top of page


ጥቅምት 10 2018 - ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ህይወታቸው ማለፉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተናግሯል።
Oct 201 min read


ጥቅምት 8 2018 "ልዩ ባስ" የሚል መጠርያ ያለው ለሀገር አቋራጭ መንገደኞች ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ
አዲስ ፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ እና እንግዳ ትራቭል ቴክኖሎጂ  በጋራ "ልዩ ባስ" የሚል መጠርያ ያለው ለሀገር አቋራጭ መንገደኞች ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂ ዛሬ ማስጀመራቸውን ተናገሩ። ይህ ቴክኖሎጂ ደንበኞች ወይም ተጓዦች ባሉበት ቦታ ሆነው ወደየሚፈልጉበት አካባቢ ለመጓዝ "የልዩ ባስ" የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም  ቲኬታቸውን በኦንላይን መቁረጥ ይችላሉ ተብሏል። የእንግዳ ትራቭል ቴክኖሎጂ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ  አቶ ባንተአብ አብይ እንደተናገሩት ቴክኖሎጂውን ስራ ላይ ለማዋል አራት ዓመት እንደፈጀ እና አገልግሎቱን ከደንበኞች በተጨማሪ የግል ባስ ባለንብረቶች  ስራቸውን ለማቀላጣፍ መጠቀም የሚችሉበት ነው ብለዋል። ይህንን አገልግሎት ደንበኞች ቅንጡ ስልካቸውን በመጠቀም ወደቲኬት መቁረጫ ቦታ ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው መቁረጥ እንደሚችሉም ሰምተናል።
Oct 181 min read


ጥቅምት 8 2018 - በዚህ ተለዋዋጭ የዓለም ስርዓት አፍሪካ እንዴት ተጠቃሚ ትሁን?
በአፍሪካ ሰላምና ደህነት ዙሪያ የሚመክረው የጣና ፎረም የዘንድሮው መድረክ ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ስርዓት አፍሪካ እንዴት ተጠቃሚ ትሁን በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ይመክራል ተብሏል። ለተወሰነ ጊዜያት ተቋርጦ የቆየው የጣና ፎረም 11ኛው መድረክ ከመጪው ጥቅምት 14 እስከ 16 እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ፎረም ከመላው ዓለም የተወጣጡ የአፍሪካን ቀንድ ሁኔታን  የሚከታተሉ ልዩ መልክተኞች፣ የተመድ፣ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ቀጠናውን በተመለከተ እንዲወያዩ መጋበዛቸውንም ሰምተናል፡፡ በዚህ በየጊዜው እየተለዋወጠ ባለው የአለም ስርዓት አፍሪካ እንዴት ብትራመድ ተጠቃሚ ያደርጋታል በሚል፣ የአህጉሪቱ መሪዎች፣ ሚኒስትሮች እና የሚመለከታቸው አካላት እንደሚመክሩም ተነግሯል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ዘሪሁን 
Oct 182 min read


ጥቅምት 8 2018 የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ተቋም ለአንድ ዙር የመድኃኒት ግዥ ለመፈፀም 200 ቀናት እንደሚፈጅበት ተናገረ።
በዚህም ምክንያት መድኃኒት ተገዝቶ ወደ ጤና ተቋማት እስኪደርስ እስከ 4 ወር ሊፈጅ ይችላል ተብሏል። የሠላም ዕጦት ችግር ባለባቸው የኦሮሚያ፣ የአማራና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አካባቢዎች ደግሞ ችግሩ ከዚህም እንደሚከፋ ተነግሯል። ተቋሙ የመድኃኒት አገልግሎት አዋጅ እንደ አዲስ ከተሻሻለ በኋላ ለ #መድኃኒት ግዢ የሚወስድብኝ ጊዜ በፊት ከነበረው በግማሽ ቀንሷል ቢልም የክልል የጤና ተቋማት ግን አሁንም በመድኃኒት አቅርቦት መዘግየት እየተፈተንን ነው ብለዋል። ይህ የተባለው በ7ኛው ብሔራዊ የመድኃኒት አቅርቦት  ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ነው። በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ወደ ኃላፊነት የመጡ ሰሞን በህዝብ እንደራሴዎች በኩል የሚቀርብላቸው ጥያቄ ሁሉ የመድኃኒት አቅርቦት እንደነበር ተናግረዋል። በዚህም ማህበረሰቡ በመድኃኒት አ
Oct 181 min read


ጥቅምት 7 2018 - ኢትዮጵያ በተለያዩ ተቋማት ለሚዘረጉ መሠረተ ልማቶች እስከ አሁን ማስተር ፕላን እንደሌላት ተነግሯል
አሁን ማስተር ፕላኑን የማዘጋጀቱ ስራ እንደተጀመረም ሠምተናል።   ከመሰረተ ልማት ዘርጋታ ጋር በተገናኘ እያጋጣሙ ያሉ ችግሮች አንዱ መነሻ ዘርፉን የተመለከተ ማስተር ፕላን አለመኖር እንደሆነ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ተናግሯል።   የትኛው መሰረተ ልማት በየት በኩል ይለፍ፣ የትኛውስ ምን ቦታ አገልግሎት ይስጥ? የሚለው በዚህ ፕላን የተደገፈ አይደለም ሲሉ፤   የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ኢትዮጵያ በዴቻ ተናግረዋል።   አሁን ይህን ማስተር ፕላን ለማዘጋጀት ስራዎች ተጀምረዋል ያሉን አቶ ኢትዮጵያ መሰረተ ልማቶቹን የሚዘረጉ ተቋማት በስራው መሳተፋቸውንም ነግረውናል።   ተቋማቱ ማስተር ፕላኑን በማዘጋጀቱ ሂደት ከመሳተፍ ባሻገር ሃብት እና ባለሞያ ማዋጣታቸውንም ጠቅሰዋል።   በስራው እየተሳተፉ ያሉ ሞያተኞች ማስተር ፕላኑን
Oct 171 min read


ጥቅምት 7 2018 - በአዲስ አበባ አንድም የቢንጎ ማጫወቻም ሆነ የአረቄ መሸጫ ቤት መኖር የለበትም ተባለ፡፡
ከዚህ በፊትም እነዚህ ቤቶች ከከተማው አንዲጠፋ መመሪያ ተሰጥቶ ነበር፤ ግን አሁንም ድረስ ቤቶቹ መኖራቸውና በስራ ላይ መሆናቸው ታውቋል ተብሏል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም የአዲስ አበባ ከተማ ከ #ቢንጎ ማጫወቻ እና የ #አረቄ መሸጫ ቤት ነፃ እንዲሆን ይደረጋል መባሉን ሰምተናል፡፡ ይህንን ያለው የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ነው፡፡ ቤቶቹ እንዳይኖሩ ይደረጋል ያለው ተቋሙ ምክንያቴም ቤቶቹ የወንጀል ምክንያት በመሆናቸው ነው ብሏል፡፡ የቢሮው ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የቢንጎ ማጫወቻ እና በየመንደሩ ያሉ አረቄ ቤቶች የከተማው ወንጀል መፈልፈያ ቦታዎች ናቸው ብለዋል፡፡ ይህንን ማስፈፀም ያልቻሉ ሀላፊዎችም በቦታቸው አይቀጥሉም ብለዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. ገዛ ጌታሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website
Oct 171 min read


ጥቅምት 7 2018 - በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች በሬሚዲያል መርሀ-ግብር ተማሪዎች እንደማይቀበሉ ተነገረ
በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች በሬሚዲያል መርሀ-ግብር ተማሪዎች እንደማይቀበሉ ተነገረ፡፡ ይህንን ያለው ትምህርት ሚኒስቴር ነው፡፡ ሚኒስቴሩ በ2017 ዓ.ም የ12 ክፍል ፈተና ተፈትነው በሬሚዲያል መርሀ-ግብር የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን የሚያስተካክሉበት ቀንን ይፋ አድርጓል፡፡ በእዚህ መሰረት ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ( https://student.ethernet.edu.et/ ) በመግባት ማስተካከል እንደሚችሉ ተናግሯል፡፡ የተቋም ምርጫ የሚደረገውም በየትምህርት ቤቶች በተወከሉ መምህራን በኩልም ነውም ብሏል፡፡ በሀገሪቱ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥም ሰባቱ በሬሚዲያል መርሀ-ግብር ተማሪዎች እንደማይቀበሉም ተነግሯል፡፡ ተማሪዎች አይቀበሉም የተባሉት፤ ሀዋሳ
Oct 171 min read


