top of page

ህዳር 16 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Nov 25, 2025
  • 1 min read

የቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ጂን ፒንግ ታይዋን ከእናት አገሯ ጋር መቀላቀሏ በአሁኑ ወቅት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው አሉ፡፡


ሺ ጂን ፒንግ ስለዚሁ ጉዳይ በስልክ ለአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ እንደነገሯቸው የቻይና መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ማውራታቸው አናዶሉ ፅፏል፡፡

ታይዋን ራሴን የቻልኩ ነፃ አገር ነኝ ብትልም ቻይና ግን ታይዋንን እንዳፈነገጠች የገዛ ግዛቷ አድርጋ  ትቆጥራታለች፡፡


የቻይና መንግስት እና አድራጊ ፈጣሪው የቻይና ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር ቀደም ሲል ታይዋን በዚያም ሆነ በዚህ መልሳ የቻይና አካል መሆኗ አይቀርም ሲሉ ቆይተዋል፡፡


በአዲሱ የቻይና ፕሬዘዳንት የታይዋን አቋም የአሜሪካ ይፋዊ አስተያየት ምን እንደሆነ  አልተሰማም፡፡


ቻይና ቀደም ሲል በታይዋን ዙሪያ ገባ ታላላቅ የጦር ልምምዶችን ማድረጓን መረጃው አስታውሷል፡፡



አሜሪካ በደቡብ ኮሪያ ለቋሚ የጦር ቅኝት ያሰለፈችው ሰው አልባ በራሪ MQ9 ቢጫ ባህር ውስጥ ወደቀ፡፡


ሰው አልባው የቅኝት አውሮፕላን በምን ምክንያት ባህር ውስጥ እንደወደቀ የተጠቀሰ ነገር እንደሌለ አናዶሉ ፅፏል፡፡


በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም ተብሏል፡፡


አሜሪካ ሰው አልባውን የቅኝት አውሮፕላን በኮሪያ ካሰለፈችው ገና 2ኛ ወሯ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በቀጠናው ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር በቋሚ የጦር ፍጥጫ ላይ ትገኛች፡፡


አሜሪካ ከ70 ዓመታት በላይ የኮሪያ የጦር አጋር ሆና ዘልቃለች፡፡


ዋሽንግተን በደቡብ ኮሪያ 30,000 ያህል ወታደሮች እንዳሏት ይነገራል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page