top of page

የልብ ህመም ለገጠማቸውና ወረፋ ለሚጠባበቁ ህፃናት ከእንግሊዝ በመጡ ባለሙያዎች ህክምና እየተሰጠ ነው ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Nov 25
  • 1 min read

ህዳር 16 2018

 

በልብ በር መጥበብ እንዲሁም በኢንፌክሽን ምክንያት የልብ ህመም ለገጠማቸውና ወረፋ ለሚጠባበቁ ህፃናት ከእንግሊዝ በመጡ ባለሙያዎች ህክምና እየተሰጠ ነው ተባለ፡፡

 

በኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ውስጥ ካሉ አብዛኛዎቹ በዚህ ችግር ምክንያት የመጡ ህፃናት መሆናቸው ተነግሯል፡፡

 

ህክምናው ልብ ሳይከፈት በደምስር የሚሰጥ የልብ ህክምና አይነት መሆኑን የነገሩን የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ዳዊት እሸቱ ከህክምና ስራው ባለፈ ለማዕከሉ የሚያስፈልጉ አላቂ የህክምና ዕቃዎች ድጋፍ ይገኝበታል ብለዋል፡፡

 

በዚህ ዙር ከ18-20 ህፃናት ህክምናው እንደሚሰራላቸውም ተናግረዋል፡፡

 

በማዕከሉ አሁንም ድረስ ወረፋ የሚጠባበቁ 8 000 ያህል ህፃናት መኖራቸውን የሚናገሩት ዶክተር ዳዊት አብዛኛዎቹ የዚህ ቀዶ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ናቸው፤ ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ህፃናት ቁጥርም በየዓመቱ ከሚሰራው በላይ እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡

 

በማዕከሉ በዓመት እስከ 650 ለሚሆኑ ህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና ይሰራል በሌላ በኩል በየዓመቱ 1300 አዳዲስ ህጻናት ወደ ማዕከሉ ይመጣሉ ተብሏል፡፡

 

ትልቁን ቁጥር የሚይዘው ይህ የልብ ህመም አይነት ነው የሚሉት ዶክተር ዳዊት በልጅነት የሚከሰቱ በተለያዩ ኢንፌክሽኖች ምክንያት የልብ በሮች ላይ ጉዳት ይደርሳል፤ ይህ ደግሞ የተለያዩ ችግሮችን ያመጣል ብለዋል፡፡

 

አሁን በዚህ የህክምና ተልዕኮ ህክምናው የሚሰራላቸው የልብ በር መጥበብ ችግር ያለባቸው ልጆች መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

 

ቼን ኦፍ ሆፕ የተባለው የህክምና ተልዕኮ ቡድን ከኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ጋር ከ 20 ዓመታት በላይ በጋራ ሲሰራ መቆየቱ የተነገረ ሲሆን ለዚህ የህክምና ተልዕኮ በዚህ አመት ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ሰምተናል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

ምህረት ስዩም

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Recent Posts

See All
በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡

ታህሳስ 6 2018 በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ የአካባቢው ቡሣ ጎኖፋ ወይም የእርዳታ ማስተባበሪያ በበኩሉ ድጋፍ እንዲቀጥል ለሚመለከተው የበላይ አካል ባሳውቅም ድጋፍ ግን ሊቀጥል አልቻለም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page