ጥቅምት 6 2018በየመስሪያ ቤቱ ያለ አገልግሎት የተከማቹ ንብረቶችን በወቅቱ በማስወገድ ወይም በመጠገን ብክነትን መከላከል ያስፈልጋል ተባለ።
የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን፤ ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸሮችን መልሼ በመጠገን ከ187 ሚሊየን ብር በላይ ከብክነት አድኛለሁ ብሏል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፈው የ2017 በጀት ዓመት 5,580 ፈርኒቸሮችንና 6,519 የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ጠግኖ ወደ አግልግሎት መመለሱን ተናግሯል። ይህ የተነገረው ዛሬ የኤሌክትሮኒክስና የፈርኒቸር ጥገና የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ነው። የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የንብረት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ጸሐይ መንግስቱ  ያለ አገልግሎት የተከማቹ ንብረቶችን በወቅቱ በማስወገድና በመጠገን ብክነትን መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል። ኃላፊዋ ለ2018 በጀት ዓመትም ተጠግነው አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ንብረቶች  በኮሌጅ፣ በሆስፒታል፣ በጤና ጣቢያ፣ በትምህርት ቤት ወረዳ እና ክፍለ ከተማ፣ የ
Oct 161 min read


ጥቅምት 6 2018 - ኢትዮጵያ በንጋት ሃይቅ ላይ በምትጀምረው የውሃ ትራንስፖርት ከሱዳኑ ሪዞሬ ግድብ መስመሩን የማስተሳሰር ፍላጎት አላት ተባለ
ኢትዮጵያ በንጋት ሃይቅ ላይ በምትጀምረው የውሃ ትራንስፖርት በቅርብ ርቀት ከሚገኘው የሱዳኑ ሪዞሬ ግድብ ጋር መስመሩን የማስተሳሰር ፍላጎት አላት ተባለ። ይህም ሁለቱ ሀገሮች የሚጋሩት ውሃን መሰረት ያደረገ የቱሪዝም አማራጭን ሊፈጥር የሚችል ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ መገንባት ተከትሎ በተፈጠረው በአፍሪካ በመጠኑ አራተኛ ነው በተባለው #የንጋት_ሃይቅ ላይ እና በዙሪያው የምትሰራውን ስራ የሚመራ ፍኖተ ካርታ እያሰናዳች ነው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) በሃይቁ ዙሪያና በአጠቃላይ በተፋሰሱ ላይ የሚሰሩ ሰራዎች ሁሉ የሚመሩበት ማመሳከሪያ ፍኖተ ካርታ ያስፈልጋል ብለዋል። የሃይቁን ውሃ መያዝ ተከትሎ የሚመረተው የዓሣ ምርት መጠኑ ከጊዜ ጊዜ እያደገ መጥቷል። ሚኒስትሩ እንደሚሉት ግን የቱ ቦታ ለዓሳ ምርት፣ የቱ ለውሃ ትራንስፖ
Oct 161 min read


ጥቅምት 6 2018 - ''ተገልጋዮችን የሚያንገላቱ፣ ጉቦ የሚቀበሉ ሰራተኞቼን እያባረርሁ በህግ እንዲጠየቁም እያደረግሁ ነው'' ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
ተገልጋዮችን የሚያንገላቱ፣ ጉቦ የሚቀበሉ እና መሰል ጥፋቶችን የሚሰሩ ሰራተኞቼን እያባረርሁ በህግ እንዲጠየቁም እያደረግሁ ነው ሲል የከተማዋ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡   የነዋሪነት መታወቂያ፣ ያገባና ያላገባ ሰነዶችን ማግኘትና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት ተገልጋዩን የሚያመላልሱ ሰራተኞች መኖራቸው ተነግሯል።   እነዚህን ሰራተኞች በስልጠና አግዛለው፤ አጥፍተው የሚገኙትንም መቅጣት እጀምራለሁ ብሏል ተቋሙ።   ይህንን ያሉን የኤጀንሲው ምክትል ዳሬክተር ጥጋቡ ሹመይ ናቸው።   ነዋሪዎች ከተቋሙ አገልግሎት ፈልገው በሚመጡበት ወቅት፤ ጉዳይ የሚያንዛዙ የተቋሙ ሰራተኞች እንዳሉ ደርሼበታለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡   በተለይም እንዲህ ዓይነቱ ችግር በወረዳዎች ላይ እንደሚታይ ነግረውናል፡፡   በተያያዘም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12
Oct 161 min read


