top of page


አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡
ሚያዝያ 7/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #አሜሪካ አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡ እስያዊቱ አገር የአሜሪካን እርምጃ አደገኛ ነው እንዳለችው አናዶሉ ፅፏል፡፡ ሀላፊነት የጎደለውም ስትል ጠርታዋለች፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአሜሪካ የባህር ወሽመጡን መዝጋት ውጥረቱን ይበልጥ የሚያባብስ ነው የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ለችግሩ መቃለል ዘላቂ እና አጠቃላይ የተኩስ አቁም የሚደረግበት መላ ቢፈለግ የተሻለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦቱን ችግር እያባባሰው መምጣቱ ይነገራል፡፡ አሜሪካ የባህር መተላለፊያ ወሽመጡን ከሰኞ ቀን 8 ሰዓት አንስቶ ዘግቼዋለሁ ማለቷን መረጃው አስታውሷል፡፡ #ናይጀር
Apr 151 min read


መጋቢት 28/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች
#ፍልስጤም የፍልስጤማውያኑ የጦር እና የፖለቲካ ድርጅት (ሐማስ) የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚፈፀመውን ጥቃት አቁሞ ጠቅልሎ ካልወጣ በስተቀር በጭራሽ ትጥቅ አልፈታም አለ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ሰርጥ የወደፊት ሰላም ቀደም ሲል ያቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች የሰላም እቅድ ሐማስ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈታ የሚጠይቅ መሆኑን ሬውተርስ አስታውሷል፡፡ የሐማስ የበላዮች በዚህ ጉዳይ ትናንት ከአደራዳሪዎቹ ጋር መመካከራቸው ተሰምቷል፡፡ ይሄን ተከትሎም የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ ቃል አቀባይ አቡ ኦባይዳ የእስራኤል ጦር ከመንፈቅ በፊት በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የጋዛ ሰርጥን ለቅቆ ካልወጣ በስተቀር በጭራሽ ትጥቅ አንፈታም ብለዋል፡፡ በጋዛ የወደፊት ዘላቂ ስለማለቱ የሐማስ ትጥቅ መፍታት ነገር በጣሙን አስቸጋሪው ጉዳይ እንደሆነ ይነገራል
Apr 62 min read


መጋቢት 22/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ጀርመን በጀርመን ከሚኖሩ ስደተኞች 80 በመቶዎቹ ወደ አገራቸው እንደሚሸኙ መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ ሜርዝ ተናገሩ፡፡ ሶሪያውያኑ ስደተኞች በመጪዎቹ 3 አመታት ከጀርመን ወደ አገራቸው ይሸኛሉ መባሉን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ መራሄ መንግስት ሜርዝ 80 በመቶዎቹ ሶሪያውያን ስደተኞች በ3 አመታት ጊዜ ወደ አገራቸው እንደሚሸኙ እወቁልን ያሉት ከሶሪያው ጊዜያዊ ርዕሰ ብሔር አህመድ አልሻራ ጋር በበርሊን ከተነጋገሩ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ ብዙዎቹ ሶሪያውያን ስደተኞች ጀርመን የገቡት በአገራቸው ተቀስቅሶ የነበረው ውስብስብ የእርስ በርስ ጦርነት በተፋፋመበት ወቅት ነበር፡፡ አሁን ስደተኞቹን ከጀርመን መመለስ ይጀመራል ቢባልም ዝርዝሩ ገና አልታወቀም፡፡ ሶሪያ በአሁኑ ወቅት ከ10 ዓመት በፊት ከነበረው በእጅጉ የተሻለ ፀጥታ እንደሚስተዋልባት መረጃው አስታውሷል፡፡ #አሜሪካ አ
Mar 312 min read


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡
መጋቢት 21/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡ የካርግ ደሴት የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት ማምረቻ እና ለውጭ ገበያ ከታለመው ነዳጅ 90 በመቶው የሚላከው ከዚሁ ደሴት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ከወር በላይ ባስቆጠረው የኢራን ጦርነት ምክንያት በአለም ዙሪያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በጣሙን እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ ኢራን በኢስፍሐን ዩኒቨርስቲ ላይ ለተፈፀመባት ጥቃት በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው አገሮች በሚገኙ የአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የአፀፋ ጥቃት እንደምታደርስ ዝታለች፡፡ ኢራን በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል የኢንዱስትሪዎች መገኛ ላይ በፈፀመችው የሚሳየል ድብደባ ከባድ ቃጠሎ መድረሱ ታውቋል፡፡
Mar 302 min read


