ከተሞች ሲለሙ ያለፉበትን የረዥም ታሪክ አሻራ የሚያሳዩ የኪነ ህንፃና መሰል ቅርሶች እንዳይጠፉ ጥናትን እና ወይይትን መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 1 min read
ህዳር 30 2018
ከተሞች ሲለሙ ያለፉበትን የረዥም ታሪክ አሻራ የሚያሳዩ የኪነ ህንፃና መሰል ቅርሶች እንዳይጠፉ ጥናትን እና ወይይትን መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡
ጥያቄው የቀረበው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ75ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ልደታ በሚገኘው የቴክኖሎሎጂ እና ቢልት ኢንቫይሮመንት ኮሌጅ ‹‹በቅርስ ጥበቃ እና ጥናት ላይ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች›› በሚል መሪ ቃል ባሰናደው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
በቅርስ ጥበቃ እና ጥናት ላይ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች በሚል ርዕስ ጽሁፍ ያቀረቡት አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ ስለቅርስ ያለው አረዳድ ዝቅተኛ መሆን፣ የበቂ በለሞያ እጥረት እና መሰል ችግሮች ለዘርፉ እንቅፋት መሆናቸውን ዘርዝረዋል፡፡
የወይይቱ ተሳታፊዎች እና ባለሙያዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ፖለቲካ ለመስኩ ስጋት መሆንን አስረድተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ያሬድ እንሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🟦Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1