ጥቅምት 6 2018 - የኢትዮጵያ የሚዲያ የልህቀት ማዕከል ስራ ጀመረ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ስራ የጀመረው ማዕከሉ የሚዲያ ተቋማትንና  የባለሞያዎችን አቅም የመገንባት ስራን ይሰራል ተብሏል። ማዕከሉ የተመሰረተው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን መሆኑን በዝግጅቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡ በልህቀት ማዕከሉ መክፈቻ ዝግጅት ላይ የሕዝብ እንደራሴዎች  ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡ በልህቀት ማዕከሉ በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስልጠና እንደሚሰጥ የተነገረ ሲሆን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እና ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተነግሯል። የማዕከሉ መቋቋም ዋና ዓላማ የጋዜጠኞችን የሙያ እውቀት እና ክህሎትን ማሳደግ ላይ በትኩረት መስራት ነው ተብሏል። በአለም አቀፍ የሚዲያ አሰራር መሰረት ባለሙያው ከጋዜጠኝነት ትምህር
Oct 161 min read


ጥቅምት 6 2018 - “የግዕዝ ቋንቋ በትምህርት ስርዓት ውስጥ”
የግዕዝ ቋንቋ በአማራ ክልል በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሰጠት በዚህ ዓመት ተጀምሯል፡፡ ይህንን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ ወጥቶታል፡፡ አንዳንዶች እስይ ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ አስፈላጊ አይደለም ልጆቻችንም አይማሩም ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ በቋንቋ አስፈላጊነት ላይ ጥያቄ ባያነሱም ከስንተኛ ከፍል ጀምሮ ነው ቋንቋው ለተማሪዎች መሰጠት ያለበት በሚለው ላይ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ “የግዕዝ ቋንቋ በትምህርት ስርዓት ውስጥ” በሚል ርዕስ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም  በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አዘጋጅነት በርካታ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተሳታፊዎች በተገኙበት ውይይት ተካሄዷል፡፡ በስነ ልሳን መምህሩ እና ተመራማሪው ዘላለም ልየው(ፕ/ሮ) አወያይነት፤ በበድሉ ዋቅጅራ(ዶ/ር) እና በይኩኖአምላክ መዝገቡ መካከል ውይይ
Oct 165 min read


