እስራኤል በመላዋ ኢራን በአገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ቢሮዎች እና ፅህፈት ቤቶች በላይ ያነጣጠረ ታላቅ ድብደባ ፈፀምኩ አለች፡፡
- 2 hours ago
- 1 min read
የካቲት 25/2018
እስራኤል በመላዋ ኢራን በአገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ቢሮዎች እና ፅህፈት ቤቶች በላይ ያነጣጠረ ታላቅ ድብደባ ፈፀምኩ አለች፡፡
በሊባኖስ ድብደባ እየፈፀመች መሆኑን ቢቢሲ ፅፏል፡፡
የርዕሰ ከተማዋ ቤይሩት ደቡባዊ ክፍል ነዋሪዎችም አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች ተብሏል፡፡
እስራኤል እና አሜሪካ በጣምራ በኢራን ላይ ድብደባ መፈፀም ከጀመሩ ወዲህ የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሔዝቦላህ ወሰን አሻግሮ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን እየተኮሰ መሆኑ ይነገራል፡፡

የሊባኖሷ ርዕሰ ከተማ ቤይሩት ደቡባዊ ክፍል የሄዝቦላህ መሪዎች መናኽሪያ ነው ይባላል፡፡
ሔዝቦላህ የኢራን የጦር እና የፖለቲካ አጋር እንደሆነች መረጃው አስታውሷል፡፡
በሌላ መረጃ ሲሪላንካ አቅራቢያ የኢራን የጦር መርከብ መስመጡ ተሰምቷል፡፡
በኔፓን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች የሰጠመችው መርከብ ባሕረኞች በሕይወት መታደጋቸው ታውቋል፡፡
የኢራኗ የጦር መርከብ ኔፓል አቅራቢያ በምን ምክንያት ልትሰጥም እንደቻለች በዝርዝር የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

