top of page

የአሜሪካ ግዛቶችን የመታው ማዕበል የቀላቀለ ከፍተኛ የበረዶ ክምር ከ5 ሺህ በላይ በረራዎች እንዲሰረዙ ማድረጉ ተነገረ።

  • Feb 24
  • 2 min read

የካቲት 17/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች



ኒውዮርክን ጨምሮ የአሜሪካ ግዛቶችን የመታው ማዕበል የቀላቀለ ከፍተኛ የበረዶ ክምር ከ5 ሺህ በላይ በረራዎች እንዲሰረዙ ማድረጉ ተነገረ።


ሄርናንዶ በተሰኘው ማዕበል እንደ ኒውዮርክ፣ኒውጀርሲ እና ማሳቹሴትስ ያሉት ግዛቶች በከፍተኛ ደረጃ መጠቃታቸው ተነግሯል።


በአንዳንድ አካባቢዎች የበረዶ ክምሩ ከ55ሴንቲ ሜትር በላይ ከፍታ ያለው መሆኑም ተነግሯል።


በከባድ ነፋስ በታጀበው የበረዶ ክምር ከ40 ሚሊየን በላይ ህዝብ በቤት ውስጥ ተገድቦ ውሎ ለማደር መገደዱም ተሰምቷል።


በከፍተኛው የበረዶ ክምርና ነፋስ ምክንያት በውሃ ዳርቻ አካባቢ ባሉ ከተሞች የጎርፍ ስጋት እንዳይኖርም አስግቷል ተብሏል።


የሚበዙት ግዛቶችም በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ለመቆየት ተገደዋል ሲል ፒ.ቢ.ኤስ የወሬ ምንጭ ዘግቧል።


ከባድ የአየር ሁኔታው ከ670 ሺህ በላይ ቤቶች ከመብራት ተራርቀው በጨለማ እንዲያሰሰልፉ ማድረጉም ተነግሯል።


ለብዙዎቹ አካባቢዎች ክስተቱ በረጅም ዓመት አይተው የማያውቁት እንደሆነባቸውም ተወርቷል።



በሜክሲኮ በተቀሰቀሰ ረብሻ ከ25 በላይ የሜክሲኮ ብሔራዊ ዘብ አባላት መገደላቸው ተነገረ።


በሜክሲኮ ድብልቅልቋን ያወጣው ነውጥ የተቀሰቀሰው ኤል-ሜንቾ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የአደገኛ የወንጀል ቡድን መሪ መገደልን ተከትሎ ነው ተብሏል።


የአደገኛ እፅ አዘዋዋሪው የወንጀል ቡድን መሪ መገደልን ተከትሎ የሜክሲኮ የሚበዙት ግዛቶች በረብሻ እየተናጡ መሆኑን ቢቢሲ አውርቷል።


ኔሜሲዮ ኦሴጉኤራ ካርቫንቴ ወይንም በቅፅል ስሙ ኤል-ሜንቾ ከትናንት በስቲያ እሁድ የሜክሲኮ ልዩ ሃይል በወሰደው እርምጃ ቆስሎ መያዙ ተነግሯል።


ለህክምና በጉዞ ላይ እንዳለም ህይወቱ ማለፉ መነገሩ ይታወሳል።


የወሬ ምንጩ እንደዘገበው ከጥቃቱ በውሃላ ከ20 በላይ የሜክሲኮ ግዛቶች ከፍተኛ ረብሻ ውስጥ ገብተዋል ተሽከርካሪዎችም በእሳት ሲጋዩ ውለዋል።


ከ25 በላይ የሜክሲኮ ብሔራዊ ዘብ አባላት መገደላቸውም ተነግሯል።


ኤል-ሜንቾ የሚመራው ሲ.ጄ.ኤን.ጂ የተሰኘው የወንጀል ቡድን በሜሲኮ እጅግ ከሚፈሩት ውስጥ መሆኑ ይነገራል።


የኤል-ሜንቾን ግድያ ተከትሎ የተቀሰቀሰው ረብሻ አሁንም አለመብረዱ ተነግሯል።



ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በውሃላ እጅግ የከፋው የተባለው የሩሲያ ዩክሬይን ጦርነት ዛሬ አራተኛ ዓመቱን ደፍኗል።


ጦርነቱ ምንም አይነት የመቆም ምልክት አይትይበትም።


ከሁለቱም ሀገሮች በኩል የሚወጣው መረጃ የተለያየ ቢሆንም ከሁለቱም ወገን ግን በጦርነቱ የመቶ ሺዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።


ዓለም አቀፉ የስትራቴጂክ ጥናት ተቋም ባወጣው መረጃ በሩሲያ በኩል ከ325ሺህ በላይ በዩክሬይን በኩል ከ140ሺህ በላይ በጦርነቱ ህይወታቸው አልፏል ብሏል።


ከሁለቱም ወገን ወደ አምስተኛ ዓመቱ በተሻገረው ጦርነት ከ1.8 ሚሊየን በላይ ህዝብ እስካሁን ሙትና ቁስለኛ መሆኑ ተነግሯል።


በጦርነቱ ከ5.9 ሚሊየን በላይ ዩክሬናዊያን ቀያቸውን ጥለው መሰደዳቸውንም ፒ.ቢ.ኤስ የመረጃ ምንጭ ዘግቧል።


የቅርብ ጊዜውን የጄኔቫውን ጨምሮ ለጦርነቱ እልባት ለመስጠት የተለያየ የማሸማገል ሙከራ ቢደረግም አውዳሚው ጦርነት ግን ያለ አንዳች መፍትሄ ወደ አምስተኛ ዓመቱ ተሸጋግሯል።



አሜሪካ አሳግታ የወሰደቻቸውን የቀድሞውን የቬንዙዌላ ፕሬዘዳንት ኒኮላስ ማዱሮና ባለቤታቸውን ባስቸኳይ መልቀቅ አለባት ተባለ።


አሜሪካ የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ኒኮላስ ማዱሮንና ባለቤታቸውን ሴሊያ ፍሎሬስን መልቀቅ አለባት ያሉት የሀገሬው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዪቫን ጊል ናቸው።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ፊት ባደረጉት ንግግር የቀድሞውን ፕሬዘዳንት መለቀቅ ጠይቀዋል።


አሜሪካ አሳግታ ወስዳ በእስር እንዲቆዩ ያደረገቻቸውን ማድሮና ባለቤታቸውን መልቀቅ አለባት ማለታቸውን አልጀዚራ አውርቷል።


አሜሪካ ታህሳስ 25 ቀን ድንገት በወሰደችው እርምጃ የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ኒኮላስ ማዱሮንና ባለቤታቸውን ወደ ኒውዮርክ መውሰዷ የሚታወስ ነው።


በእስር ላይ ሆነውም ከአደገኛ እፅ ዝውውር ጋር በተገናኘ የሚመሰረትባቸውን የክስ ሂደት እየተጠባበቁ መሆኑ ተነግሯል።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግን የአሜሪካን እርምጃ ምንም ተጨባጭ ያልሆነ ፖለቲካዊ ተልእኮ ነው ማለታቸው ተወርቷል።


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page