top of page

ራሚስ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ ከ4.2 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • 11 minutes ago
  • 1 min read

ህዳር 29 2018


ራሚስ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ ከ4.2 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናገረ።


ይህም በአንድ ዓመት ውስጥ የ85 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ሲል ባንኩ ትናንት ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ባወጣው ሪፖርት ተናግሯል።


ራሚስ ባንክ በበጀት ዓመቱ  ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ በማስመዝገብ ወደ ትርፍ ተሸጋግሬያለሁም ብሏል።


ገቢው በዓመቱ ውስጥ የ3,726 ከመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።

ree

ራሚስ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰቡንም ጠቅሷል።


የቅርንጫፎቹን ብዛት 47፣ የደንበኞቹ ብዛት ደግሞ 352,000 መድረሳቸው በሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል።


ባንኩ በበጀት ዓመቱ ማገባደጃ ላይ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያንና የካርድ ባንኪንግ አገልግሎቶቹን ለደንበኞቹ ማስተዋወቁን እና  የላቁ የዲጅታል ባንክ አማራጮችን እንደ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ዋሌት እና ኢ–ሙራባሃ የዲጀታል አገልግሎቶችን ለመተግበር  እየሰራ መሆኑን አስረድቷል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page