top of page


ከተሞች ሲለሙ ያለፉበትን የረዥም ታሪክ አሻራ የሚያሳዩ የኪነ ህንፃና መሰል ቅርሶች እንዳይጠፉ ጥናትን እና ወይይትን መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡
ህዳር 30 2018 ከተሞች ሲለሙ ያለፉበትን የረዥም ታሪክ አሻራ የሚያሳዩ የኪነ ህንፃና መሰል ቅርሶች እንዳይጠፉ ጥናትን እና ወይይትን መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡ ጥያቄው የቀረበው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ75ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ልደታ በሚገኘው የቴክኖሎሎጂ እና ቢልት ኢንቫይሮመንት ኮሌጅ ‹‹በቅርስ ጥበቃ እና ጥናት ላይ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች›› በሚል መሪ ቃል ባሰናደው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ በቅርስ ጥበቃ እና ጥናት ላይ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች በሚል ርዕስ ጽሁፍ ያቀረቡት አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ ስለቅርስ ያለው አረዳድ ዝቅተኛ መሆን፣ የበቂ በለሞያ እጥረት እና መሰል ችግሮች ለዘርፉ እንቅፋት መሆናቸውን ዘርዝረዋል፡፡ የወይይቱ ተሳታፊዎች እና ባለሙያዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ፖለቲካ ለ
Dec 9, 20251 min read


ጉዳያችን - የከተማ ልማትና የመልሶ ግንባታ
ህዳር 29 2018 ጉዳያችን - የከተማ ልማትና የመልሶ ግንባታ የከተማ ልማትና የመልሶ ግንባታ ስራ ውስጥ መታሰብ ያለባቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው? በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የከተማ ፕላን መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ውብሸት ብርሃኑ(ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ የሰጡንን ማብራሪያ ለማድመጥ… ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw 🟦Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1 💬WhatsApp : https://whatsapp.com/chan
Dec 8, 20251 min read


ሕብረት ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከግብር በፊት የ749.04 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ፡፡
ህዳር 29 2018 ሕብረት ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከግብር በፊት የ749.04 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ፡፡ ባንኩ ይህን ያለው 28ኛውን የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው እለት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡ በጉባዔው ላይ የባንኩን ዓመታዊ ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ተሰማ የባንኩ ሀብት 113.93 ቢሊየን ብር መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ17.96 በመቶ ወይም የ17.35 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል። የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 92.68 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተጠቅሷል። ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ18.03 ቢሊዮን ብር ወይም የ24.16 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የቦርድ ሰብሳቢው አስረድተዋል፡፡ ከወለድ ነፃ ፋይናንስን ጨምሮ አጠቃላይ የባ
Dec 8, 20251 min read


ኢትዮጵያ በ10 ዓመት፤ ከተቻለም ከዚያ ባጠረ ጊዜ ውስጥ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ትገነባለች ተባለ።
ህዳር 29 2018 ኢትዮጵያ በ10 ዓመት፤ ከተቻለም ከዚያ ባጠረ ጊዜ ውስጥ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ትገነባለች ተባለ። ዛሬ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ዝግጅት፣የኒውክሊየር የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ መጀመር ይፋ ተደርጓል። በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንም ስራዬን መጀመሬን እወቁት ብሏል። የኒውክሊየር የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱን ለመገንባት ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ (አይ.ኤ.ኢ.ኤ) የሚያስቀምጣቸውን 19 መሠረታዊ የሆኑ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቃል ተብሏል። ኢትዮጵያም ይህንኑ መስፈርት አሟልታ በተቆጣጣሪ ኤጀንሲው እገዛና ክትትል ለመስራት ዝግጁ ነች ተብሏል። የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አብዱረዛቅ ዑመር ሲናገሩ እንደሰማነው የስራው ሂደት ሶስት ምዕራፎች ይ
Dec 8, 20251 min read


