top of page

በኢትዮጵያ በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች፤ የሚደርስባቸው የመብት ጥሰት ቀጥሏል ተብሏል፡፡

  • sheger1021fm
  • 32 minutes ago
  • 2 min read

ህዳር 26 2018


በኢትዮጵያ በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች፤ የሚደርስባቸው የመብት ጥሰት ቀጥሏል ተብሏል፡፡

 

ይህ የተባለው ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (Forum For Social Studies) የተሰኘ ተቋም በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችን በተመለከተ እየሰራው ላለው ፕሮጀክት ከሚመለከታቸው አካላት ግብዓት ለመሰብሰብ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው፡፡

ree

የፕሮጅክቱ ከዋኝ ብድን አባል የሆኑት ደግነት አበባው(ዶ/ር) በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች የበዙ ችግሮች እየገጠሟቸው እንደሆነ አንስተዋል፡፡

 

ከሀገሪቱ የዋጋ ንረት ጋር የማይጣጣም ክፍያ፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ያለመወሰን፣ እንዳይደራጁ መከልከል፣ ምቹ ያልሆነ የስራ ቦታን ጨምሮ ሌሎች ተደራራቢ ችግሮች በሰራተኞቹ ላይ እንደሚደርሱ አስረድተዋል፡፡

 

በሀገሪቱ ካለው የስራ አጥ ብዛት አንጻር አንድ ሰው ስራ ማግኘቱ እንጂ በስራ ቦታው ምን ያህል መብቱ ተከብሮለታል የሚለው ችላ እንደተባለ የጠቀሱት ደግሞ ከኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን የተወከሉት ተሳታፊ ናቸው፡፡

 

ምንም እንኳ የተወሰኑ የህግ ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮች ቢኖሩም የሰራተኛውም ሆነ የአሰሪው መብት የሚጠብቁ አሰራሮች በህግ ተደንግገዋል፤ ነገር ግን ተፈጻሚነታቸው ደካማ ነው ሲሉ ተናግረዋል ተሳታፊው፡፡

 

ከኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ባለሞያዎች ማህበር እንደተወከሉ የተናገሩት ሌላ የመድረኩ ተሳታፊ፤ በመድረኩ በሰፊው ተነስቶ በነበረው የሰራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን አስመልክተው ሲናገሩ፣ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገሮች ልምድ ልትወስድ ይገባታል ብለዋል፡፡

 

ለአብነትም በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት የምትታወቅው ቱርክ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ወስና፤ ይህም አንዳንዴ በ6 ወር አንዳንዴ በአንድ ዓመት የጊዜ ልዩነት የሀገሪቱን የዋጋ ንረትን ከግምት በማስገባት ዝቅተኛ የደመወዝ ለወለል ተግባራዊ እያደረገችና በዚህም ውጤታማ እንደሆነች አብራርተዋል፡፡

 

በአንዳንድ ኢንዱስትሪዎች የሚሰሩ ሰራተኞች መጸዳጃ ለመሄድ ራሱ የሚፈቀደው የተወሰነ ሰዓት እንዳላቸው ወይም በየተራ እንጂ መጸዳጃ ቤት በሚፈልጉበት ጊዜ መሄድ እንደማይፈቀድላቸው በመድረኩ የተሳተፉ የዘርፉ አካላት ሰናገሩ ሰምተናቸዋል፡፡

 

ree

በሌላ በኩል ኢንዱስትሪዎች የሚከፍሉት ክፍያ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ አሁን አሁን የሚቀጠር ሰራተኛ ራሱ በማጣታቸው እየተዘጉ  ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች  መኖራቸውን የጠቀሱት ደግሞ ከኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ፣ ቆዳ እና ልብስ ስፌት ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን የተወከሉት ይማም ሁሴን ናቸው፡፡

 

የህግ ባለሞያዋ ቤተልሄም ከፋለ ደግሞ በመጀመሪያ ሰራተኛው ራሱ ስለ መብቶቹ በቅጡ ያውቃል ውይ ሲሉ ጠይቃዋል፡፡  ይህንን ስናሳውቀው ነው ሰራተኛው መብቶቹን እንዲከበርለት ሊናገር የሚችለውም ብለዋል፡፡

 

በተለይ በኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የሚበዙት ከገጠሪቱ አካባቢ የሚመጡ ስለሆኑ ስለመብቶቻቸው መጠየቅም ሆነ የማወቅ ልማድ አያዳብሩም ሲባል ሰምተናል በመድረኩ፡፡

 

ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወክለው ሀሳባቸውን የሰጡት ጤፎቴ ፍላቴ፤ በኢንዱስትሪዎች ምልከታ በምናደርግበት ወቅት የተለያዩ ሰራተኞቹን ሊጎዱ የሚችሉ ችግሮች እናስተውላለን ሲሉ በኢንዱስትሪ ሰራተኞች ስለሚደርስባቸው፡፡

 

ስለችግሮቹ  ሰራተኞቹን በምጠይቃቸው ወቅት አይናገሩም፤ ይህም ከተናገርን በኋላ ጫና ይደርስብናል ብለው ካላቸው ፍርሃት የተነሳ እና ሌሎች አማራጮች ስለሌላቸው ነው ብዬ አስባለሁ ሲሉ ተናግዋል፡፡

 

በዘርፉ የሚሰሩ የውጪ እና የሀገር ውስጥ ዜጎችም የሚታዩበት አተያይ የተጋነነ እና ልክ ያለሆነ እንደሆነ በመድረኩ ተሳታፊዎች ሲናገሩ ሰምተናል፡፡

 

ለአብነትም አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ እና እንድ ኢትዮጵያዊ የማይራራቅ ስራ እየሠሩ የሚከፈላቸው ክፍያ ግን በ10 ሺዎች  የሚራራቅ እንደሆ ተጠቅሷል፡፡


 ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ማንያዘዋል ጌታሁን

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page