top of page

ጥቅምት 28 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 2 min read

 

የካሜሮኑ አረጋዊ ፕሬዘዳንት ፖል ቢያ ለ8ኛ ጊዜ ቃለ መሐላ በመፈፀም አዲሱን ሀላፊነታቸውን ተረከቡ፡፡

 

ፖል ቢያ ለ8ኛ ጊዜ ቃለ መሐላ በመፈፀም ሀላፊነታቸው የተረከቡት በቅርብ ጊዜው የካሜሩን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አሸንፈዋል ከተባለ በኋላ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡

 

የ92 አመቱ አረጋዊ ፖል ቢያ እስካሁን ካሜሮንን ከ40 አመታት በላይ መርተዋታል፡፡

ree

 

በአሁኑ ጊዜም ከአገር መሪዎቹ መካከል በእድሜ አንጋፋው እሳቸው ናቸው፡፡

 

ፖል ቢያ በምርጫው አሸንፈዋል የተባለው ሁነኛ ተፎካካሪዎች ከምርጫ በታገዱበት አጋጣሚ ነው ተብሏል፡፡

 

ተቃዋሚዎች ፖል ቢያ አሸናፊ የተደረጉበትን ምርጫ ህገ መንግስታዊ ጠለፋ ነው ሲሉ እየጠሩት መሆኑን መረጃው አስታውሷል፡፡

 

 

ሩሲያ የአሜሪካ የወረራ ስጋት ተጋርጦብኛል ለትምትለው የደቡብ አሜሪካዋ አገር ቬኒዙዌላ ዘመን አፈራሽ ሚሳየሎችን እንደምታስታጥቅ ፍንጭ ሰጠች፡፡

 

ሩሲያ ለቬኒዙዌላ ታስጣትቃቸዋለች ከተባሉት ዘመን አፈራሽ ሚሳየሎች መካከል አዲስ ስሪቱ ኦሪሺኒክ ሚሳየል እንደሚገኝበት ዘ ቴሌግራፍ ፅፏል፡፡

 

ኦሪሽነክ የኒኩሊየር ርዕሰ ጦር የሚገጠምለት እና ከድምፅ በላይ የሚምዘገዘግ ነው ተብሏል፡፡

 

ለየትኛውም የሚሳየል መከላከያ የማይበገር መሆኑም ተነግሮለታል፡፡

 

ሩሲያ ሚሳየሉን ለቬኒዙዌላ ልታስታጥቃት እንደምትችል የአገሪቱ ፓርላማ የመከላከያ ኮሚቴ ምክትል  ሰብሳቢ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

 

የቬኒዙዌላው ፕሬዘዳንት ኒኮላስ ማዱሮ አሜሪካ በአደገኛ እፅ መከላከል ሽፋን ወረራ ልትፈፅምብን እየተሰናዳች ነው የሚል ክሳቸውን ደጋግመውታል፡፡

 

አሜሪካ ታላላቅ የጦር መርከቦቿን ወደ ቀጠናው እያስጠጋች መሆኑ ይነገራል፡፡

 

ቬኒዙዌላ አሜሪካ አምርራ በምትጠላቸው ግራ ክንፈኛ ፖለቲከኞች የምትተዳደር አገር ነች፡፡

 

 

በሱዳን የRSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በአራትዮሹ አደራዳሪዎች በቀረበው የተኩስ አቁም ሀሳብ ተስማምቻለሁ ማለቱ ተሰማ፡፡

 

የተኩስ አቁም ሀሳቡ አቅራቢዎች አሜሪካ ፣ ግብፅ ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ሳውዲ አረቢያ እንደሆኑ TRT ዎርልድ ፅፏል፡፡

 

የተኩስ አቁሙ ከሁሉም በላይ ሰብአዊ እርዳታን ለማቀለጣጠፍ የታለመ ነው ተብሏል፡፡

 

ቀደም ሲል የአሜሪካው የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሱዳን መንግስትም በተኩስ አቁም ሀሳቡ ተስምምቷል ብለው ነበር፡፡

 

ዘግይቶ እንደተሰማው ግን የሱዳን ጦር ሹሞች RSF ከሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ ለቅቆ ሲወጣ ብቻ ነው የተኩስ አቁም የምናደርገው ሲሉ ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡

 

ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉም ትጥቅ መፍታት አለበት ብለዋል፡፡ የሱዳን የጦር ሹሞች፡፡

 

የሱዳን መንግስት ጦር እና የRSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ሲዋጉ 2 አመት ከመንፈቅ ሆኗቸዋል፡፡

 

 

በፊሊፒንስ ከባድ ጉዳት ያደረሰው ካልማጂ የተሰኘው አውሎ ነፋስ ቬየትናምንም እየመታት ነው ተባለ፡፡

 

ካልማጂ በፊሊፒንስ 200 ያህል ሰዎችን ከገደለ እና መጠነ ሰፊ የንብረት ውድመት ካስከተለ በኋላ አሁን ደግሞ ቬየትናምን እያስጨነቃት መሆኑን ቢቢሲ ፅፏል፡፡

 

በቬየትናምም በጥቀቱ 5 ሰዎችን ገድሏል፡፡

 

ቬየትናም ከወዲሁ የነፍስ አድን እና የመልሶ ማቋቋሙን ተግባር እንዲረዱ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ወታደሮቿን ማሳለፏ ታውቋል፡፡

 

አውሎ ነፋሱ በጎርፍ እና በመሬት ናዳ ጭምር የታገዘ ነው ተብሏል፡፡

 

ጎርፉ ቤቶችን ማጥለቅለቅ እና ማፈራረስ መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

 

የአገሪቱ የአየር ሁኔታ ተከታታይ መስሪያ ቤት በብዙ አካባቢዎች መሰል አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል ተብሏል፡፡

 

በአገሪቱ የተወሰኑ ኤርፖርቶችም ለአደጋ ስጋት ቅነሳ እንዲዘጉ መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

 

የኔነህ ከበደ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page