የታይዋኗ ርዕሠ ከተማ ታይፔ የቀድሞ ከንቲባ በጉቦ ቅሌት የ17 አመታት የእስር ቅጣት ተከናነቡ፡፡
መጋቢት 18/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ታይዋን የታይዋኗ ርዕሠ ከተማ ታይፔ የቀድሞ ከንቲባ በጉቦ ቅሌት የ17 አመታት የእስር ቅጣት ተከናነቡ፡፡ ኮ ዌን ጄ የተባሉት የታይፔ የቀድሞ ከንቲባ ለ17 አመታት እስር ቅጣት የተዳረጉት የ532 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የምንዛሪ ግምት ያለው ገንዘብ በጉቦ መቀበላቸው ተረጋግጦባቸው እንደሆነ AFP ፅፏል፡፡ በተሰጣቸው ጉቦ ለውጥ ለሪል ስቴት አልሚዎች ከተፈቀደላቸው በላይ ሰፊ መሬት መምራታቸው ታውቋል፡፡ ግለሰቡ በጠበቆቻቸው አማካይነት ይግባኝ መጠየቃቸው ተጠቅሷል፡፡ ጉዳያቸው በይግባኝ እስኪታይም በዋስ ሆነው ውጤቱን ይጠባበቃሉ ተብሏል፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በሰላሙ ጉዳይ ያለ አንዳች ማንገራገር ካልተስማማች ከእስካሁኑም የከፋ ከባድ ድብደባ ይጠብቃታል ሲሉ
Mar 273 min read


መጋቢት 16/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ኢራን ለኢራን ጠቅላይ የደህንነት ምክር ቤት አዲስ የበላይ ተሰየሙ፡፡ የምክር ቤቱ የበላይ ሆነው የተሰየሙት ሞሐመድ ባጌር ዘልግ ሐድር እንደሆኑ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ የቀድሞው የምክር ቤቱ የበላይ ዓሊ ላርጃኒ ባለፈው ሳምንት በእስራኤል ጥቃት መገደላቸው ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ላርጃኒን ተከትሎም የቀድሞው የደህንነት ሚኒስትርም ተገድለዋል፡፡ ከ3 ሳምንታት በላይ ባስቆጠረው ጦርነት የቀድሞው ጠቅላይ መሪ አሙያቶላህ ዓሊ ሐሚኒን ጨምሮ በርካታ ሹሞች መገደላቸው ይነገራል፡፡ በጦርነቱ በአገሪቱ ከ1300 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡ ኢራንም በእስራኤል እና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች በሚገኙባቸው የአረብ አገሮች የአፀፋ የሚሳየል እና የድሮን ጥቃት እየሰነዘረች መሆኑን መረጃው አስታውሷል፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጦርነቱ ማብቂያ
Mar 252 min read


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን የአየር እና የባህር ሀይሎች እንዳልነበሩ አድርገን አውድመናቸዋል አሉ፡፡
የካቲት 25/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን የአየር እና የባህር ሀይሎች እንዳልነበሩ አድርገን አውድመናቸዋል አሉ፡፡ ትራምፕ የኢራንን የአየር እና የባህር ሀይሎች እንዳልነበሩ አድርገን ደምስሰናቸዋል ያሉት በዋይት ሐውስ ከጀርመኑ መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ከተመካከሩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢራን የባህር እና የአየር ሀይል እንዳይኖራት ማድረጋቸው ትራምፕ ተናግረዋል፡፡ አሜሪካ እና እስራኤል ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ አንስቶ በጣምራ በኢራን ላይ ከባድ ድብደባ እየፈፀሙ ነው፡፡ ቢቢሲ እንደፃፈው ትራምፕ የኢራንን የጦር አቅም አነካክቼዋለሁ ቢሉም ፋርሳዊቱ አገር በእስራኤል እና በቀጠናው በሚገኙ የአሜሪካ ተቋሞች ላይ የአፀፋ ጥ
Mar 42 min read


