአሁኑ ሰዓት በስዊዲን ሀገር የሚኖሩት  የመልዕክተኛው  የልጅ ልጅ  ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም በዛሬው ዕለት በራስ መኮንን አዳራሽ በተከናወነ ሥርዓት አስረክበዋል።

ree

ቅርሶቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም፣ የጀርመን ኤምባሲ፣ የስዊዲን ኤምባሲ በትብብር መስራታቸው ተሰምቷል።


በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ የጀርመን ኤምባሲ ጉዳይ አስፈፃሚ ፈርዲናንድ ቮን ቬይሄ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡


ቅርሶቹ ወደ ቤታቸው መመለሳቸው እጅግ አስደሳች ነው ሲሉ የተናገሩት የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ  የአምባሳደሩ ቤተሰቦች ቅርሶቹን መልሰው በማስረከባቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር ዮሃንስ አድገ(ዶ/ር) ቅርሶቹ መመለሳቸው ለጥናት እና ምርምር ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።


በመላው ዓለም በግለሰቦች እጅ እና በተቋማት ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያስረዱ ቅርሶች  ወደ ሀገር የማስመለሱ ስራ ይቀጥላል ተብሏል፡፡


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page