top of page

አሜሪካ የመርከብ ላይ ሆስፒታሏን ወደ ግሪንላንድ ደሴት ለመላክ መወጠኗን ዴንማርክ ውድቅ አደረገችው፡፡

  • Feb 23
  • 2 min read

የካቲት 16/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች



አሜሪካ የመርከብ ላይ ሆስፒታሏን ወደ ግሪንላንድ ደሴት ለመላክ መወጠኗን ዴንማርክ ውድቅ አደረገችው፡፡


ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመርከብ ላይ ሆስፒታሉን ወደ ግሪንላንድ ለመላክ መወጠናቸውን በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እወቁልኝ ማለታቸውን AFP አስታውሷል፡፡


የዴንማርኩ የመከላከያ ሚኒስትር ግሪንላንድ ይሄ ዓይነቱ የአሜሪካ የጤና ድጋፍ አያሻትም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡



የአርክቲክ ክበቧ የአለማችን ታላቋ ደሴት ግሪንላንድ የአውሮፓዊቱ ዴንማርክ የራስ ገዝ ግዛት ነች፡፡


ትራምፕ ለአሜሪካ ደህንነት በእጅጉ አስፈላጊ በመሆኗ ከአሜሪካ ጋር መዋሐድ ይኖርበታል ሲሉ ቆይተዋል፡፡


የትራምፕ ውጥን ከዴንማርክም ሆነ ከግሪንላንዳውያ በኩል ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ግን ግሪንላንድን የአሜሪካ አባል የማድረግ ውጥናቸውን የመተው ምልክት አላሳዩም፡፡



ዩጋንዳ የRSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል አዛዥ የሆኑትን ሌተና ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎን ተቀብላ ማስተናገዷ የሱዳንን ወታደራዊ መንግስት ክፉኛ አስቆጣው፡፡


የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ፣ ዩጋንዳ ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎን ማስተናገዷን በሱዳን ሕዝብ ላይ የተሰነዘረ ስድብ ያህል ቆጥሬዋለሁ ማለቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡


የዩጋንዳው ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ባለፈው ሳምንት አርብ የሱዳኑን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል አዛዝ ሌተና ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎን በኢንቴቤ ቤተ መንግስት ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል ተብሏል፡፡


ሙሴቬኒ ስለ ሰላም የሱዳኖቹን ተፋላሚዎች እንዲሸመግሉ በአፍሪካ ህብረት መሰየማቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡


የሱዳን መንግስት ጦር እና የRSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በጦርነት ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡


ጦርነቱ በአገሪቱ ሰብአዊ ቀውሱን እያነባበረ ያለ ሁነኛ መፍትሄ ወደ 3ኛ አመቱ እየተቃረበ ነው፡፡



በአሜሪካ ፍሎሪዳ በፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደሚተዳደረው የማራ ላጎ ቅጥር ለመዝለቅ የሞከረ ግለሰብ በፕሬዘዳንቱ ሚስጥራዊ የጥበቃ ክፍል (ሴክሬት ሰርቪስ) ባልደረቦች ተተኩሶበት ተገደለ ተባለ፡፡


ወደማራ ላጎ ቅጥር ለመዝለቅ ሲሞክር ተገደለ የተባለው በ20ዎቹ የእድሜ እርከን የሚገኝ ወጣት ሽጉጥ የታጠቀ እና በቆርቆሮ የተሞላ ተቀጣጣይ ቁስ የያዘ ነበር መባሉን አልጀዚራ ፅፏል፡፡


በአጋጣሚው ወቅት ፕሬዘዳንት ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ ነበሩ ተብሏል፡፡


ከቅርብ አመታት ወዲህ ትራምፕ ተደጋጋሚ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው ተጠቅሷል፡፡


ከአመት ተኩል በፊት በዚያው በማራ ላጎ በፕሬዘዳንቱ ላይ የግድያ ሙከራ አድርጎ የነበረ ግለሰብ በቅርቡ እድሜ ይፍታህ እንደተፈረደበት መረጃው አስታውሷል፡፡


የአሜሪካ ፌዴራል የምርመራ ቢሮ (FBI) የማራ ላጎውን አዲስ አጋጣሚ በዝርዝር እያጣራው ነው ተብሏል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን

 
 
 
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ።

ሐምሌ 23 2018 የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ። የአፍሪካ ሀገሮች እርስ በእርስ፣በአፍሪካና በሩሲያ እንዲሁም አፍሪካ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማሳደግን ዓለማው ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተባበሩት መንግስታት የአ

 
 
 

3 Comments


Cole Kelp
Cole Kelp
Jul 15

Helpful post, especially "አሜሪካ የመርከብ ላይ ሆስፒታሏን ወደ ግሪንላንድ ደሴት ለመላክ መወ". Related reference: Carpet Cleaning Simulator- trees game

Like

hannah1561990
Jun 16

Interesting development. remove bg ai It shows how sensitive sovereignty and military presence in the Arctic has become. Even humanitarian offers can carry political weight in regions like Greenland, so it makes sense Denmark is cautious about outside involvement.

Like

retrobowlgame.college
Feb 24

Retro Bowl College made me rethink recruiting when a late steal flipped my entire depth chart. One unexpected signing reshaped the season.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page