የአሜሪካ ግዛቶችን የመታው ማዕበል የቀላቀለ ከፍተኛ የበረዶ ክምር ከ5 ሺህ በላይ በረራዎች እንዲሰረዙ ማድረጉ ተነገረ።
የካቲት 17/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ ኒውዮርክን ጨምሮ የአሜሪካ ግዛቶችን የመታው ማዕበል የቀላቀለ ከፍተኛ የበረዶ ክምር ከ5 ሺህ በላይ በረራዎች እንዲሰረዙ ማድረጉ ተነገረ። ሄርናንዶ በተሰኘው ማዕበል እንደ ኒውዮርክ፣ኒውጀርሲ እና ማሳቹሴትስ ያሉት ግዛቶች በከፍተኛ ደረጃ መጠቃታቸው ተነግሯል። በአንዳንድ አካባቢዎች የበረዶ ክምሩ ከ55ሴንቲ ሜትር በላይ ከፍታ ያለው መሆኑም ተነግሯል። በከባድ ነፋስ በታጀበው የበረዶ ክምር ከ40 ሚሊየን በላይ ህዝብ በቤት ውስጥ ተገድቦ ውሎ ለማደር መገደዱም ተሰምቷል። በከፍተኛው የበረዶ ክምርና ነፋስ ምክንያት በውሃ ዳርቻ አካባቢ ባሉ ከተሞች የጎርፍ ስጋት እንዳይኖርም አስግቷል ተብሏል። የሚበዙት ግዛቶችም በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ለመቆየት ተገደዋል ሲል ፒ.ቢ.ኤስ የወሬ ምንጭ ዘግቧል። ከባድ የ
Feb 242 min read


አሜሪካ የመርከብ ላይ ሆስፒታሏን ወደ ግሪንላንድ ደሴት ለመላክ መወጠኗን ዴንማርክ ውድቅ አደረገችው፡፡
የካቲት 16/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ አሜሪካ የመርከብ ላይ ሆስፒታሏን ወደ ግሪንላንድ ደሴት ለመላክ መወጠኗን ዴንማርክ ውድቅ አደረገችው፡፡ ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመርከብ ላይ ሆስፒታሉን ወደ ግሪንላንድ ለመላክ መወጠናቸውን በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እወቁልኝ ማለታቸውን AFP አስታውሷል፡፡ የዴንማርኩ የመከላከያ ሚኒስትር ግሪንላንድ ይሄ ዓይነቱ የአሜሪካ የጤና ድጋፍ አያሻትም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የአርክቲክ ክበቧ የአለማችን ታላቋ ደሴት ግሪንላንድ የአውሮፓዊቱ ዴንማርክ የራስ ገዝ ግዛት ነች፡፡ ትራምፕ ለአሜሪካ ደህንነት በእጅጉ አስፈላጊ በመሆኗ ከአሜሪካ ጋር መዋሐድ ይኖርበታል ሲሉ ቆይተዋል፡፡ የትራምፕ ውጥን ከዴንማርክም ሆነ ከግሪንላንዳውያ በኩል ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳ
Feb 232 min read


ሜታ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የአውስትራሊያ አዳጊ ወጣቶችን ገፆቹን እንዳይጠቀሙ አደረጋቸው፡፡
ጥር 5/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አውስትራሊያ የእነ ፌስ ቡክ እና ኢኒስታግራም የማህበራዊ ድረ ገፆች እናት ኩባንያ (ሜታ) ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የአውስትራሊያ አዳጊ ወጣቶችን ገፆቹን እንዳይጠቀሙ አደረጋቸው፡፡ ክልከላው በአውስትራሊያ ስራ ላይ የዋለውን ህግ መሰረት ያደረገ መሆኑን ABC ፅፏል፡፡ አዲሱ የአውስትራሊያ ህግ እድሜያቸው ከ16 አመታት በታች የሆነ አዳጊ ወጣቶች በጭራሸ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዳይገለገሉ የሚከለክል ነው፡፡ አዳጊ ወጣቶች ክልከላውን ተላልፈው የማህበራዊ ትስስር ገፆቹን ሲገለገሉ ከተገኙ አገልግሎት አቅራቢያ ኩባንያዎች የገንዘብ ቅጣት እንዲቆነደዱ ያደርጋል፡፡ አዳጊ ወጣቶችን የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዳይገለገሉ በማድረግ አውስትራሊያ ቀዳሚዋ አገር ሆናለች፡፡ #ሶማሊያ የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት ከተባበ
Jan 132 min read


የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ያሰኛጋል አሉ፡፡
ጥር 1/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ኮሎምቢያ የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ያሰኛጋል አሉ፡፡ ጉስታቮ ፔትሮ በአሜሪካ የጦር ጣልቃ ገብነት ስጋት ገብቶኛል ያሉት ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት አሜሪካ በቬኔዙዌላ ላይ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ የአገሪቱን ፕሬዘዳንት ኒኮላስ ማዱሮን አሳግታ ወደ ኒውዮርክ ማስወሰዷ ይታወቃል፡፡ ከዚያ ወዲህ በርካታ አገሮች በአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ክፉኛ ስጋት እንደገባቸው ይነገራል፡፡ በአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ስጋት ገብቶኛል የሚሉት የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የዋይት ሐውስን አስተዳደር በግላጭ በመንቀር ይታወቃሉ፡፡ ትራምፕ እንደ ቬኔዙዌላ ሁሉ በኮሎምቢያም ላይ ሲዝቱ መቆየታቸው መረጃው አስታውሷል፡፡ #ሶማሊያ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ሹሞቹ
Jan 92 min read


ታህሳስ 10/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
ታህሳስ 10/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ አሜሪካ በተጨማሪ ሁለት አለም አቀፉ የወንጀል ችሎት (ICC) ዳኞቹ ላይ ማዕቀወብ ጣለችባቸው፡፡ ዳኞቹ ለአሜሪካ ማዕቀብ የተዳረጉት ችሎቱ እስራኤል በጋዛ ዘመቻዋ ፈፅማዋለች የተባለውን የጦር ወንጀል መመርመሩን እንዲያቆም ያቀረበችውን መሟገቻ ውድቅ በማድጋቸው ምክንያት እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ ችሎቱ ቀደም ሲል በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና በቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም የተነሳ አሜሪካ በበርካታ የICC ዳኞች እና አቃቢያነ ህግ ላይ ማእቀብ እያከታተለችባቸው ነው፡፡ የአሜሪካ ጦር ባልደረቦች በአፍጋኒስታን አድርሰውታል የተባለን የጦር ወንጀል ለመመርመር የተነሱ የICC ባልደሮችም ለማዕቀብ መዳረጋቸው
Dec 19, 20252 min read


ህዳር 16 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ቻይና የቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ጂን ፒንግ ታይዋን ከእናት አገሯ ጋር መቀላቀሏ በአሁኑ ወቅት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው አሉ፡፡ ሺ ጂን ፒንግ ስለዚሁ ጉዳይ በስልክ ለአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ እንደነገሯቸው የቻይና መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ማውራታቸው አናዶሉ ፅፏል፡፡ ታይዋን ራሴን የቻልኩ ነፃ አገር ነኝ ብትልም ቻይና ግን ታይዋንን እንዳፈነገጠች የገዛ ግዛቷ አድርጋ ትቆጥራታለች፡፡ የቻይና መንግስት እና አድራጊ ፈጣሪው የቻይና ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር ቀደም ሲል ታይዋን በዚያም ሆነ በዚህ መልሳ የቻይና አካል መሆኗ አይቀርም ሲሉ ቆይተዋል፡፡ በአዲሱ የቻይና ፕሬዘዳንት የታይዋን አቋም የአሜሪካ ይፋዊ አስተያየት ምን እንደሆነ አልተሰማም፡፡ ቻይና ቀደም ሲል በታይዋን ዙሪያ ገባ ታላላቅ የጦር ልምምዶችን ማድረጓን መረጃው አስታውሷል፡፡ #አ
Nov 25, 20251 min read


ህዳር 15 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ናይጄርያ ከናይጄርያዋ ኒጀር ግዛት የአንድ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ከታገቱት ከ300 በላይ ተማሪዎች መካከል ሃምሳው ከአጋቶቻቸው ማምለጣቸው ተሰምቷል፡፡ ጉዳዩን የሚከታተለው ቡድን 50ው ተማሪዎች ከአጋቾቻቸው ማምለጣቸውን አረጋግጫለሁ ማለቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ይሁንና በምን ሁኔታ እና ከየት እንዳመለጡ አላብራራም፡፡ አምላጮቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል ማለቱ ተሰምቷል፡፡ የናይጀሪያ የፀጥታ ሀይሎች ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በተቀናጀ አሰሳ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያም በኬቢ ግዛት ከሚገኝ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት 20 ተማሪዎች ታግተው መወሰዳቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡ እገታውን በመስጋት ብዙዎቹ የናይጀሪያ ግዛቶች ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ማድረጋቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ #ሳውዲ_አረቢያ ሳውዲ አረቢያ በ1
Nov 24, 20252 min read