''ኢትዮጵያን የትኛውም ትንኮሣ ከጀመረችው የብልፅግና ጉዞ አያስቆማትም'' ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ህዳር 29 2018 ''ኢትዮጵያን የትኛውም ትንኮሣ ከጀመረችው የብልፅግና ጉዞ አያስቆማትም'' ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። የሚገጥመንን እያንዳንዱን ፈተና ወደ ዕድል በመቀየር የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን እናደርጋለንም ብለዋል። 20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው፡፡ በአከባበሩ ላይ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን መልዕክቶችም ተላልፈዋል። የዕለቱ የክብር እንግዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባደረጉት ንግግር በዓሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚደምቁበት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያውያን መተባበርን እና በአንድነት መቆምን የጋራ ሃብታችን እናድርግ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች የሚደነቁ ውጤቶችን
Dec 8, 20251 min read


ራሚስ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ ከ4.2 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናገረ።
ህዳር 29 2018 ራሚስ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ ከ4.2 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናገረ። ይህም በአንድ ዓመት ውስጥ የ85 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ሲል ባንኩ ትናንት ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ባወጣው ሪፖርት ተናግሯል። ራሚስ ባንክ በበጀት ዓመቱ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ በማስመዝገብ ወደ ትርፍ ተሸጋግሬያለሁም ብሏል። ገቢው በዓመቱ ውስጥ የ3,726 ከመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል። ራሚስ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰቡንም ጠቅሷል። የቅርንጫፎቹን ብዛት 47፣ የደንበኞቹ ብዛት ደግሞ 352,000 መድረሳቸው በሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል። ባንኩ በበጀት ዓመቱ ማገባደጃ ላይ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያንና የካርድ ባንኪንግ አገልግሎቶቹን ለደንበኞቹ ማስተዋወቁን እና የላቁ የዲጅታል ባንክ አማራጮችን እንደ ኢንተር
Dec 8, 20251 min read


የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በሚል ምክንያት ከሲዳማ ክልል ሃገረ ሰላም እስከ ዝዋይ ባቱ ድረስ ባለው መንገድ በርከት ያሉ ማደያዎች ቢኖሩም አንዳቸውም ናፍጣ የላቸውም።
ህዳር 29 2018 የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በሚል ምክንያት ከሲዳማ ክልል ሃገረ ሰላም እስከ ዝዋይ ባቱ ድረስ ባለው መንገድ በርከት ያሉ ማደያዎች ቢኖሩም አንዳቸውም ናፍጣ የላቸውም። በጄሪካን ግን ይሸጣል። በሲዳማ ክልል ሀገረ ሰላም እስከ ሀዋሳ ከተማ መግቢያ ድረስ፣ ከሃዋሳ እስከ ዝዋይ ባቱ ባሉ ማደያዎች የመኪና ናፍጣ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን ከቦታው ተመልክተናል። በእዚህ አካባቢ ስንዘዋወር እንደተመለከትነው ማደያዎች ውስጥ ነዳጅ የለም ቢባልም ማደያው አካባቢና ማደያዎች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች በጀሪካን ነዳጅ እንደሚሸጥ ሲናገሩና ሂሳብ ለማስማማት ሲሞክሩም አይተናል። በሲዳማ ክልል ሀገረ ሰላም ላይ ህዳር 27 ቀን 2018 በነበርንበት ወቅት ማደያዎች ውስጥ ናፍጣ የለም የሚል ተደጋጋሚ ምላሾች ቢሰጡንም እዚያው አካባቢ ያሉ ግለሰቦች ግን ናፍጣ በጀ
Dec 8, 20251 min read


በኢትዮጵያ በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች፤ የሚደርስባቸው የመብት ጥሰት ቀጥሏል ተብሏል፡፡
ህዳር 26 2018 በኢትዮጵያ በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች፤ የሚደርስባቸው የመብት ጥሰት ቀጥሏል ተብሏል፡፡ ይህ የተባለው ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (Forum For Social Studies) የተሰኘ ተቋም በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችን በተመለከተ እየሰራው ላለው ፕሮጀክት ከሚመለከታቸው አካላት ግብዓት ለመሰብሰብ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው፡፡ የፕሮጅክቱ ከዋኝ ብድን አባል የሆኑት ደግነት አበባው(ዶ/ር) በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች የበዙ ችግሮች እየገጠሟቸው እንደሆነ አንስተዋል፡፡ ከሀገሪቱ የዋጋ ንረት ጋር የማይጣጣም ክፍያ፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ያለመወሰን፣ እንዳይደራጁ መከልከል፣ ምቹ ያልሆነ የስራ ቦታን ጨምሮ ሌሎች ተደራራቢ ችግሮች
Dec 5, 20252 min read