ጥቅምት 5 2018 በኮሪደር ልማት ላይ ሸንቶ ያመለጠ ግለሰብ ተይዞ 2,000 ብር ተቀጣ፡፡
በኮሪደር ልማት ላይ ሸንቶ ያመለጠ ግለሰብ ተይዞ 2,000 ብር ተቀጣ፡፡ መኪና በማቆም በኮሪደር ልማት ላይ የምትሸኑ ከድርጊታችሁ ተጠንቀቁ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አሳስቧል፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ከዋናው አየር መንገድ ልዩ ስሙ ወሎ ሰፈር አካባቢ መኪና በማቆም በኮሪደር ልማት ላይ ሽንት በመሽናት ያመለጠ ግለሰብ ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር መዋሉን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ግለሰቡ በፈፀመው የደንብ መተላለፍ ም  2,000 ብር መቅጣቱ ተነግሯል፡፡ መሰል ደንብ ተላለፊዎች  ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣ ደንብ ተላላፊዎችም ከድርጊታቸው ተቆጠቡ ሲል  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  አሳስቧል። ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲ
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018 - የመጀመሪያው የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል?
የመጀመሪያው የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ ትናንት በተጀመረው እና እስከ ነገ በሚቀጥለው ጉባኤ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሚኒስትሮች፣ የዘርፉ ባለሞያዎች፣ ባህርተኞች እና ቀጣሪ ድርጅቶች እየተሳተፉ ነው፡፡ ለመሆኑ ይህ ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል ስንል #የኢትዮጰያ_ማሪታይም_ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋን ጠይቀናቸዋል፡፡ ጉባኤው በዘርፉ ለሚሰለጥኑ ባለሞያዎች የገበያ ትስስር፣ ለማሰልጠኛ  ተቋማት ደግሞ ዘርፉ የሚፈልገውን አለም አቀፍ ክህሎት ምን መሳይ ነው የሚለው እንዲያውቁት እንዲሁም ከትልልቅ የዘርፉ ድርጅቶች ልምድ ለመውሰድ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል ሀላፊው፡፡  ኢትዮጵያ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ማሪታይም ትሬኒንግ ኢኒስትቲዩት እና በቢሾፍቱ የሚገኘው የባቦጋ
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018 - ልዩ የኢኮኖሚ ዞንም ለመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ እንዲሆን ተወስኗል
ኢትዮጵያ ከመድሀኒት ፍላጎቷ ከ40 በመቶ በላዩን በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን መቻሏ ይነገራል፡፡ መንግስት ለመድሀኒት ግዥ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በሂደት በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ሙሉ በሙሉ የማስቀረት ፍላጎት አለው፡፡ ኢትዮጵያ ካሏት 10 የኢኮኖሚ ዞኖች የቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንም ለመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በኢንዱስትሪ መንደሩ ግን የሚፈለገውን ያህል ባለሀብቶች እየገቡ አይደለም፡፡ ታዲያ የታሰበውን ግብ እንዴት ማሳካት ይቻላል? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ንጋቱ ረጋሣ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRa
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018 - የመንግስት ሰራተኞች ከፈቃዳቸው ውጪ፣ ከደመወዛቸው ገንዘብ እየተቆረጠባቸው ነው ተባለ
ይህም ህገ ወጥም አሳሳቢም ነው ተብሏል። ይህንን ያለው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ነው። ተቋሙ ከህግ ውጪ የመንግስት ሰራተኞች ከደመወዛቸው የሚቆረጥባቸው ገንዘብ ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል። የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ተደጋጋሚ ቅሬታ እየቀረበልኝ ነው ብሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲዳማ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ያሉ መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሰራተኞች ፈቃዳቸውን ሳይሰጡ ከደመወዛቸው ላይ ገንዘብ እየተቆረጠባቸው መሆኑን ነግረውኛል ብሏል። በተመሳሳይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞንም በተለያዩ ወረዳዎች የሚሰሩ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተነግሯል። ይህም የችግሩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረስ ያሳያል ብሏል የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ መግለጫ። ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ስምምነቱን በፅሁፍ ሲገልፅ፣
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018የመስከረም ወር የዋጋ ግሽበት 13.2 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ፡፡
ያለፈው ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት መጠን 13.2 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተናግሯል። ከአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ውስጥ የምግብ ነክ ዕቃዎች (Food Items) የዋጋ ግሽበት 12.1 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) የዋጋ ግሽበት ደግሞ 14.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ነሐሴ ወር ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ በነሐሴ ወር አጠቃላይ የግሽበት ምጣኔው  13.6 በመቶ ነበር፡፡ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Faceb
Oct 151 min read


ጥቅምት 5 2018 - በታዋቂ ሰዎች የተዋወቁ ምርትና አገልግሎቶች ''የሀሰት ሆነው አገኘናቸው እነሱን አምነን ተታለልን'' የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ፡፡
በገበያው የሚሸጥ የሚለወጠው ብዙ ነው፡፡ ቤት፣ መኪና፣ አክሲዮን፣ የፋብሪካ ምርት፣ አገልግሎት፣ በየመገናኛ ብዙሃኑ የሚተዋወቀው ብዙ ነው፡፡  ገዥና ሻጭም በዚሁ የማስተዋወቂያ መንገድ በቀላሉ ይገናኛል፡፡ ውል ይታሰራል ግብይት ይፈፀማል፡፡ ማስታወቂያ አስነጋሪዎች መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ #ታዋቂ_ግለሰቦችን መጠቀም አምባሳደር አድርገው ማሰራታቸውም የተለመደ ነው፡፡ አንዳንዴ ግን በእነዚህ ታዋቂ ሰዎች የተዋወቁ ምርትና አገልግሎቶች ''የሀሰት ሆነው አገኘናቸው እነሱን አምነን ተታለልን'' የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ፡፡ ለመሆኑ በዚህ ጉዳይ ህጉ ምን ይላል? ተጠያቂውስ ማነው? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ገዛ ጌታሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube...
Oct 151 min read