ህዳር 9 2018 -የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው ለሳውዲ አረቢያ ዘመን አፈራሾቹን F 35 የጦር ጄቶች እንደምትሸጥ ፍንጭ ሰጡ፡፡ ቀደም ሲል አሜሪካ F 35 የጦር ጄቶች በአረብ አገሮች እጅ እንዲገቡ ፍላጎት እንዳልነበራት አልጀዚራ ፅፏል፡፡ አሁን ግን ትራምፕ ለሳውዲ F 35 የጦር ጄቶችን እንሸጥላታለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ሳውዲዎች ታላቅ አጋሮቻችን ናቸው ይሄንንም እናደርገዋለን ብለዋል ትራምፕ፡፡ ትራምፕ የአብርሃም ስምምነቶች በሚሰኘው ማዕቀፍ ሳውዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንድትመሰርትላቸው ይሻሉ ተብሏል፡፡ ሳውዲ አረቢያ ግን ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመመስረቴ አስቀድሞ የፍልስጤማውያን ነፃ መንግስት በሚቋቋምበት መላ አስተማማኝ ዋስትና ማግኘት እሻለሁ እያለች ነው፡፡ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሳውዲው
Nov 18, 20252 min read


ህዳር 1 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ስሎቫኪያ በአውሮፓ አገሮች ታግዶ የሚገኘው የሩሲያ ገንዘብ ለዩክሬይን በብድር የመሰጠቱ ሀሳብ ከስሎቫኪያ በኩል ጠንካራ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ በአውሮፓ ህብረት ዘንድ ታግዶ ከሚገኘው የሩሲያ ገንዘብ 140 ቢሊዮን ዩሮው ለዩክሬይን የጦር መደገፊያ በብድር እንዲሰጣት ምክር ከተያዘ መቆየቱን አናዶሉ አስታውሷል፡፡ የስሎቫኪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ ግን እኛ የዚህ ውጥን አካል አይደለንም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚህ ይልቅ ለዩክሬይኑ ጦርነት ማብቃት ጥረቱ ቢበረታ ይሻላል ብለዋል ፊኮ፡፡ የታገደው የሩሲያ ገንዘብ ለዩክሬይን የጦር መደገፊያነት በብድር በሚሰጥበት መላ በአውሮፓ ህብረት መድረክ በመጪው ወር በታላቁ እንደሚመከርበት ታውቋል፡፡ ገንዘቡ ለዩክሬይን በብድር እንዲፈቀድላት የሁሉንም የህብረቱ አባል አገሮች ሙሉ ስምምነት እንደሚሻ ተ
Nov 10, 20252 min read


ጥቅምት 29 2018 - ጥቅምት 29 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የቡድን 20 አባል አገሮች ጉባኤ አይገኝም አሉ፡፡ የአሜሪካውፕሬዘዳንት አፍሪካ ነርስ በተሰኙት ነጭ ደቡብ አፍሪካዊያን ላይ እልቂት እና ማሳደዱ በርትቶባቸዋል የሚል ክሳቸውን እየደጋገሙት መሆኑን አናዶሉ አስታውሷል፡፡ የፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ መንግስት በትራምፕ የሚቀርበውን ውንጀላ በተደጋጋሚ እያስተባበለ ነው፡፡ ትራምፕ ግን የደቡብ አፍሪካን መንግስት ጥምድ አድርገው እንደያዙት ነው፡፡ እንደውም ደቡብ አፍሪካ ከቡድን 20 አባል አገርነቷ ልትባረር ይገባል ያሉት ሰሞኑን ነው፡፡ የቡድን 20 አባል አገሮች ስብሰባ በደቡብ አፍሪካ ቢካሄድም ያለ አሜሪካ ተሳትፎ ይሆናል ተብሏል፡፡ #ማሊ በምዕራብ አፍሪካዊቱ ሀገር ማሊ
Nov 8, 20251 min read


ጥቅምት 26 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#እስራኤል የእስራኤሉ የኢነርጂ እና የመሰረተ ልማት ሚኒስትር ኤሊ ኮኸን ወደ ጋዛው ጦርነት መመለሳችን አይቀርም አሉ፡፡ ዔሊ ኮኸን በጋዛ ወደ ጠንካራው ድብደባችን ለመመለስ የምንጠብቀው የሟች ታጋቾችን አስከሬን በሙሉ መረከብ ብቻ ነው ሲሉ ለአገራቸው ቻናል 7 ቴሌቪዥን መናገራቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ባቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች የሰላም እቅድ በጋዛ አልፎ አልፎ ቢጣስም የተኩስ አቁም ስራ ላይ ውሏል፡፡ እቅዱ የተኩስ አቁሙን መዝለቅ የሚከታተል አለም አቀፍ አረጋጊ ሀይል በጋዛ እንዲሰፍር ይጠይቃል፡፡ ዔሊ ኮኸን ግን አለም አቀፍ ሀይል ቢሰፍር እንኳ ሐማስን ትጥቅ ማስፈታቱ አይሆንለትም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የአገራቸው ጦር ግን ወደ ጋዛው ዘመቻ ተመልሶ ሐማስን ትጥቅ ማስፈታቱን በብቃት ማሳካት ይችላ
Nov 5, 20252 min read


