ኢትዮጵያ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ አቅሟን ለማሳደግ ከፈረንሳይ ተቋም ጋር ውል አሰረች፡፡
- sheger1021fm
- 12 minutes ago
- 1 min read
ጥቅምት 25 2018
ኢትዮጵያ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ አቅሟን ለማሳደግ ከፈረንሳይ ተቋም ጋር ውል አሰረች፡፡
የመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ተጠቃሚዎች የሆኑት ኢንዱስትሪዎች መሆኑ የተነገረ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያስተዳድራቸው እና ከሚመራቸው መስመሮች አንዱ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ አቅምን ለማሳደግ የተፈራረመችው ከፈረንሣዩ 'ኤሊክቲሪሲቲ ደ ፍራንስ' (EDF) ጋር መሆኑን ሰምተናል፡፡
በሌላ በኩል አገልግሎቱ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግብዓቶች ከሚያመርት የኬንያ ኩባንያ ጋር ውይይት ማረጉን ተናግሯል፡፡
ተቋሙ ከኩባንያው ጋር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግብዓቶችን በኢትዮጵያ ማምረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየቱን የሰማን ሲሆን ለኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ የሚያገለግሉ ኬብሎችን፣ ኮንዳክተሮች፣ ምሰሶዎች፣ ስማርት ሜትሮችና ተያያዥ ግብዓቶች እንደሚያርት ተነግሮለታል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








