top of page

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ ኢራንን ለመምታት መዘጋጀቱን ተሰማ፡፡

  • 1 hour ago
  • 1 min read

የካቲት 12/2018

 

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ ኢራንን ለመምታት መዘጋጀቱን ተሰማ፡፡

 

ዋሽንግተንን ቴህራንን በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለመምታት ዝግጅት ማድረጓን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ሰዎች ነግረውናል ብሎ የዘገበው ሲ ኤን ኤን ነው፡፡

 

ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን የመጨረሻውን ውሳኔ አለመስጠታቸው በመረጃ ተጠቅሷል፡፡

 

የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣናት በትላንትናው እለት በዋይት ሐውስ ተገኝተው በኢራን ጉዳይ ላይ ውይይት ማድረጋቸውም ተነግሯል፡፡

 

ትራምፕም ከኢራን ጋር ስለተደረገው ድርድር ሁኔታ ከልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ እና ከአማቻቸው ጃሬድ ኩሽነር ማብራሪያ እንደተሰጣቸው በመረጃው ተነስቷል፡፡

 

አሜሪካና ኢራን ያደረጉት ትራምፕ ቀይ መስመር በሚላቸው ጉዳዮች ላይ አሁንም ከስምምነት አለመድረሱ ተዘግቧል፡፡

 

በተጨማሪም አሜሪካ በሶሪያ የቀሯትን ወታደሮች ልታስወጣ ተነግሯል፡፡

 

ዋሽንግተን ከሶሪያ ወታደሮቿን በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ለማስወጣት መዘጋጀቷን የዋይት ሐውስ ምንጮቼ ነግረውናል ብሎ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

 

አሜሪካ ወደዚህ እርምጃ የገባችው ሶሪያ በግዛቷ ውስጥ ሽብርተኝነትን በመዋጋት በኩል የመሪነት ሚና እንድትጫወት ለማስቻልና በዚያ የአሜሪካ ሀይል በከፍተኛ ቁጥር መኖር ከዚህ በኋላ አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ ነው ተብሏል፡፡

 

የአሜሪካ ወታደሮች የአይ ኤስ ተፅዕኖንን ለመግታት የፀረ ሽብር ዘመቻ አካል ሆነው ባለፉት 11 አመታት በሶሪያ ውስጥ መቆየታቸው መረጃው አስታውሷል፡፡

 

በዚህ አመት መጀመሪያ አካባቢ በሶሪያ ከሚገኙ ሁለት የጦር ሰፈሮች የአሜሪካ ወታደሮች ለቀው መውጣታቸውም ተጠቅሷል፡፡

 

አሜሪካ ከሶሪያ ቀሪ ወታደሮቿን ለማስወጣት የወሰነችው ከኢራን ጋር የገባችው ፍጥጫ እየተካረረ ባለበት አጋጣሚ ነው፡፡

 

ንጋቱ ሙሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Recent Posts

See All
አዋሽ ኢንሹራንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦችን የጉዞ የጤና ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ።

የካቲት 12/2018 አዋሽ ኢንሹራንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦችን የጉዞ የጤና ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ። ስምምነቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኮሜርሺያል ኦፊሰር አቶ ለማ ያዴቻ እና የአዋሽ ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጅባት አለምነህ በዛሬው እለት ተ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page