ጥቅምት 17 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ቱርክ በቱርክ PKK የተሰኘው የኩርዶች የቀድሞ አማጺ ቡድን ታጣቂዎቹን ከቱርክ ወደ ኢራቅ ማስወጣት ጀመረ፡፡ PKK ታጣቂዎቹን ወደ ኢራቅ ማስወጣት የጀመረው ከቱርክ መንግስት ጋር በጀመረው የሰላም ሒደት መሰረት እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ የኩርዶቹ ታጣቂ ቡድን ከእንግዲህ የትጥቅ አመፅ እርም ይሁንብኝ ያለው ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ በትጥቅ መፍታት ሒደት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ PKK ታጣቂነቱን ትቶ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ብቻ የመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ተጠቅሷል፡፡ ቡድኑ ለወሰደው እርምጃ አስተማማኝነት የቱርክ መንግስት PKK ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ማህበርነት የሚለወጥበትን ሁኔታ እንዲያመቻችለት መጠየቁ ተሰምቷል፡፡ PKK የትጥቅ አመፅ እርም ይሁንብኝ ያለው ከ40 አመታት በኋላ እንደሆነ መረጃው አስታውሷ
Oct 27, 20252 min read


ጥቅምት 13 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ሱዳን በሱዳን የRSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከአገሪቱ ኤርፖርቶች የሚነሱ እና በኤርፖቶቹ የሚያርፉ አውሮፕላኖችን በሙሉ አወድማለሁ ሲል ዛተ፡፡ ዛቻውን ያሰሙ የፈጥኖ ደራሹ ሀይሉ አዛዥ ሌተና ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ እንደሆኑ ሱዳንስ ፖስት ፅፏል፡፡ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ትናንት ወደ አገልግሎት ተመልሷል በተባለው የካርቱም ኤርፖርት ላይ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ሰንዝሯል ተብሏል፡፡ የካርቱም ኤርፖርት ትናንት ከ2 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ በረራ አውሮፕላን ማስተናገዱ ታውቋል፡፡ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ከሱዳን መንግስት ጦር ጋር ሲዋጋ ከ2 ዓመታት ከመንፈቅ በላይ ሆኖታል፡፡ ጦርነቱን ማቆሚያ አንዳችም ፍንጭ አይታይም፡፡ #አሜሪካ በአሜሪካ በሁለት የሩሲያ ታላላቅ የነዳጅ ኩባንያዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ማዕቀብ ጣለች፡፡ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ሮስ
Oct 23, 20252 min read


ጥቅምት 12 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ካሜሩን በካሜሩን ከሳምንት በፊት በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አረጋዊው የአገሪቱ መሪ ፖል ቢያ እንዳሸነፉ የቅድሚያ ውጤቱ አሳየ ተባለ፡፡ የአገሪቱ የምርጫ አከናዋኝ መስሪያ ቤት በቅድሚያ ውጤቱ ፖል ቢያ ለፕሬዘዳንታው ምርጫው ከተሰጠው ድምፅ 53 በመቶውን በማግኘት አሸንፈዋል ማለቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ የፖል ቢያ የቅርብ ተፎካካሪ ኢሳ ቺሮማ ባካሪ ያገኙት ድምፅ 35 በመቶ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ባካሪ ከምርጫው በኋላ በተደጋጋሚ አሸንፌያለሁ ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ ኢሣ ቺሮማ ባካሪ ውጤቱ በወጉ ይጣራልኝ ማለት መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡ የ92 አመቱ አረጋዊ ፖል ቢያ የምርጫ ድላቸው ከፀናላቸው የ42 አመታት መሪነታቸውን በመ5 ዓመታት ይጨምርላቸዋል ተብሏል፡፡ የአገሪቱ ህገ መንግስታዊ ምክር ቤት ይፋዊ ውጤቱን ሰሞኑን እወቁት እንደሚል በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
Oct 22, 20252 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

