top of page

የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ያሰኛጋል አሉ፡፡

  • sheger1021fm
  • 4 hours ago
  • 2 min read

ጥር 1/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች



የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ያሰኛጋል አሉ፡፡


ጉስታቮ ፔትሮ በአሜሪካ የጦር ጣልቃ ገብነት ስጋት ገብቶኛል ያሉት ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው፡፡


ባለፈው ሳምንት አሜሪካ በቬኔዙዌላ ላይ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ የአገሪቱን ፕሬዘዳንት ኒኮላስ ማዱሮን አሳግታ ወደ ኒውዮርክ ማስወሰዷ ይታወቃል፡፡


ከዚያ ወዲህ በርካታ አገሮች በአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ክፉኛ ስጋት እንደገባቸው ይነገራል፡፡


በአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ስጋት ገብቶኛል የሚሉት የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የዋይት ሐውስን አስተዳደር በግላጭ በመንቀር ይታወቃሉ፡፡


ትራምፕ እንደ ቬኔዙዌላ ሁሉ በኮሎምቢያም ላይ ሲዝቱ መቆየታቸው መረጃው አስታውሷል፡፡



የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ሹሞቹ በሞቃዲሾ ከሚገኘው የአለም የምግብ ፕሮግራም መጋዘን የእርዳታ እህል ዘርፈዋል መባሉን አስተባበለ፡፡


የሶማሊያ የመንግስት ሹሞች መጋዘኑን ምንቅርቅሩን በማውጣት 76 ቶን እህል ዘርፈዋል የሚል ክስ ያቀረበው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡


የእርዳታ ምግቡ የአሜሪካም ድርሻ ያለበት ነው ተብሏል፡፡


በዚህ የተነሳም የአሜሪካ መንግስት ከእንግዲህ ለዚህ ዓይነቱ እርዳታ ሰባራ ሳንቲም አላወጣም ማለቱ ተሰምቷል፡፡


አሜሪካ ለሰብአዊ እርዳታ የምትሰጠውን ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሷ ይነገራል፡፡


ያም ሆኖ ባለፈው አመት 2 ቢሊዮን ዶላር መለገሷ ተጠቅሷል፡፡


የሶማሊያ መንግስት ሹሞቹ የእርዳታ እህል ዘርፈዋል መባሉን አስተባብሎ ጉዳዩን አጣራዋለሁ ማለቱን መረጃው አስታውሷል፡፡



የአሜሪካው ምክትል ፕሬዘዳንት ጄ ዲ ቫንስ ዴንማርክም ሆነች የተቀሩት አውሮፓውያን ለግሪንላንድ ደሴት መከላከያ የረባ ነገር እንዳላደረጉ ተናገሩ፡፡


ቫንስ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አሜሪካንም ሆነ ዓለማችንን እንደ ሩሲያ እና ቻይና ከመሳሰሉት አገሮች ጥቃት ለመጠበቅ ግሪንላንድ በእጅጉ አስፈላጊያችን ነች ብለዋል፡፡


የአሜሪካ ሹሞች በአርክቲክ ክበብ የምትገኘውን የግሪናልንድ ደሴት በዚም ሆነ በዚህ በዚህ በእጃችን ማስገባት አለብን ማለቱን ደጋግመውታል፡፡


ግሪንላንድ የአውሮፓዊቱ ዴንማርክ የራስ ገዝ አስተዳደር ነች፡፡


ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት ደሴቲቱን በጦር ሀይል ከመያዝ እንደማይመለሱ በተደጋጋሚ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡


ዴንማርክም ሆነች የግሪንላንድ ደሴት አስተዳደር በተደጋጋሚ የትራምፕን የጥቅለላ ውጥን እየተቃወሙት ነው፡፡


የዴንማርኳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን አሜሪካ ግሪንላንድን ከጠቀለለቻት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ ማብቂያው ይሆናሉ ሲሉ እያስጠነቀቁ ነው፡፡



የጋና የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ኬን ኦፎሪ አታ አሜሪካ ውስጥ ተይዘው ታሰሩ፡፡


የጋናው የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር አሜሪካ ውስጥ ተይዘው የታሰሩት በዚያ በጥገኝነት በሚኖሩበት ምክንያት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


የቀድሞው ሚኒስትር በአገራቸው ሹም በነበሩበት ወቅት የመንግስትን ገንዘብ በመመዝበር እና በማባከን ተጠያቂ ናቸው ተብለው እንደሚፈለጉ ተጠቅሷል፡፡


የጋና መንግስትም ቀደም ብሎ የቀድሞው የገንዘብ ሚኒስትር ተላልፈው እንዲሰጡት ለአሜሪካ ጥያቄ አቅርቦ ነበር ተብሏል፡፡


ኬን ኦፎሪ አታ ባለፈው አመት ወደ አሜሪካ ያቀኑት በህክምና ሰበብ እንደነበር ታውቋል፡፡


ግለሰቡ ለጋና ተላልፈው ይሰጡ አይሰጡ ለጊዜው የተብራራ ነገር የለም ተብሏል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Recent Posts

See All
 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ  እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡

ጥር 1/2018   የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ እራሳቸውን በገንዘብ  እንዲችሉ ያግዛል ተባለ፡፡   ይህም የሚሰጡት ስልጠና ጥራት እንዲኖረው ይረዳል ሲሉ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሙያ ጠቅሰዋል፡፡   ባለፈው አመት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ወጥቶ ወደ ስራ ገብቷል፡፡   ፖሊሲው ው

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page