በጥልቀት ማድመጥን ለተሻለ ተግባቦት እንዴት እንጠቀምበት በሚለው ጉዳይ ላይ እየሰራበት መሆኑን ብሪትሽ ካውንስል ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- Nov 25
- 1 min read
ህዳር 16 2018
ሰዎችን ይበልጥ የምንረዳበት መላ የሆነውን በጥልቀት ማድመጥን ለተሻለ ተግባቦት እንዴት እንጠቀምበት በሚለው ጉዳይ ላይ እየሰራበት መሆኑን ብሪትሽ ካውንስል ተናገረ፡፡
በእንግሊዝ መንግስት የሚደገፈውና በሃገራት መካከል ግንኙነቶችን ለማጠናከር እንዲሁም ለወጣቶች የተለያዩ እድሎችን በመፍጠር እየሰራ እንደሆነ የሚናገረው ብሪትሽ ካውንስል፤ ዩዝ ኮኔክት በተባለው ፕሮግራሙ ወጣቶች ክልሎቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ይሰራል ያሉን የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተርና የፕሮግራም ሃላፊ የሆኑት መፅናናት ሳህለ ናቸው፡፡
ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ ከ70 በላይ ወጣቶችን በጥልቀት መደማመጥና መግባባት ላይ በማሰልጠን እነርሱ ሌሎችን እንዲያሰለጥኑ ለማድረግ እየሰሩ ስለመሆኑም ነግረውናል፡፡
ስለምን ይህንን ጉዳይ መረጣችሁት ያልናቸው ወ/ሮ መጽናናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገራችን የሚስተዋሉት አለመግባባቶችና ግጭቶች ያለመደማመጥ ውጤቶች በመሆናቸው ከዚህ እንድንወጣ እንዴት የበለጠ እንግባባ? የሚለው ጉዳይ መነጋገሪያ እንዲሆን፤ባህላችንን እንድንፈትሽ፤የጥናት መነሻ ሃሳብ እንዲሆን ለማድረግ ያለመ ነው ብለውናል፡፡
በባህላችን በጋራ ተነጋግረን ችግሮችን የምንፈታባቸው እንደ ቡና ስርዓት አይነት ልምዶች አሉን የሚሉት ሃላፊዋ ጥያቄው እንዴት በበጎ መልኩ ተጠቀምንበት የሚለው ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተቃራኒ ሃሳብ ያለውን ሰው ሃሳብ ምን ያህል የማዳመጥ ትዕግስት አለን?የሚለውም መፈተሽና መነጋገር ያለብን ጉዳይ ነው ሲሉም ያስረዳሉ፡፡
ባለመደማመጣችን እዚህም እዚያም ያሉ ግጭቶች ተፈጥረዋል ያሉን የዚህ አቶ አሳዬ ንጉሴ የተባሉ ስልጠናው ተሳታፊ ፖለቲከኞች አድምጡን ብለው የሚመጡትን ያህል ህዝቡ ምን ይፈልጋል የሚለውን ማድመጥ ቢችሉ መልካም ነው ይላሉ፡፡
በማህበራዊ ህይወታችን በአሁኑ ወቅት በብዙ ውጥረት ውስጥ እያለፍን ነው የሚሉት የህክምና ባለሙያ እንደሆኑ የለገሩን ሌላኛዋ ተሳታፊ ለሰዎች ችግር ጆሮ እየነፈግን ነው፤ ሰዎች መደመጥ ፈልገው የገጠማቸውን ሲነግሩን መልሰን የእኛን ችግር እንጭንባቸዋለን ብለዋል፡፡
ባሳለፍለነው እዳሜና እሁድ ለወጣቶች ስልጠናውን የሰጠው ብሪትሽ ካውንስል ወጣቶቹ ጥልቅ በሆነ መደማመጥ ዙሪያ ሌሎችን እንዲያሰለጥኑ ይደረጋል፤የዚህ ውጤት ታይቶ ፍላጎቱ ካለ ስልጠናውን ወደ ክልሎች እንደሚያሰፋውም ነግሮናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments