top of page

''ኢትዮጵያን የትኛውም ትንኮሣ ከጀመረችው የብልፅግና ጉዞ አያስቆማትም'' ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

  • sheger1021fm
  • Dec 8, 2025
  • 1 min read

ህዳር 29 2018 


''ኢትዮጵያን የትኛውም ትንኮሣ ከጀመረችው የብልፅግና ጉዞ አያስቆማትም'' ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።


የሚገጥመንን እያንዳንዱን ፈተና ወደ ዕድል በመቀየር የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን እናደርጋለንም  ብለዋል።


20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት  በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው፡፡


በአከባበሩ ላይ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን መልዕክቶችም ተላልፈዋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባደረጉት ንግግር በዓሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚደምቁበት ነው ብለዋል።


ኢትዮጵያውያን መተባበርን እና በአንድነት መቆምን የጋራ ሃብታችን እናድርግ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።


ኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች የሚደነቁ ውጤቶችን እያስመዘገበች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ጥረት ለማደናቀፍ በየጊዜው ሙከራዎች እንደሚደረጉም ጠቅሰዋል።


ማንኛውም ትንኮሳ ግን ኢትዮጵያን ከብልፅግና ማቆም አይችልም ሲሉ ተናግረዋል።


የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ከጋራ ታሪካችን እና እሴታችን የተቀዳ የጋራ ማንነት ሊኖረን ይገባል ብለዋል።


በዓሉ የመመካከር እና የመወያየት ባሕል በኢትዮጵያ እንዲያድግ ረድቷል ያሉት ደግሞ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ናቸው።


ንጋቱ ረጋሳ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page