''በሩብ ዓመቱ 3,319 የመድሀኒት እና የክትባት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርቶች ደርሰውኛል'' የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን
ህዳር 26 2018 በሩብ ዓመቱ 3,319 የመድሀኒት እና የክትባት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርቶች ደርሰውኛል ሲል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2018 ሩብ ዓመት፣ 723 የመድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርቶችን(ADE) እንዲሁም 2,596 የክትባት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርቶችን (AEFI) በድምሩ 3,319 ሪፖርቶች እንደሰበሰበ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም 15 አስከፊ የመድኃኒት ወይም የክትባት የጎንዮሽ ክስተት ሪፖርቶችን የማጣራት ስራ ሰርቻለሁም ብሏል፡፡ 257 አዳዲስ የህክምና መሳሪያዎች ሰነድ በመገምገም የገበያ ፈቃድ እንደሰጠም ተናግሯል፡፡ ለ13 ህክምና መሳሪያ አስመጪና አከፋፋይ ደግሞ የቅድመ ፈቃድ ኢንስፔክሽን አድርጎ የብቃት ማረጋገጫ እንደተሰጠም አስረድቷል፡፡ የህክም ሙከራ እንድካሄድ የተፈቀደላቸዉን ተቋማት ላ
Dec 5, 20251 min read


ትክክል ያልሆኑ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን እንዴት በህግ ተጠያቂ ማድረግ ይቻላል?
ህዳር 26 2018 ማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን በብዙ ሰዎች እንደ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ይታያሉ። ሁሉም ላይ ባይሆንም ታዲያ በእነዚህ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ ቅሬታዎች ይሰማሉ። መደበኛ መገናኛ ብዙሃን በብዙ ጥረት ያዘጋጁትን መረጃ የራሳቸው አድርገው ያቀርባሉ፣ ጫፍ ብቻ ይዘው ትክክል ያልሆኑ መረጃዎችንም ያሰራጫሉ በሚል ይወቀሳሉ። ለመሆኑ በዚህ አይነቱ ተግባር የሚሳተፉ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን እንዴት በህግ ተጠያቂ ማድረግ ይቻላል? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡...
Dec 5, 20251 min read


ሕብረት ኢንሹራንስ በ2017 በጀት ዓመት በታሪኬ ለመጀመሪያ ጊዜ በቢሊዮን የሚቆጠር ትርፍ አገኘሁ አለ።
ህዳር 26 2018 ሕብረት ኢንሹራንስ በ2017 በጀት ዓመት በታሪኬ ለመጀመሪያ ጊዜ በቢሊዮን የሚቆጠር ትርፍ አገኘሁ አለ። በአንድ አክሲዮን የተመዘገበው ትርፍ 68.55 በመቶ መሆኑን ኩባንያው ዛሬ ባካሄደው ዓመታዊ የባለ አክሲዮኖች ጉባኤ ላይ ያቀረበው ሪፖርት ተናግሯል። ሕብረት ኢንሹራንስ በ2017 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን የተናገረ ሲሆን ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ79 በመቶ ጭማሬ አሳይቷል ብሏል። ኩባንያው ከግብር በኋላ ያገኘው የተጣራ ትርፍ 843 ሚሊዮን ብር ሲሆን ይህም ከቀዳሚው አመት ጋር ሲነፃፀር በተመሳሳይ የ79 በመቶ እድገት ማሳየቱን ከሪፖርቱ ተመልክተናል። በአንድ አክሲዮን የተመዘገበው ትርፍ (Earnings Per Share) አምና ከነበረው በ47.78 ከመቶ ወደ 68.55 ከመቶ ከፍ ያ
Dec 5, 20252 min read


ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የብር የመግዛት አቅም ከዶላር አንፃር በ6 ብር ተዳክሟል፡፡
ህዳር 25 2018 ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የብር የመግዛት አቅም ከዶላር አንፃር በ6 ብር ተዳክሟል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠናከር እንዳለበት የሚጠበቀው የብር የመግዛት አቅምን እየተዳከመ ቀጥሏል፡፡ ይህም የሰዎችን የመግዛት አቅም የሚፈትን፤ በተለይ ከውጭ የሚመጡ ቁሶችን ዋጋ ደግሞ እጅጉ የሚያስወድድ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ከወጭ ንግድ እና ከተለያዩ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ ምንጮች እየተገኘ ያለው ዶላር ከአምናው ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑ እና በመሰል ምክንያቶች የውጭ ምንዛሬ ገበያው በራሱ መረጋጋት ይጠበቅበት ነበር ያሉት የፕራግማ ካፒታል መስራችና የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ባለሙያው መርዕድ ፍቅረዮሐንስ ናቸው፡፡ ይሁንና በብልሹ አሰራር ፣ በባንኮች ግልፅ ያልሆነ የውጭ ምንዛሬ ግብይትና በተለያዩ ች
Dec 4, 20251 min read


ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች በፈረሡላ 8,000 እና 9,000 ብር ይገዛ የነበረ ቡና ዋጋ በእጥፍ በመጨመሩ ላኪዎች እየተቸገሩ ነው ተባለ።
ህዳር 25 2018 ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች በፈረሡላ 8,000 እና 9,000 ብር ይገዛ የነበረ ቡና ዋጋ በእጥፍ በመጨመሩ ላኪዎች እየተቸገሩ ነው ተባለ። ላኪዎች በዚህ ዋጋ ቡና እየገዙ ለአለም ገበያ ማቅረብ እንደሚከብዳቸው የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ተናግሯል። አርሶ አደሮች እና ላኪዎች ዋጋውን ከፍ ያደረጉት ወደፊት ይበልጥ ይጨምራል በሚል ግምት እንደሆነም ማህበሩ ጠቅሷል። ወደ ውጪ ቡና የሚልኩ ነጋዴዎች ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች ምርቱን የሚገዙበት ዋጋ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ተናግሯል፡፡ የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ግዛት ወርቁ እንዳሉት ቀደም ሲል በፈረሱላ ስምንት ሺህ እና ዘጠኝ ሺህ ብር ከአርሶ አደሮችና አቅራቢዎች ይገዛ የነበረ ቡና አሁን በፈረሱላ እስከ ሃያ ሺህ ብር እየተባ
Dec 4, 20251 min read
ህዳር 25 2018 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሁለት ሚኒስትሮችን እና የአንድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሹመትን አፀደቀ።
ሹመታቸው በምክር ቤቱ የፀደቀላቸው የሠላም ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ እድሪስ፤ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቢንያም ኤሮ ናቸው። አቶ መሃመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተሹመው ስራ የጀመሩት ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም እንደነበር ይታወሳል። አቶ አዲሱ አረጋ ደግሞ ሐምሌ 25/ 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብርና ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ አንድ የምክር ቤቱ አባል በተለይ የሠላም ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ እድሪስ ከተሾሙ ዓመት እንዳለፋቸው በመጥቀስ ሹመቱ እስከ አሁን በምክር ቤቱ ሳይጸድቅ መቆየቱ አግባብ ነው ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ በሰጡት ምላሽ በተለያዩ ምክንያቶች ሹመቱ በምክ
Dec 4, 20251 min read


ህዳር 25 2018 በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ወስደው ሰፈራ መሬት ከወሰዱ ባለሀብቶች እስከ 75 በመቶው ወደ ልማት ሲገቡ አይታይም፡፡
መሬቱ ላይ ለመስራት ሳይሆን በተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ፈቃድ የባንክ ብድር ለማግኘት አልመው ወደዚህ ስራ የሚገቡ አሉ ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ 7,000 የሚሆኑ ባለሃብቶች በእርሻ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት 2.2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ ክልሎች መውሰዳቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ባለሃብቶቹ መሬቱን የወሰዱት ለገበያ የሚውሉ የተለያዩ ሰብሎችን ለማምረት እንደሆነ መረጃው ያመለክታል። ለግብርና ኢንቨስትመንት ከተሰጠው 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት እስከ አሁን ባለሃብቶቹ የለማው ግን 25 በመቶው ብቻ እንደሆነ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል። የለማው 25 በመቶ መሬትም ቢሆን ምርታማነቱ አጥጋቢ እንዳልሆነ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የመስሪያ ቤታቸውን የ2018 በጀት አመት የሶስት
Dec 4, 20252 min read


