top of page

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ተወዳደሪ ለመሆን የጉምሩክ አሰራሯን ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚጠበቅባት ጥናት አመላከተ፡፡

  • sheger1021fm
  • Nov 25
  • 1 min read

ህዳር 16 2018


ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ተወዳደሪ ለመሆን የጉምሩክ አሰራሯን ቀላል እና ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚጠበቅባት ጥናት አመላከተ፡፡


ጥናቱን ያስጠናው የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ሲሆን፤ ጥናቱን ለማጠናቀቅ 4 ወራት ፈጅቷል ተብሏል፡፡


የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና 1.4 ቢሊዮን ሰዎችን እና ወደ 3 ትሪሊዮን ዶላር ዓመታዊ ጥቅል ምርት የሚይዝ መሆኑ በጥናቱ ተካቷል፡፡


በጥናቱ መሰረት የኢትዮጵያ የጉምሩክ አሰራር ውስብሰብ እና ቅልጣፍና የሚጎለው ነው፡፡ ይህም አገሪቱ ተወዳዳሪ እንዳትሆን የሚደርግ ነው ፡፡


ኢትዮጵያ ከ6 ዓመታት በፊት ባፀደቀቸው በዚህ ነፃ የንግድ ስምምነት ተጠቃሚ እና ተወዳዳሪ ለመሆን የህግ ማዕቀፎቿን ፣ የተቋማት ቅንጅት፤ የጉምሩክ ህጎቿን እና የመሰረተ ልማት ክፍተቷን ማስተካካል ይጠበቅባታል ተብሏል፡፡

ree

ሀገሪቱ የንግድ ቀጠናውን የተመለከተ ፖሊሲ ቢኖራትንም በትግበራው እና ወደ ስራው መግባት ላይ ውስንነት መኖሩ ተጠቁሟል፡፡


የአገልግሎት እና ምርት ንግድ በዋናነት የሚያተኩረው አካባቢው ንግድ ላይ እንደሆነ የሚጠቁመው ጥናቱ አሁን በስራ ላይ ያለው ፖሊሲም አህጉር አቀፍ ንግድ ውድድር ላይ ከማተኮር ይልቅ ስራ እድል ፈጠራ፣ ከአባቢያዊ ንግድ ላይ ነው የሚተኩረው ይላል ጥናቱ፡፡


የኢንቨስትመንት የህግ ማዕቀፎችም ቢሆኑ ዋነኛ ትኩረታቸው በሀገር ውስጥ ላይ ነው ተብሏል፡፡


የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ሆኑ ሌሎች ተቋማት አሰራራቸውን በዲጂታል እና በአንድ መስኮት ማድረግ ፣ የተንዛዛ እና የማያሰራ የአሰራር ሥርዓቶቻቸቸውን ማስቀረት እንዳለባቸው ጥናቱ ይመክራል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Recent Posts

See All
በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡

ታህሳስ 6 2018 በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ የአካባቢው ቡሣ ጎኖፋ ወይም የእርዳታ ማስተባበሪያ በበኩሉ ድጋፍ እንዲቀጥል ለሚመለከተው የበላይ አካል ባሳውቅም ድጋፍ ግን ሊቀጥል አልቻለም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page