ጥቅምት 4 2018 - ህንድ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የባህላዊ መድሀኒት ሀብት በሳይንስ የተደገፈ እንዲሆን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ተናገረች።
ህንድ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የባህላዊ መድሀኒት ሀብት በሳይንስ የተደገፈ እንዲሆን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ተናገረች። በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የህክምና ግብዓት፣ የመድሃኒት አቅርቦት እና የህክምና እሴት ለማሳደግ ይርዳል የተባለለት ጉባኤ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በህንድ ኤምባሲ ተካሄዷል፡፡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ከህንድ ሀገር የመጡ የህክምና ባለሞያዎች፣ የጤና ተቋማት ሃላፊዎች እና መድሃኒት አስመጪዎች ተገኝተዋል። በመድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር፤ አፍሪካ ተላላፊ እና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ቀዳሚ ተጎጂ አህጉር መሆኑን አስረድተዋል። የሳምባ፣ ቲቢ፣ የወባ፣ ኤችአይቪ፣ የአዕምሮ ህመም፣ ካንሰር፣ ስኳር፣ ኩላሊት እና በመሰል ህመሞች አፍሪካ እንደምትሰቃይ ተና
Oct 143 min read


ጥቅምት 4 2018 - ኢትዮጵያ ታሪኳን ሙሉ ከዓለም ፊት ሲያሳንሳት የቆየው አንዱና ዋና ጉዳይ የምግብ ማጣት
የሀገሬው ህዝብ  ከገበታው ብዙ ጊዜ የሚያገኘው እንጀራ፣ ጤፍን እንኳን የጠገቡት ሀገሮች ረሃብተኞች የሚመገቡት እህል ነው የሚል ተቀጽላ  እስከመስጠት የደረሱበት ነው፡፡ "አንደ ኢትዮጵያዊ፣ አንደ ሀገር ስናስበው የፖለቲካ ታሪካችን ያበላሸብን፣ ውጪ ሀገር ስንሄድ አንገታችንን የምንደፋበት፣ የምናዝንበት ጉዳይ ረሃብ በሚባለው ነው፡፡ ጤፍ ምንድነው ሲባል የረሃብተኞች ምግብ ነው ይባላል፡፡ እናንተ እኮ አልተገዛችሁም ግን ረሃብተኛ ናችሁ ይሉናል" ይላሉ የግብርና ተመራማሪው እና መምህሩ ፍሬው መክብብ(ፕ/ር)፡፡ #የምግብ ጉዳይ መልስ ለመስጠት ሀገራት አንዳላቸው አቅም መንገዳቸውም ይለያያል፡፡ ገንዘብ ካለ ምግቡ የትም ይመረት ገዝተው የሚበሉ፣ ዜጎቻቸውን የሚመግቡ ሀገራት ብዙ ናቸው፡፡ የገበሬ ሀገር ባይሆኑም ህዝባቸው የሚመገበው አያጣም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ 
Oct 141 min read


ጥቅምት 4 2018 - ''መጪው ምርጫ የሚደረገው ከዚህ በፊት በነበረው የምርጫ ሥርዓት፣ ወይስ?'' ኢዜማ
መጪው ምርጫ የሚደረገው ከዚህ በፊት በነበረው የምርጫ ሥርዓት፣ ወይስ ሀገራዊ ምክክሩ በሥምምነት የሚቀይራቸውን ከፖለቲካና ከምርጫ ሥርዓቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ባካተተ ሁኔታ በአዲስ መልክ  ነው ሲል ኢዜማ ጠየቀ፡፡ በአዲስ መልክ ምርጫ ለማካሔድስ ምርጫው በተቀመጠለት ጊዜ ማጠናቀቅ ይቻላል ወይ ሲልም ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አንስቷል? ፓርቲው ይህንነ ጥያቄ ያነሳው ምረጫ ቦርድ የምርጫ ህጉ አንዳልተቀየረ ከተናገረ ብኋላ በመሆኑ ጥያቄው የረፈደበት አይሆንም ወይ? ፓርቲውን ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….  የኔነህ ሲሳይ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/Sheger
Oct 141 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