600 ሚሊዮን አፍሪካዊያን አሁን ድረስ የኤሌክትሪክ ብርሃን ማየት እንዳልቻሉ የአፍሪካ ህብረት ተናገረ።
ህዳር 24 2018 600 ሚሊዮን አፍሪካዊያን አሁን ድረስ የኤሌክትሪክ ብርሃን ማየት እንዳልቻሉ የአፍሪካ ህብረት ተናገረ። ባለው የተደራሽነት ችግር ምክንያት 1 ቢሊዮን ገደማ አፍሪካዊያን ምግባቸውን የሚያበስሉት ንፅህናውን ባልጠበቀ እና ባህላዊ በሆነ መንገድ ነውም ተብሏል። ይህ የተባለው ፊታችን ታህሳስ 1 እና 2 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን የአፍሪካ ኢነርጂ ብቃት ጉባኤን በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ነው። መግለጫውን የሰጡት በአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽነር የሆኑት ሌራቶ ማታቦጌ፤ አፍሪካ ኤሌክትሪክን ለህዝቧ ለማዳረስ ገና ብዙ ስራዎች ይጠብቋታል ብለዋል። የጉባኤው አላማ የህብረቱ አባል ሃገራት በኤነርጂው ዘርፍ ያላቸውን ተሞክሮ የሚጋሩበት፣ በየሃገራቱ ያሉ የኤነርጂ ብቃትና ቁጠባ ስትራቴጂዎች አተገ
Dec 3, 20251 min read


የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 100ሚሊዮን ብር ወጪ ያደረገበትንና የቁጥጥር ባለሙያዎቹን የሚከታተልበት ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናገረ።
ህዳር 24 2018 የአዲስ አበባገቢዎች ቢሮ 100ሚሊዮን ብር ወጪ ያደረገበትንና የቁጥጥር ባለሙያዎቹን የሚከታተልበት ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናገረ። ግብር ከፋዮችን ለመከታተል የሚሰማሩ የመስሪያ ቤቱ የቁጥጥር ባለሙያዎችን ካሜራ የተገጠመበት የደምብ ልብስ አልብሶ ማሰማራቱን ቢሮው ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርቶ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል። የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ወደዚህ ስራ የተገባበትን ምክንያት ሲያስረዱ የቁጥጥር ባለሙያዎች ያለ አግባብ ይቀጡናል፤የእጅ መንሻ እንድንሰጥ ይደራደሩናል የሚሉና ሌሎችም ቅሬታዎች ተደጋግመው ከግብር ከፋዩ የሚመጡ በመሆኑ ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ነው ብለዋል። ባለሙያዎቹ የሚለብሱት ካሜራ የተገጠመበት የደምብ ልብስ በቀጥታ በማዕከል ከተተከለው የቁጥጥር ካሜራ ጋር የተገናኘ ነው የሚሉት አቶ ቢኒያም፤
Dec 3, 20251 min read


በኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ለጋሾች ድጋፍ መቀነስ በኤችአይቪ መከላከልና ህክምናው ላይ እያሳደረ ያለው ተፅዕኖ
ህዳር 24 2018 በኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ለጋሾች ድጋፍ መቀነስ ምክንያት በኤችአይቪ መከላከልና ህክምናው ላይ ተጽዕኖ እንዳይበረታ ካልተሰራ የበሽታውን መከላከል ስራ ወደኋላ እንዳይመልሰው ያሰጋል ተባለ፡፡ ለዚህም በመንግስት እንዲሁም በአገር በቀል ድርጅቶች በኩል የሚሰራው ስራ መጠናከር እንዳለበት ተነግሯል፡፡ የአለም ኤድስ ቀን በኢትዮጵያ እየታሰበ ነው፤ የዘንድሮ ቀን የሚታሰበው ደግሞ ችግሮችን በመቋቋም የኤችአይቪ ኤድስ ( #HIV_AIDS ) ምላሽ ዘላቂነት ማረጋገጥ ላይ አተኩሮ ነው ተብሏል፡፡ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የድጋፍ መቀነስ በተለይም የበሽታው መከላከል ላይ ተጽእኖ ከዚህ በላይ እንዳይሰፋ የሀገር ውስጥ ሀብት በማሰባሰብ አገልግሎቶች እንዳይቋረጡ ማድረግ ላይ መሠራት እንዳለበት የተነግሯል፡፡ በኢትዮጵያ በድጋፍ ላይ የሚሰሩት
Dec 3, 20252 min read


