ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በኢትዮጵያ በሚከሰቱ ሞቶች ከግማሽ በላይ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑንን ጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
- sheger1021fm
- 25 minutes ago
- 1 min read
ህዳር 12 2018
ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በኢትዮጵያ በሚከሰቱ ሞቶች ከግማሽ በላይ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑንን ጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
የኩላሊት ህመተኞችን በተመለከተ የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች መጀመራቸውን ሰምተናል፡፡
እየጨመሩ ካሉ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች መካከል የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት፣ ስትሮክ፣ ኩላሊት፣ የልብና የደም ስር መዘጋት እንዲሁም የአዕምሮ መታወክና ካንሰር ከብዙ በጥቂቶቹ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ተናግሯል፡፡

በተለይም የደም ግፊት ከፍተኛ ለሆነ የኩላሊት በሽታ እያጋለጠ እንደሆነና በዚህም 6 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ስር ለሰደደ የኩላሊት ህመም አንደሚጋለጡ በጥናት መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ነግረውናል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያሉት ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምን ለማከም የቅድመ ምርመራ ለመከወን እንዲሁም የጤና ባለሞያዎችን ለማብቃት የወጣውን መመሪያ ለማብሰር እና የዚሁ አካል ከሆኑት ከPSI ኢትዮጵያ እና አስትራ ዜኒካ ከተባሉ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