የአ/አ ት/ት ቢሮ ከት/ቤቶች ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ለወላጆች ቅሬታ ፈጥሯል
ህዳር 24 2018 የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ለወላጆችና መምህራን ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ ቢሮው ከ256 ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 40,000 ተማሪዎች በ54 ማዕከላት በተሻለ የማስተማር ችሎታቸው በተመረጡ መምህራን ከመደበኛው የትምህርት ቀን ወጪ የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠሁ ነው ብሎ ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አሰራር በሌሎች ሀገራትም የተለመደ ቢሆንም ከተማሪ ወላጆችና መምህራን በማጠናከሪያው ላልተካተቱ ተማሪዎችስ ምን ታስቧል? የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡ የተማሪ ወላጆችና መምህራን ጥሩ ውጤት ላላቸው ተማሪዎች ማጠናከሪያ ከመስጠት፣ በትምህርት አቀባበላቸው ደከም ያሉትን ማበረታታት አይሻልም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ትምህርት ቢሮው
Dec 3, 20251 min read


ከተሰጣቸዉ የስልጣን ድንበር ተሻግረዉ የሚሰሩ ኤጀንሲዎች
ህዳር 23 2018 መመሪያዉ በሚጠይቀዉ፣ ህጉ በሚያስገድደዉ ልክ ሆነዉ፣ ቢሮ ከፍተዉ ሰራተኛ ቀጥረው፣ ህጋዊ ሆነዉ፣ ፍቃድ አዉጥተው፣ ሰራተኛን ወደ ውጪ ለመላክ ሃላፊነት ወስደዉ፣ ደንብ አክብረዉ በስነምግባር የሚሰሩ ኤጀንሲዎች አሉ፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ፋቃድን ተገን አድርገው፣ የተጣለባቸዉን ሃላፊነት ወደ ጎን ትተው፣ ህግ ጥሰው፣ ደንብ ተላልፈው፣ ከተሰጣቸዉ የስልጣን ድንበር ተሻግረዉ የሚሰሩ ኤጀንሲዎች ቁጥራቸዉ ትንሽ አይደለም፡፡ በተለይም ከተፈቀደላቸዉ ሀገር ውጪ መላክ፣ በተለያዩ ህግ መተላለፎች ፍቃዳቸዉ ከተሰረዘ በኋላ መስራትና ገንዘብ መቀበል በተደጋጋሚ ኤጀንሲዎች የሚጠየቁባቸዉ ጥፋቶች እንደሆነ ይነሳል፡፡ በተለይም ኤጀንሲዎች በምንም ምክንያት ስራ ፈልገዉ ከሚሄዱ ሰዎች ብር መቀበል እንደማይችሉ በህግ ተጠቅሶ፣ በአዋጅ ሰፍሮ ቢገኝም
Dec 2, 20252 min read


ከ25 ዓመታት በኋላ ከአውሮፕላን የሚወጣውን በካይ ጋዝ ወደ ዜሮ የተጠጋ ለማድረግ ኢትዮጵያ እንዴት እየተዘጋጀች ነው?
ህዳር 22 2018 ከ25 ዓመታት በኋላ ከአውሮፕላን የሚወጣውን በካይ ጋዝ ወደ ዜሮ የተጠጋ ለማድረግ በአለም ላይ እቅድ አለ፡፡ ኢትዮጵያ ለዚህ እንዴት እየተዘጋጀች ነው? የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2
Dec 1, 20251 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








